(ጌታቸው ሽፈራው)

ተከሳሾች ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት እንዲነሱላቸው ጥያቄ አቀረቡ

“እሱ ተከራካሪ፣ እሱ መልዕክት አስተላላፉ፣ እሱ ዳኛ ሊሆን አይችልም” አቶ አታላይ ዛፌ
“የተከሰሳችሁት በወልቃይት አማራ ማንነት ነው ወይስ በሽብርተኝነት የሚለው የሚታይ ይሆናል” ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት

“እኚህ ዳኛ በማህበራዊ ሚዲያ ያቀረቡት የህወሓትን አቋም ነው” ዘመነ ጌቴ

 

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት የግራ ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት ሊዳኙን አይገባም ሲሉ ተከሳሾች ጥያቄ አቅርበዋል። ዛሬ ህዳር 11/2010 ዓም የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት በአቶ አታላይ ዛፌ አማካኝነት በዳኛው ላይ ተቃውሟቸውን ሲያቀርቡ በግንቦት 7 እና ኦነግ ክስ የቀረበባቸው ሁሉም ችሎት ውስጥ የነበሩ ተከሳሾች ጥያቄው የሁላችን ነው በማለት ቆመው ተቃውሟቸውን ገልፀዋል። ወልቃይት አማራ ነው ብለው በህገ መንግስቱ መሰረት ጥያቄያቸውን በማቅረባቸው መታሰራቸውን የገለፁት አቶ አታላይ ዳኛ ዘርዓይ በማህበራዊ ሚዲያና በቴሌቪዥን ወልቃይት የትግራይ ነው እያሉ አቋማቸውን እየገለፁ ሊዳኙዋቸው እንደማይገባ ተቃውሞ አቅርበዋል። አቶ አታላይ ”እሱ ተከራካሪ፣ እሱ መልዕክት አስተላላፉ፣ እሱ ዳኛ ሊሆን አይችልም” ብለዋል። ዳኛ ዘርዓይ በበኩላቸው “የተከሰሳችሁት በወልቃይት አማራ ማንነት ነው ወይስ በሽብርተኝነት የሚለው የሚታይ ይሆናል” ሲሉ መልሰዋል።

በእነ ክንዱ ዱቤ መዝገብ ስር የተከሰሱትም ተቃውሟቸውን ያቀረቡ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ ዘመነ ጌቴ “ማዕከላዊ የተደበደብኩት ወልቃይት የማን ነው እየተባልኩ ነው። እኚህ ዳኛ በማህበራዊ ሚዲያ ያቀረቡት የህወሓትን አቋም ነው። የከሰሰኝ ህወሓት ነው። ስለሆነም ግለሰቡ የፖለቲካ ወገንተኝነት አለባቸው። በመሆኑም ጉዳያችንን በገለልተኝነት ሊያዩልን ይችላሉ ብለን አናምንም” የሚል ተቃውሞውን አቅርቧል።

በሌሎች መዝገቦችም ዳኛ ዘርዓይ እንዲነሱ ተቃውሟቸውን ያቀረቡ ሲሆን ዳኛው ይነሱልን ያሉበትን ምክንያት በፅሁፍ እንዲያቀርቡ ለህዳር 14፣15 እና 18/2010 ዓም ቀጠሮ ተይዟል።

አቶ ዘመነ ጌቴ ዳኛ ዘርዓይ ወልደሰንበት በማህበራዊ ሚዲያዎች አወጡት ያሉትን ፅሁፍ ይህን ማያያዣ በመጫን ማንበብ ይቻላል፡፡ ( የወልቃይት የማንነት ጥያቄ – በታሪክና በህገ መንግስቱ) http://hornaffairs.com/am/2016/06/02/ethiopia-wolqait-identity-history-constitution/ ( PDF )

 

****************

(አያሌው መንበር)

ለማንኛውም #ስለዘርዓይ ወልደሰንበት November 4 ይህንን ብለን ነበር። ሶስት የህግ ባለሚያዎችም በጉዳዩ ላይ አስተያየት ሰጥተውበት ነበር።

