የኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ- ባጣራሁት ልክ! (ሙሉቀን ተስፋው)

image_pdf

 

ማምሻውን በአርማጭሆና በመተማ አካባቢ ያሉ የአገር ተቆርቋሪና ድንበር ጠባቂ ሰዎችን ለማግኘት ጥረት አድርጌ ነበር፡፡ የአነጋገርኳቸውን ሰዎች አስተያየት ሳጠቃልለው የሚከተለው ነው፡፡
1. የሱዳን ወታደሮች በምራብ አርማጭሆ ወደ ውስጥ ገብቷል፤ ይህ ብቻ ሳይሆን የእርሻ ቦታዎችን አቃጥሏል፡፡ ለጊዜው ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ አራሾችን ቦታ አስነስቷል፡፡ ዛሬ የሱዳን የጦር ሔሊኮፍተር ከአብደራ በቅርብ ርቀት አርፋለች፡፡

2. ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን የሚሔዱ መኪናዎች እንደሁልጊዜው ሲዘዋወሩ ውለዋል፤ ምንም የተፈጠረ ችግር ያለ አይመሰልም፡፡

3. ኮር ሑመር አካባቢ የሱዳንና የወያኔ ወታደሮች አብረው ተደባልቀው ሲጠጡ ውለዋል፡፡ የሱዳን ወታደሮች ሲጠየቁ ከወያኔዎች ድንበራችሁን ሰጠናችኋል፤ ገብታችሁ ድንበራችሁን መጠበቅ የእናንተው ፋንታ ነው ስለተባሉ የተሰጣቸውን ድንበር ለመጠበቅ እንደገቡ ነው የሚገልጹት፡፡ ኮር ሑመር አካባቢ በትብብር ደንበር ሲደነብሩ እንደዋሉም መረጃዎቼ ገልጸውልኛል፡፡

4. ከሰሞኑ በተለየ ሁኔታ በታችና ምዕራብ አርማጭሆ እንዲሁም ጠገዴ አካባቢዎች ሕገ ወጥ በሚል የመሣሪያና ጥይት መግፈፍ በደንብ ተጠናክሯል፡፡

5. ጠቅለል ስናደርገው የሱዳን ወታደሮች የገቡት በወያኔዎች መልካም ፈቃድ እንጅ በራሳቸው ፍላጎት አይመስልም፡፡ የታጠቁ የአገዛዙ ወታደሮች ወደ አርማጭሆና ቋራ በብዛት እየሔዱ ቢሆንም የመከላከል ሳይሆን የማገዝ ሥራ እያከናወኑ እንደሆነ ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት፡፡ ስለሆነም ከዚህ በፊት የተሰጠውን መሬት አጠቃሎ የማስከበር ዓይነት ነው፡፡

No widget added yet.

← Stop the Enslavement of Black Africans in Libya ጄኔራል ተሾመ ተሰማ ያቺን ሰአት> አገር ስትከፋፈል ማየት ጠልቶ የአፄውን ሞት በራሱ ሽጉጥ ደገመው!! →

Leave A Reply

Comments are closed

Visit Us On TwitterVisit Us On FacebookVisit Us On YoutubeVisit Us On Linkedin