eet

Pin
Email
Share

ፕሮፌሰር መስፍን በአንድ ወቅት እዚህ አዲስ አበባ ባለው በስዊዝ ኤምባሲ ተባባሪነት ስለ ኢትዮጵያዊነት አንዲት አጭር መድብል አሳተመው ነበር። ማንም ጤነኛ አይምሮ ላለው ሰው መጽሃፏ ፖለቲካዊ አጀንዳ አላት ብሎ መደምደም የሚቻልው አይመስለኝም። ስለ አገር ፍቅር ልክፍት ስለተከፈለው ዋጋ ወዘተ የምታትት እና መጸሃፏ በታተመችበት ወቅት ኢትዮጵያዊት ፈተና የሆነባቸውና ባንዲራችንን በሶ ሲቋጥሩበት የኖሩት ጭንጋፎች ከነተባያቸው የሚኒሊክ አልጋ ላይ የወጡበት ወቅት በመሆኑ ዛሬ የምናየው አደጋ ፕሮፌሰሩ ጥላውን አስቀድመው ስላዩት ነበረ፤
“ኢትዮጵያዊነት ለእየሱስ ክርስቶስ ለሙሴና ለመሃመድ የሚጨሰው እጣን በ አንድ ላይ መጥቆ የሚደባለቅበት እምነት ነው፤
ኢትዮጵያዊነት በቄጠማ ጉዝጔዝ ላይ የምናየው ፍቅርና መተሳሰብ ነው፤
ኢትዮጵያዊነት ኩራትና ክብር ጥቃትና ውርደትም ነው..” ወዘተ የሚሉት አገላለጦች ዛሬ አገር ማለት ምን ማለት እንደሆነ ትርጉሙ ጠፍቷቸው ቆላ ደጋ ለሚረግጡት መሳጢ ተኩላ ሁሉ እንዲህ አምሮ ተቀምጦላቸው ነበር፤ መጽሃፉ እንደሚለው እሱራን ግኡዛን ናቸውና ለማየት አልታደሉም እንጅ።

ይህም በመሆኑ አፉ ላይ የሰለጠነው ዜናዊ የተባለ የደደቢት ፑሮፌሶር የስዊዘርላንዱ አምባሳደሩ ላይ ቢያንባርቅበት አገሪቱን በደደቢቶቹ ዘለፈቶዎች ጫማ የለካው አምባሳደር ፕሮፌሰር መስፍንን ያስጠራና “እኛ ገንዘብ የረዳነው የራስዎን የፖለቲካ አላማ እንዲያራምዱበት አልነበረም..” ብሎ ሊዘልፋቸው ይሞክራል። አንዲት ትናንት የተፈጠረች፣ አጼው እንዳሉት “ለስሟ መጻፊያ ቦታ የለላት” ፤ ትናንት በኦሽዊትዝ ቡከን ወልድና በንቻዲዝን ከመሳሰሉ የናዚ የሰው ቄራዎች የሚሊዮኖች አይሁዳውያንን ንብረትና የወርቅ ጥርስ ሳይቀር በጉጥ እየተነቀለና ከደሃ አገር እየተዘረፈ ባባንኳ ውስጥ በሚከማች ገንዘብ የደለበች አገር ዜጋ እራሱን ከፍ ያለ ማማ ላይ ሰቅሎ ፕሮፌሰሩን አዘቅዝቆ ለማየት የሞከረበት ኩነት ነበር። ሰውየው የዋዛ አልነበሩምና ውለው ሳይድሩ ጥቂት አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያንን በኢሰመጉ ቢሮ ውስጥ ሰብስበው በስዊዝ ኤምባሲ ውስጥ የሆነውን ነገር በቁጭት አስረዱ። ነገር ግን በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ከተሰብሳቢዎች አንዱ ስመጥር ኢትዮጵያዊ የስዊዝ መንግስት መጽሃፉዋን ለማሳተም እረዳ የተባለውን የአስር ሽህ ዶላር ቸክ እዚያው ቆርጠው በመስጠታቸው ፕሮፌሰሩ እለቱን ወደ ኢኤምባሲው ተመልሰው በመሄድ “ስማ !ከነገንዘብህ ገደል ግባ እንጅ አንተ ለኛ ምን መጻፍ እንዳለብን ልታስተምረን አትችልም። ያንተ አስር ሽህ ዶላር እኛ ላይ አፍህን ለመክፈት ንግድ ፈቃድ አይደለም። ደሃ ብንሆንም ብሄራዊ ኩራት ያለን ለመሆናችን ታውቅ ዘንድ ትንሽ የታሪክ መዛግብትን ብታገላብጥ ከእንዲህ ያለ ነውር ይታደግሃል..” ብለው እስከ ዶቃ ማሰሪያው ነግረውት ቸኩን አስቀምጠውለት የወጡበትን አጋጣሚ ባንድ ወቅት በጽሁፍ እንዳስነበቡን አስታውሳለሁ።

