ንዳዶች «መቀሌ፤ የሚባል፤ የሚደረግበትን እንዳትሰማ-እንዳታይ የተዘጋባትን ስብሰባ አስተናገደች» ይላሉ፤ አድዋ ተሾመች። ሌሎች የመለስ ቡድን «ሲፈርስ»-የስብሐት ቡድን «ሲነግስ» አይነት አባባል አላቸዉ።

ሰወስቱ ፖለቲከኞች የስለላ ድርጅቶችን የሚመሩ፤ ይመሩ ወይም ያገለግሉ የነበሩ ናቸዉ

የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሐት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ነባር መሪዎቹን ሽሮ አዳዲስ ሾሞ ማራቶን ጉባኤዉን አጠናቅቋል። የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) መሥራች እና በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳርፈዉ የሕወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ ከአንድ ወር በላይ በፈጀዉ ጉባኤዉ «ሥር ነቀል»ግምገማ ማድረጉን አስታዉቋል። የሕወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ ግምገማ፤ የባለሥልጣናቱ ሹም ሽር እና ቃል ኢትዮጵያን ለሚያብጠዉ ፖለቲካዊ ቀዉስ መፍትሔ ይሆን ይሆን?

በ1984 የያኔዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኢሕዴን)የመጀመሪያዉን የአማራ ክልላዊ መንግሥት የመሠረተበት ስብሰባ ባሕዳር ዉስጥ ሲጀመር ስብሰባዉ ለጋዜጠኞች ዝግ ይሁን ክፍት የሚለዉ ሐሳብ ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ተሰብሳቢዎችን አካራክሮ ነበር።የስብባዉ መሪ የነበሩት ባለሥልጣን ለሕዝብ ታግሎ፤ ሕዝብን አታግሎ እዚሕ የደረሰዉ ኢሕዲን-ኢሐአዴግ ከሕዝብ የሚደብቀዉ የለም» አሉ። ወሰኑ።ሹማምንቱ መሿሿም-መፋተጋቸዉን፤ ጋዜጠኞቹም ማነፍነፍ መዘገባቸዉን ቀጠሉ።

1984 በርግጥ 2010 አይደለም።እንኳንስ ዘመኑ ፓርቲዉም ከኢትዮጵያነት ወደ ብሔርነት፤ ከሐገር አቀፍነት ወደ አማራነት፤ ከኢሕዴንነት ወደ ብአዴንነት ተለዉጧል።አድጓል ወይም ወድቋል።ኢሕዲን አልነዉ ብአዴን-ሕወሐት አይደለም።ግን የሕወሐት አምሳያ፤ እሕት፤ ወይም አጋራነቱ አንድ ሁለት የለዉም።

ሰሞኑን መቀሌ ላይ የሆነዉን፤ ከሩቅ የሰማነዉ ከ26 ዓመታት በፊት ባሕር ዳር ላይ ካየን እና ከሰማነዉ የሚቃረን መሆኑ ግልፅ ነዉ።በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን ከተደረጉ የፖለቲከኞች ጉባኤዎች ሁሉ የመቀሌዉ አንደኛዉ ባይሆን ከረጃጅሞቹ አንዱ ነዉ።አንድ ወር ካንድሳምንት ግድም ፈጀ።

ጉባኤተኞች በስብሰባቸዉ ማብቂያ ባወጡት መግለጫ የጉባኤያቸዉን ጠቃሚነት ፓርቲያቸዉ «ክልላዊና አገራዊ ተልዕኮዉን ከመወጣት አንፃር» በማለት ገልፀዉታል።ለሐገር እና ለክልል የሚጠቅም ያሉት ጉባኤቸዉ ግን እስከ ዉሳኔያቸዉ ድረስ ከሕዝብም

Äthiopien 40. Jahrestag TPLF (DW/T. Weldeyes)

ከመገናኛ ዘዴም ዝግ ነበር።

አንዳዶች «መቀሌ፤ የሚባል፤ የሚደረግበትን እንዳትሰማ-እንዳታይ የተዘጋባትን ስብሰባ አስተናገደች» ይላሉ፤ አድዋ ተሾመች።ሌሎች የመለስ ቡድን «ሲፈርስ»-የስብሐት ቡድን «ሲነግስ» አይነት አባባል አላቸዉ።የእሳቸዉም አስተያየት ተመሳሳይ ነዉ።

 እኝሕኛዉ ሁለተኛዉ።

የፖለቲካ ተንታኝ እና ደራሲ አቶ አስራት አብረሐም ደግሞ ድሮም-ዘንድሮም የሕወሐት ፖለቲካ ማለት የአድዋ ፖለቲካ ነዉ ይላሉ።

አዲስ አበባ እንደ ሹም ከላከቻቸዉ አንዷን እንደ ተሻሪ፤ ብዙዎቹን እንደ በሹመት ላይ ሹመት ደራቢ፤ እንደ ተሻሪ የሸችዉን አንዱን እንዳዲስ ተሿሚ ተቀበለች።ድፍን ኢትዮጵያ 26 ዓመት የምታዉቃቸዉን የትግራይ ፖለቲከኞች እንደገና በቴሌቪዥን መስኮት አየች።እንደ ፌደራላዊ መንግሥት ሚንስትር፤ እንደ ሥራ አስኪያጅ፤ እንደ ሰላዮች አለቃ የምታዉቃቸዉን እንደ ፓርቲ መሪም አወቀቻቸዉ።

