06/12/2017 |

 

“እኔ የሚፈለግብኝን አደራ ተወጥቻለሁ። ከጥር 30ቀን 1982 እስከ ዛር የካቲት 9 ቀን 1982 ሞት ሽረት ትግል አድረጌአለሁ።የሻዕቢያን የጥፋት ዓለማ ለመግታት ያላደረግኩት ጥረት የለም። ከዚህ በሗላ ግን የራሴን ሕይወት በክብር ከማጥፋትና ለኢትዮጵያ ጀግኖችና ታሪክ ፀሐፊዎች ታላቅ ተምሳሌት ከመሆን ሌላ አማራጭ የለኝም። ጀግንነት ማለት በሁሉም መልክ ለጠላት አመች ሆኖ አለመገኘት ማለት ነዉ።…
“በዚች የኢትዮጵያ ህዝብ የባሕር በርና ዓለም አቀፍ ወደብ በሆነችዉ በምፅዋ ከተማና በቀይ ባሕር ጠረፍ ላይ
ቆሜ ሽጉጤን ለመጠጣት ዝግጁ ሆኜአለሁ። በ እዉነት እኔ ዛሬ በሞት ብሸነፍም በታሪክና በመጭዉ የኢትዖጵያ ትዉልድ ፊት አልሸነፍም። የ አፄ ቴዎድሮስን ዕድል በማግኘቴም በጣም እኮራለሁ። እኔ አሁን የተዘጋጀሁለት ሞት ዘለዓለማዊ ክብርና ሕይወት ይሰጠናል። በሻዕቢያ እንደ እነ ጀኔራል ጥላሁን እና ጀኔራል ዓሊ ሓጂ ተማርኬ የሻዕቢያን መሪዎች ዓይን ማየት ግን የሞት ሞት ነዉ። አፄ ቴዎድሮስ በእንግሊዞች እጅ ወድቀዉ ከመዋረድ ሞትን መርጠዉ የራሳቸዉን ሕይወት መቀቅደላ ላይ አጠፉ። እኔ ደግሞ በተራየ ከኢትየጵያ ሕዝብ መንግሥት የተሰጠኝን የጄኔራልነት ማዕረግ ሳላስደፍር ለመንግሥትና ለሕዝብ በገባሁት ቃል ኪዳን መሰረት አስቀድሜ የፈቀደዉን ያህል ተዋግቼና አዋግቼ ሻዕቢያን አራግፌአለሁ። እንደ ጦር መሪም እንደ ተራ ተዋጊም ሁኜ ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ይዤ ተፋልሜአለሁ። አሁን ግን ለመጨረሻዋ መስዋዕትነት ህይወቴን ለማጥፋት የቀሩኝ ጥቂት ደቂቃዎች ናቸዉ።… “ጎበዝ ስሙኝ! ይህ አደራ መልዕክቴ ነገ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይደርስ ይሆናል። ምናልባት አምለክ ካለ ከእናነተ አንዱ መልዕክቴን ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግሥት አደርስ ይሆናል። ዛሬ ሻዕቢያ ምፅዋን ተቆጣጥሬአለሁ በማለት የዓለምን መገናኛ ብዙሃን እንደሚያጨናንቅ ጥርጥር የለዉም። ይህ ደግሞ ለ ኢትዮጵያ ሀግርና ሕዝቧ ትልቅ አደጋ ነዉ። በቀይ ባሕር በራችን በኩል ብዙዉን ጊዜ ወረራ ፈጽመዉብን በተደጋጋሚ የሳፈርናቸዉና ፊት ለፊት ያልቻሉን ምዕራባዉያን ሀገሮችና ዓረቦች ዛሬ የሻዕቢያን ጊዜያዊ ድል ሰምተዉ ይፈነጥዛሉ። ምናልባትም የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ድንበር የሆነዉንና ለዘመናት በአባቶቻችን የደም ዋጋ ፀንቶ የቆየን የባሕር በራችንን በመዝጋት እንዲሁም ቀይ ባሕር የኢትዮጵያ ባሕር አይደለም በማለት በምድር ተወስነን እንድንቀር ይደረግ ይሆናል። ይህ ደግሞ የሞት ሞት ነዉ። “ ይሁን! ምንም ማድረግ አልችልንም። ሁሉም ነገር ከቁጥጥሬ ዉጭ ሆኗል። ከሙታን ዓለም መጥቼ ማረጋገጥ ባልችልም የፈለገ ጊዜ ይጠይቅ እንጂ ጀግናዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ የባሕር በር አልባ ሆኖ
፤በኢምፔርያሊስቶችና ጋሻ ጃግሬዎቻቸዉ ተሸንፎና እጁን አጣጥፎ አይቀመጥም። ይህ ከሆነማ የአፄ ዮሐንስ
የቀይ በሕር ተጋድሎ እና የጀግናዉ ራስ አሉላ አባነጋ አጥንት እንዲሁም የእኔን ጨምሮ የአበዮታዊ ሠራዊት
አባላት አጥንትና ደም የኢትዮ ያን ትዉልድ ሁሉ እሰከዘላለሙ የፋረዳል። ኢትዮጵያ ሀገሬ የጀግኖች
መፍለቅያና ገናና ታሪክ ያላት ሀገር ናት። በመሆኑም ጀግናዉ ሕዝቧ ሕዝባዊ የባሕር በሩ በሻዕቢያ ተይዞና
የጠላቶቹ መፈንጫ ሆኖ አይኖርም። የፈለገ ጊዜ ይቆይ እንጂ ሻዕቢያ ምፅዋን እንደያዛት ለዘላለሙ
አይኖርም”። ጊዜዉ ጠብቆ የኢትዮጵያ ጀግና ጠላትን ደምስሶ ምፅዋን ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሚያስረክብ
እምነቴ የፀና ነዉ።”
አሉና ትንፋሽ ዋጡ: የትንሽ ፋታ ወሰዱ። የጀኔራል ተሾመ ዓይን የቆሰለ የነብር ዓይን መስሏል፡ ከንፈራቸዉ
በዉሃ ጥም ደርቆ ቅርፊት ይዟል። ፊታቸዉ በደረቅ ላብ ዥንጉርጉር ሆኗል። ሆዳቸዉ ከወገባቸዉ ተጣብቋል።
በተሰበሰበዉ አባል ዉስጥ በሰፈነዉ ጸጥታና ዝምታ መሃል “እናንተ አብየታዊ መኮንኖች ባለሌላ ማዕረጎች!
