December 6, 2017 00:54

መንግስቱ ሙሴ

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የተከሰተው የሱዳን ጦር ድንበር ጥሶ መግባትን አስመልክቶ የሚዘዋወር ሹክሹክታ ነው። ሱዳናዋያን የኢትዮጵያን ድንበር መጣስን አስመልክቶ የመጀምሪያ እንዳልሆነ ሁሉ በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎች የሱዳን ጦር ድንበር መጣስን አስመልክቶ አቤቱታ እያሰሙ ነው የሚል ዜና እየደረሰን ነው። በዚህ በማህበራዊ ሚዲያ እንዳየነው የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ መግባትን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል እየተዘዋወረ ይገኛል። በዚህ ድንበር አካባቢ አገራችን በአንድ ምእተ አመት የተወሰነ ሳይሆን ለአለፉ ብዙ ምእተ አመታት ሱዳን የይገባኛል ጥያቄ ይዛ ድንበራችንን መጣስ እና ሰፋፊ ውጊአወች ማድረግ። ለብዙ ዜጎች ህይወት መጥፋት ምክንያት የሆኑ ጦርነቶች መቀስቀስ እና ድንበር ጥሶ መግባት አድርጋለች። እናም ይህ ዜና ቢሰራጭ አይሆንም አልተደረገም ለማለት የሚያስችል እና ሱዳን በሰሜን ምእራብ ድንበራችን ብዙ ጉዳት ያደረሰች በመሆኑ ሊያጠራጥረን አይችልም። ወራውን አስፍታ እስከ ውስጥ በመግባትም ንብረት አውድማለች። በታሪካችን አንድን በጦርሜዳ በውጊያ የተሰው ንጉሠ ነገስትን አንገት በመቁረጥ ነፍስ እንዳለው ምርኮኛ ይዞ በመሄድ በጦርሜዳ ያልተደረገ ስራን ሰርታብናለች። የንጉሥ ተክለሃይማኖትን የበኩር ልጅ በመማረክ ሳትመለስ ቀርታለች ወዘተ። በ1980ወቹ የሱዳን ጦር ደጋግሞ ቢገባም ያኔ በቋራ እና በመላ ምእራብ ጎንደር እና ጎጃም ይንቀሳቀስ የነበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ሰራዊት (ኢሕአሰ) የሱዳንን ጦር በመውጋት ድንበሩን እንደተከላከለ ይታወቃል። ዛሬ ኢትዮጵያ በአንድ ጠባብ ኅይል የተያዘች እና እንዴውም ይህ ጠባብ ቡድን ከሱዳን ጋር ያለውን ግንኙነት ላለማሻከር ዮሀንስ የወደቁለትን ድንበር አሳልፎ እንደተደራደረበት እናውቃለን። ይህ በዚህ እንዳለ የደብረጺዮን ልዑካን ገደአሪፍ መግባትም በሹክሹክታ እየሰማን ነው። አምራኮባን፣ እንጉልጃ እና ተነድባ የተባሉ በአለፉት 35 አመታት የኢትዮጵያውያን የስደተኛ ካምፖች የነበሩ አሁን ግን ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ቀይረዋቸው ጥሩ የሱዳን ከተሞች የሆኑት እንደምናውቀው ህወሓት ደጋፊወች ስለአሏት ልዑካኑ ወደነዚህ ቦታወች ጎራ ብለው ነበር የሚልም ሀሜት አለ። ይህ ከምንሰማው ተባራሪ ዜና ጋር ተዳምሮ ስጋት ቢቀሰቅስ የሚጠበቅ ይሆናል ማለት ነው።
ሱዳን በድንበር ጉዳይ ከወያኔ ሊተባበር ትችላለ?
የሚል ስጋት በሰፊው እየተስተጋባ ነው። ይህ ከሆነ ብዙ ዜጎች ሊጎዱ እንደሚችሉ ሁላችንም ልናውቅ ይገባል። ለምሳሌ በኢትዮጵያ ሶማሌ በኩል አስካሁን ያልተቋጨው በኦሮሞ ዜጎቻችን ላይ የደረሰው የመፈናቀል፣ ሞት እና ንብረትን እየተው መሰደድ አንዱ ጉዳይ ምንም እንኳን የጠራ አቋም ባይወሰድም የህወሓት እጅ እንዳለበት ይገመታል። ይህ እውነትነት ከተረጋገጠ ደግሞ ህወሓት መቸውንም ለሀገር የምታስብ ስብስብ እንዳልሆነች ሁሉ በምስራቅ የፈጸመችውን ወንጀል በሰሜን ምእራብ ልትደግመው ትችላለች ማለት ነው። የሱዳን ጦር ድንበር ከጣሰ ልክ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ማርችህ 10 ቀን 1889 ዮሀንስ በጦርነት እንደተሰው ሁሉ ከአንድ ከስምንት ወራት በፊት ደርቡሽ እስከ ማህል ጎንደር ዘልቆ በመግባት አቢያተክርስቲያናት አቃጥለው ብዙ ንብረት ዘርፈው የንጉስ ተክለሀይማኖትን ልጅን ወይዘሮ ሰብለወንጌልን ማርከው እንደሄዱት እና በግዜው የጎጃምን እና የጎንደርን የገበሬ ጦር ያለመሪ እንደጎዱት ሁሉ ዛሬ ተመሳሳይ ሁኔታ ሱዳን ብትፈጥር የአለማቀፍም ሆነ የአህጉሯ ማህበራት አንድ እስኪሉ ሰፊ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል ሊገመት ይገባል። ይህ ጉዳት መቸም ወያኔ ኢትዮጵያን እንደሀገር የምትመለከት ስብስብ ሳትሆን የእኔ የምትለውን ትግራይን እስካልተነካች በአሁኑ ሰአት የምትጠላውን አካባቢ እና ሕዝብ ትከላከላለች የሚል እምነት ከብዙ ዜጎች ልቦና ወጥቷል። ለዚህ የእምነት ማጣት ዋናው ምክንያት ደግሞ ወያኔ በይፋ ከሱዳን ተደራድራ መሬታችንን አሳልፋ እንደሰጠች እና የውል ሰነዱ መቋጨት ባለመቻሉ እስካሁን ቢቆይም። ሱዳን ብትወር እንደመንግስት የራሷን ዳር ድንበር በስምምነት ያልተቻለ ስለሆነ በኃይል አስከበረች ወደሚል የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ በህዝባችን ሊሰራበት መቻሉን መገንዘብ ያስፈልጋል። ወያኔ በሰላማዊ ጥያቄ በምስራቅ እና በመላ ኦሮሚያ ስትወጠር ጎሳ ለጎሳን ማጋጨቷ እንደተጠበቀ ሆኖ። ከሶማሌ በኩል ያለው የታጠቀ እና መንግስታዊ ትብብር የተደረገለት በመሆኑ በኦሮሞ ዜጎቻችን ከባድ ጉዳት ሊደርስ ችሏል። ከዚህ በላይ በንፅጽር ለማሳየት የሞከርኩት በሰሜን ምእራብ ቢደገም ጉዳቱ ከፍተኛ ሊሆን እንደሚችል እና የዜጎችን ትኩረት ከመብት ጥያቄ ወደ ዋና የዳርድንበር እና የህልውና ጥያቄ ካዞረው በእርግጥም በጠላት በኩል በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንዲሉ ከፍተኛ ተጠቃሚ ህወሓት እና ደጋፊወቿ ሲሆኑ። ጉዳቱ መላ ኢትዮጵያውያንን ይነካል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!