#ዘርዓይ_ወልደሰንበት (ለረጅም ጊዜ ይጠቀምበት በነበረው የፌስቡክ ስሙ ዘራይ ወልቃይት) “ወልቃይት የትግራይ ነው” በማለት በጭፍንና በጥላቻ የተሞሉ ፅሁፎችን ይፅፍ የነበረ እና በ2000ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒርቨሲቲ በህግ የተመረቀ ነው። ቤተሰቦቹ ናዝሬት እንደሚኖሩ የታወቀው ይሄ “ዳኛ” ባለፈው 2016 “ወልቃይት የትግራይ ነው” የሚል አስቂኝ ትርክት ፅፎ በህወሃቱ “Horn Affairs” በእነ ዳንኤል ብርሃኔ በሚመራው ሚዲያ ያስነበበንና አሁን ደግሞ ወልቃይት መሬቱም የጎንደር ህዝቡም አማራ ነው ብለው በህጋዊ መምገድ እየጠየወቁ ያሉትንና እና ይህንን በማለታቸው “በሽብርተንነት” የተከሰሱ የወልቃይት አማራዎችን የፍርድ ሂደት እየዳኘ ያለ ሰው ነው።

በእስር ላይ የሚገኙ የወልቃይት የአማራ ማንነትን የኮሚቴ አባላት ላይ ፍርድ እየሰጠ ያለው የትግሬ ወያኔ ካድሬና ዳኛ ዘርዓይ ወለደሰንብት

ልብ በሉ እየዳኘ ያለው ወልቃይት አማራ ነው የሚል ፀሀፊ በዳኛ ስም ቀጭ ብሎ እኛ አማራ ነን የሚሉ የእርሱ ባላንጣዎችን። ይህ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 4ኛ ወንጀል ችሎት ዳኛ ሁኖ የሚሰራውና “ወልቃይት አማራ ነው” የሚለው ትግሬ እና ወልቃይት አማራ ነው የሚሉትን “የሚዳኘው” ዘራይ “አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ” እንዲሉ ወልቃይት ትግሬ አለመሆኑን በህግም በሰነድም ሲረጋገጥበት ያደረገው ቢኖር የወልቃይት የአማራ ብሄርተኝነት የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴዎችን አሁንም ከህግ ውጭ በመተርጎም “ጉዳያቸው በአማራ ክልል ፍ/ቤት” ሊታይ አይገባም በሚል አሁንም ሌላ የውሸት ድርሰት በመፃፍና ሌላ በመስኮት የተመረቀ የሚመስል ዳኛን እንዲደግፈው አሞኘውና በጋራ ብይን ሰጠ። ይህኛው የዋሁ የደበብ ተወላጅ ነው የሙባለው ዳኛ ያዕቆብ ይባላል። ህግን አኝኮ ውጦ የተመረቀው የአማራ ተውላጁ አወል ግን ከህግ ጋር አንቀፅ እና አዋጅ ጠቅሶ ይህ ውሳኔ ስህተት ነው በማለት ብይኑን አልቀበልም ብሎ በልዩነት ወጣ። ብይኑ ምን ይሆን? አሰራሩስ እንዴት ነው? ስንል አንድ የዛው አካባቢ ሰራተኛ የህግ ባለሙያን አነጋግረን እንዲህ ነው የሚተነትኑልን።