ስሙኝ አንድ ምሳሌ ልንገራችሁ።” አሉ ጀኔራል ተሾመ ቆጣ ብለዉ።“አንድ ሰዉ ቤት ሲሰራ የሚሠራዉ ቤት
በርና መስኮቶች አሉት። አንድ ሰዉ ደግሞ ሞተ እንበል። መቃብር በርና መስኮት የለዉም። በርና መስኮት
የሕይወት ምልክቶች ናቸዉ። በመሆኑም ያለሀገር ነፃነትና ያለባሕር በር ብልጽግና ስለሌለ የኢትኦጵያ ሕዝብ
የባሕር በር ተነጥቆ የሚኖር ሕዝብ አይደለም። ከሻዕቢያ ጀርባ ሆነዉ ቀይ በሕር የኢትዮጵያ አይደለም የሚሉ
ሀገሮችና ጋሻ ጃግሬዎቻቸዉ ሁሉ በቀጥታም ሆኑ በተዘዋዋሪ ፍላጎታቸዉ የ ኢትዮጵያ ሞት ነዉ።
“ይህ ምሳሌ ከገባችሁ የባሕር በር የሌላት ሀገር ሞቶ ከተቀበረ ግለሰብ የምትለየዉ በትንሹ ነዉ። ምክንያቱም
የባሕር ሀብት ከማጣቷ በላይ ምርቷን ወደ ዉጭ ለመላክ የግዴታ ወደብ ስለምትከራይ ለወደብ ክፍያ
የምትከፍለዉ የገንዘብ ዉጭ ዜጎቿን ያደኸያል። በአኳያዉ ጠላቶቿን ባለወደቦቹን ያበለጽጋል። ይህ ዕድል
ለኢትዮጵያ እንዳይደርሳት ቀይ ባሕር የኢትየጵያ ትዉልድ ይፋረድ።፡ቀይ ባሕር ለእኔ ዘላለማዊ ቤቴ እንዲሆን
ወስኛለሁ። ደስተኛ እና ዕድለኛ ጀኔራል ነኝ። እኔ ብሞት ታሪኬ አይሞትም። የእኔ ታሪክ በእያንዳንዱ
ኢትዮጵያዊ ሕሊና ዉስጥ እንደሚኖር አምናለሁ። ቻዉ! ቻዉ!ቻዉ!” አሉና ጀኔራል ተሾመ ፤መኮንኖቹን
ከሰበሰቡበት ቦታ ተፈናጥረዉ ወደ ቀይ ባሕር ጠረፍ አመሩ። የባሕሩ፡ጠረፍ ከስብሰባዉ ቦታ በግምት ከስልሳ
ሜትር አይበልጥም። በፍጥነት ወደዚህ በሕር ጠረፍ ገሰገሱ። ክላሺንኮቭ ጠመንጃዉን አቀባብለዉና
አዉቶማቲክ ላይ አድርገዉ በቀኝ እጃቸዉ ጨብጠዋል፡ከምፅዋ ወደብ በስተቀኝ ከሚገኘዉ ወታደራዊ
ወደብና መደብር ላይ ሲደርሱም ለቀይ ባሕር ዉሃ መገደቢያ በተሰራ ግንብ ጠርዝ ላይ ጀርባቸዉን ወደ ቀይ
ባሕር ፊታቸዉን ወደ ምፅዋ ከተማ አድርገዉ ቆሙ። ቀጥሎ በእጃቸዉ የነበረዉን ክላሺንኮቭ ጠመንጃ ወደ
ቀይ ባሕር ወረወሩት። ከዚያም በወገባቸዉ ታጥቀዉት የነበረዉን ኮልት ሽጉጥ አወጡና የሽጉጡን አፈሙዝ
በአፋቸዉ ጎርሰዉ የካቲት 9 ቀን 1982 ዓ.ም ከጥወቱ 2፡10 ሰዓት ሲሆን ቃታዉን ሳቡት። የሽጉጥ ቶክስ
ድምፅ እንደተሰማ ወደ ጀርባቸዉ በቀይባሕር ዉሃ ላይ ወድቀዉ ሰጠሙ። ከጭንቅላታቸዉ የሚፈስ ደም
በቀይ ባሕር ዉሃ ላይ ቀልቶ ይታይ ነበር።
ምንጭ ፦ አይምፅዋ