ተሰብሳቢዎቹ የቀድሞዉን የሕወሐት መሪ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር የአቶ መለስ ዜናዊን ባለቤት ወይዘሮ አዜብ መስፍንን ከሕወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አግደዋል።ከመለስ መሞት በኋላ የፓርቲዉን የሊቀመንበርነት ሥልጣን የያዙትን የትግራይ ክልል ርዕሠ-መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱን ከሊቀመንበርነትም፤ ከሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልነትም ሽሯል።

ከስልጣን ያገዳቸዉ፤ ዝቅ ያደረጋቸዉ፤ ማስጠንቀቂያ የሰጣቸዉም ሌሎች ባለሥልጣንትም አሉ።እስካሁን የፓርቲዉ ምክትል ሊቀመንበር እና የኢትዮጵያ የመገናኛ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚንስትር ዶክተር ደረብረ ፅዮን ግብረ ሚካኤል የሕወሐት ሊቀመንበር፤ የቀድሞዋ የገንዘብ ሥለላ ማዕከል ኃላፊ የነበሩት ወይዘሮ ፈትለወርቅ (ሞንጆሪኖ) ገብረ እግዚአብሔር የፓርቲዉ ምክትል ሊቀመንበር ሆነዉ ተመርጠዋል።በፓርቲዉ አሰራር የሰወስተኝነቱን ደረጃ የያዙት የብሔራዊ መረጃ እና ደሕንነት ኃላፊ አቶ ጌታቸዉ አሰፋ ናቸዉ።

ከተሿሚ ተሻሪዎቹ ዕድሜ፤ የትዉልድ-እድገት ሥፍራ ይልቅ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳርፈዉ ፓርቲ ዉሳኔ ኢትዮጵያን ለሚያብጠዉ ፖለቲካዊ ቀዉስ የሚጠቅመዉ መኖር-አለመኖሩ ነዉ አነጋጋሪዉ።አቶ ፍፁም ብርሐኔ ፓርቲዉ የሚያስፈልገዉ የመርሕ እንጂ የሰዎች ለዉጥ አይደለም ባይ ናቸዉ።

የፖለቲካ ተንታኝ አስራት አብራሐም ደግሞ የፊተኞቹ ደብዘዝ-ያሁኖቹ ደመቅ አሉ እንጂ ለወጥ የለም ባይ ናቸዉ።የሕወሐት ዋና ዓላማም የኢትዮጵያ ሕዝብ ላነሳቸዉ ጥያቄዎች ተገቢ መልስ መስጠት ሳይሆን የነበረዉን (ስታትስኮ) ማስቀጠል ነዉ።

አቶ አስፋዉ ገዳሙም ተመሳሳይ ሐሳብ ነዉ ያላቸዉ።ሕወሐት ጥንትም ሆነ አሁን የሰዉ እንጂ የመርሕ ለዉጥ ማድረግ አያዉቅም። የሕዝብን ጥያቄም ከቁብ አይቆጥርም።

Äthiopien Stadt Mekelle (DW/Y. Gebreegziabher)

የሕወሐትን ከፍተኛ ሥልጣን አዲስ የተረከቡት ሰወስቱ ፖለቲከኞች የስለላ ድርጅቶችን የሚመሩ፤ ይመሩ ወይም ያገለግሉ የነበሩ ናቸዉ።የፖለቲካ ተንታኝ አስራት አብረሐም እንደሚሉት የሕወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ በሥለላ መስሪያ ቤት የሰሩ ወይም የሚሰሩ ፖለቲከኞችን የመረጠዉ በአጋጣሚ አይደለም።አቶ አስራት እንደሚሉት ሕወሐት ከኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች ወይም ከሌሎች ተቃዋሚዎች የበላይነቱ ይዞ የቀጠለዉ ሁለት ጠንካራ ምርኩዞችን ሙሉ በሙሉ በመያዝ ነዉ።ሥለላዉንና ጦር ኃይሉን።አብዛኛዉ ኢትዮጵያ በተቃዉሞ ጥያቄ፤ በአደባባይ ሠልፍ እና አመፅ በሚናጥበት ባሁኑ ወቅት ደግሞ ከፍተኛ መሪዎቹን የስለላ መስሪያቤት ባልደረቦች ወይም መሪዎችን ማድረጉ የበላይነቱን የማጣት ሥጋቱን ለማስወገድ እንዲጠቅመዉ አስቦበት ሳይሆን አይቀርም።

የሕወሐት አዳዲስ መሪዎች ከሌሎች የኢሕአዴግ አባል ፓርቲዎች መሪዎች ጋር የሚኖራቸዉ ግንኙነት እና የሚያሳርፉት ተፅዕኖ እስከየትነት ላሁኑ በግልፅ አይታወቅም።ባለፉት ሁለት ዓመታት በኦሮሚያ፤ በደቡብ እና በአማራ መስተዳድሮች የሚደረጉ ሕዝባዊ ተቃዉሞችን፤ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚነሱ የሙስና፤ የኑሮ ዉድነት፤ የፍትሕ፤ የሰብአዊ መብት ጥያቄዎችን ለመለስ አዳዲሶቹ መሪዎች አዲስ ዕቅድ መንደፋቸዉም አይታወቅም።መቀሌ ተሰበሰቡ፤ ከቀመሌ ነዋሪ ቢያንስ አንዱን ሻሩ፤ አዲስ አበባ ነዋሪ፤ አድዋ ተወላጆችን መረጡ። አበቁ። እኛም እናብቃ።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