“በህገ መንግስቱ መሰረት የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት በየክልሎች ይቋቋማሉ ይላል።ሆኖም እመዚህ ሁለት ፍርድ ቤቶች በየክልሎች እስኪቋቋሙ ድረስ በህገ መንግስቱ ውክልና (Automatic Constitutional delegation” መሰረት የክልል ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወደፊት ይቋቋማሉ የሚባሉትን እና አሁን ፌደራል ላይ መዋቅር ያላቸውን ክልል ላይ የፌደራሉን ወክለው አገልግሎት ይሰጣሉ፤ ይህ ሲሰራበት የቆየና እየተሰራበት ያለ ነው።ለምሳሌ የኮሎኔል ደመቀን ክስ ብንመለከት በዚህ ህገመንግስታዊ መብት መሰረት ነው እየታየ ያለው።እጅግ ብዙ ጉዳዮችም በዚህ መልኩ እየታዩ ነው። ነገር ግን በአዋጅ 322/95 proclamation 322/2003 በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በተወሰነው መሰረት በተወሰኑ ክልሎች “የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ስለተቋቋሙ ክልሎች ጉዳዩን በውክልና አያዩም” ብሎ ውክልና የተነሳባቸው ክልሎችን ዘርዝሯል። ነገር ግን አማራ፤ ኦሮሚያ እና ትግራይ ክልሎች በዝርዝሩ አልተካተቱም”።እንዲሁም በዚሁ አዋጅ በእነዚህ ክልሎች የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት አልተቋቋሙም።” ሌላኛው የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህግ ምሩቅ ወዳጀ ደግሞ እንዴው ጉዳዩን እንዴት ታየዋለህ? ብየ ለጠየቅኩት ተመሳሳይ ጥያቄ ይህንን ይለኛል።ለጠቅላላ እውቀት እንደጠየቅኩት ብቻ ነበር የነገርኩት።ከላከልኝ በኃላ ግን ወደ ህዝብ ባወታውስ ስለው በደንብ አልፃፍኩትም እንጅ ምን ችግር ኣለው? አለኝ።

ይህኛው ልክ እንደ ያዕቆብ ደቡብ ክልል የተወለደ የዚሁ ክልል አንድ ብሄረሰብ አባል ነው።ሆኖም ደቡብ መወለድና ማደጉ እንደ ያዕቆብ አልያም እንደትግሬድ ዘርዓይ ህጉን ከማወቅ አላገደውም።እንዴያውም በምሳሌ ማስረጃ ሁሉ አጅቦታል። እናም ሰላምታውን በማሰቀደም ይጀምራል። “ሰላም ላንተ ይሁን አዩ ከህግ መሰረታዊ መርሆች አንዱ የዳኝነት ስልጣንወሰን (jurisdiction) ነው። ጉዳዩበተፈጸመበት ቦታ ነው መታየት ያለበት። በፈደራል ፍ/ቤቶች ስልጣን ስር የሚወድቁ ( eg. the so called terrorisim, corruption against properties of Federal gov’t… etc) ነገር ግን በክልሎች የድንበር ወሰን ውስጥ የሚፈጸሙ ወንጆሎች በክልሎች እንዲዳኙ ህግ ይደነግጋል። ይህ የሚሆነው ከፈደራል ፍ/ቤት አንድ ደረጃ ከፍ ባለ የክልል ፍ/ቤት ነው። ለምሳሌ የፈደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ስልጣን የሆነው ጉዳይ በክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይታያል። ለዚህ መሰረታዊ ምክንያት ማስረጃዎች ወንጀሉ ተፈጽሟል በተባለበት አከባቢ ስለሚገኙ ነው።

በተለይም ተከሳሾች ክሳቸዉን የመከላከል ህገ መንግስታዊ መብታቸው ማስረጃዎች እንዲጠቀሙ የሚረዳ መርህ ነው። በነገራችን ላይ እጅግ በበርካታ ተከሳሾች ከአርማጭሆ፣ ከዛላንበሳ፣ ከኑየር (ጋምበላ) ከስማዳ፣… ተከስሶ ጉዳያቸው አ/አበባ የታየ በመሆኑ ምስክሮቻችንን ማቅረብ አንችልም በማለታቸው ፍርድ ተሰጥቷል። ከጠቀስከው ዉሳኔ አንጻር የሚነሳው ሌላው ጉዳይ ኢት/ያ የምትከተለው civil law legal system የሚባለውን የህግ ስርዓት ሲሆን ይህ ስርዓት ለዳኞች የሚሰጠው ስልጣን የወጣዉን ህግ መተርጎም ብቻ ነው(ይህ በአውሮፓ ሀገሮች የሚዘወተር ስርዓት ነው፣ በአአመርካና ሌሎች ሀገሮች የሚተገበረው የህግ ስርዓት የዳኞች ዉሳኔ እንደህግ ያገለግላል.. common law legal system) ስለሆነም በውሳኔው በፓርላማ(ህግ አዉጪው) ያልተሻረውን ህግ ፍ/ቤቱ አይተገበርም ማለቱ ህገመንግስቱን ጭምር የሚጻረር ነው። ምክንያቱም በአንቀጽ 78 መሰረት በክልሉ የፈደራል ፍ/ቤት አልተቋቋመምና። አዋጅ ቁጥር 322/95 በመግቢያው በግልጽ ‘በተወሰኑ ክልሎች የፈደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዋቋቋም በማስፈለጉ፣ ይላል ። ስለሆነም ባልተቋቋመባቸው ክልሎች በህገመንግስቱ በተቀመጠው መሰረት የክልል ፍ/ቤቶች ጉዳዮችን ያያሉ ማለት ነው።” እንግዲህ የህግ ባለሙያው አስተያየት ይህንን ከላይ ያነበባችሁትን ይመስላል።

