የኢትዮጵያ ካርታ

የኢትዮጵያ 

የነገይቱ ኢትዮጵያ በሦሥት የተቃዋሚ ድርጅቶች ዓይን ሲቃኝ።

የአገር ጉዳይ በተሰኘው ልዩ የራዲዮ መጽሔት ተከታታይ ፕሮግራም አገሪቱ በገባችበት የፖለቲካ ቀውስ እና በጊዜው ጥያቄዎች ዙሪያ የተወያዩ የሦሥት የተቃዋሚ ድርጅቶች ተጠሪዎች የነገውን አቅጣጫዎች አስመልክቶም የእኛ የሚሉትን ሃሳብ ይፈነጥቃሉ።

ለመሆኑ ምን ዓይነት ለውጥ? እንዴት? የሚሉትን ነጥቦች በውይይታቸው ይፈትሻሉ።

ተወያዮች:- ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች-ግንቦት 7 ሊቀመንበር እና የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ ምክር ቤት የጋራ ሊቀመንበር፤

አቶ ግደይ ዘርዓ-ጽዮን የኢትጵያ ሕዝብ ብሔራዊ ሸንጎ ጸሃፊ እና እንዲሁም፣ አቶ የሺ ዋስ አሰፋ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ናቸው።

ከገዢው ኢሕአዴግ በተለይም ደግሞ ሰሞንኑን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አመራርና አባላት ሹም ሽር ካደረገው የሕዝባዊ ወያኔ አርነት ትግራይ – ሕወአት ባለ ሥልጣናት ተጠሪዎች ለመጋበዝ ያደረግነው ጥረት ግን ለጊዜው አልተሳካም። ቃል በገቡበት መሠረት እንደተገኙ አነጋግረን እናቀርባለን።