ሌላ ሶስተኛ የህግ ባለሙያና በመንግስት የፍርድ ቤት ዳኛም እንዲህ ሲል ነው የመለሰልኝ።”ህገ መንግስቱ በአንቀፅ 80 በግልፅ አስቀምጦታል።ይህንን ለማረጋገጥም የኮሎኔል ደመቀን ክስና እያየው ያለውን ፍርድ ቤት ማየት በቂ ነው።እርሱም ጉዳያቸው አዲስ አበባ እየታየ ያሉትም ክሳቸው ተመሳሳይ ነገር ግን በተለያየ ቦታ እየታየ ያለ ነው ሲል ይመልሳል።ምክንያቱም ከጀርባ ያለው ፖለቲካ ነው ሲል ያክላል።ይልቁንም ከዚህ ውሳኔ ጀርባ ያለውን በደንብ እንዳየው ሲጠቁመኝ። እናም በማጠቃለያየ ይህ ዘረኛ እና ከእውቀት የፀዳ ዳኛ ይህንን ቀላሉን የራሱን መንግስት ህገ መንግስትና አዋጅ ሳያውቀው ቀርቶ ሳይሆን ውስጡን በሞላው ዘረኝነትና ከፖለቲካ ፓርቲው በተሰጠው ተልዕኮ ነው ይህንን ጉዳይ ክልሎች ሊያዩት አይችሉም ሲል ብይን የሰጠው።የደቡቡ ያዕቆብም ምናልባት የእነርሱን ክልል ተሞክሮ ግራ አጋብቶት ይሁን ተባባሪ ሁኖ የዘራይን የተልዕኮ ውሳኔ ደግፎታል።በተቃራኒው ግን አንድ ወንበር ላይ የተቀመጠውና ተመሳሳይ ትምህርትን ያጠናው አማራ ክልል የተወለደው አወል ይህ ጉዳይ ከህገ መንግስቱም ከአዋጁም ጋር ሊጣረስ የሚችል ውሳኔ አልወስንም በማለት በልዩነት ወጥቷሏልተብል።እናም በህጉ መሰረት የአማራ ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቦቶች በውክልና የፌደራል ጉዳዮችን ማየት ይችላሉ የሰሞኑ ውሳኔ ከህገ መንግስቱም ተፃራሪ ነው። በዚህም የወልቃይት የአማራ ብሄርተኝነት የማንነት ጥያቄ አስተባባሪዎችን በሶስት ነገር ለመጉዳት ያግዘዋል።

1.ጉዳያቸውን ለማጒተት፣

2.የበለጠ ለህወሃቶች ቶርቸር እንዲመቻቹ በማድረግ

3. ቤተሰቦቻቸው እንዳይጠይቋቸው፣ ችግራቸውን ለህዝብና ሚዲያ እንዳያሰሙ ለማደረግ ማለት ነው።

ይህ ፍፁም አራዊትነት እንጅ ምን ሊባል ይችላል?አለማወቅ? ሴረኝነት? ኧረ ከሁሉም በላይ አራዊትነት ነው።