ይኽ ብዙ የተባለለትን ኢትዮጵያዊነት የትግራዮቹ ባንዶች ቀብረነው መጥተናል ባሉበት፣ ብሔር ብሔረሰቦች በሚል ድሪቶ ቃላት ተክተነው ጨርሰናል ብለው በደመደሙበት ሰአት እራሳቸው በመልካችን ቀጸብነዋል ባሉበት አዲሱ ትውልድ ላይ ሳይቀር እንደከሸፈባቸው እኮ ሩቅ ሳንሄድ ባንድ ወቅት የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስብ ቡድን በአቶ ሰውነት ቢሻው ተይዞ የ አፍሪካ ዋንጫ ተካፋይ መሆን በቻለበት ወቅት ፍንትው ብሎ የወጣበትና ምድረ የትግራይ ባንዲት ሁሉ ፍራሽ ዘርግተው የሚደማ ልብ ባይኖራቸውም ቅሉ ማቅ ለብሰው ሃዘን የተቀመጡበት ሁኔታ ነበር የነበረው። ብዙ ሰው ያላስተዋለው ግን አቶ ሰውነት ቢሻውን አውሎ ሳያሳድሩ ከቦታው በማባረር በቡድኑ የአቅም ግንባታ ትንሳኤ ላይ ውሃ ያፈሰሱበት ይሄው ከብሄራዊ ኩራታችን ጋር ያላቸው የመረረ ጥላቻ ነበር።ከዚያ ቦሃላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የብሔራዊ ማንነታችን መገለጫ መሆኑ ቀርቶ እራሱም የት እንዳለ ፈጣሪ ይወቀው።

 ዛሬም እንደ ትናንቱ በየከተማው ያሉት የእግር ኳስ እስታዲዮሞቻችን የክለብ ጨዋታዎችን ሽፋን አድርገው ኢትዮጵያዊ ማንነታችንም ሆነ የአባቶቻችን የተጋድሎ ታሪክ የሚዘመርባቸው የሚዘከርባቸው የኩራት ማማዎቻች፤ የጋር መታገያ አጀንዳዎችችን የሚንጸባረቅባቸውና ፈቃድ የማይጠየቅባቸው ጸረ ወያኔ መድረኮቻችን እየሆኑ ነው።። ሰሞኑን ከባህርዳር እስከወልዲያ ከወልዲያ እስከ ደሴ የሆነውም ይኸውም ነው።ስለሆነም ይኽ መጭውን ዘመን ፍንትው አድርጎ ያሳየን ክሰተት በከፍተኛ ብልሃትና ጥበብ ሊያዝ ይገባዋል።ምክንያቱም ባሳለፍነው ወራት የኦሮሞ ልጆች “ጣና ኬኛ! ” ብለው ወደ ባህር ዳር ባቀኑ ማግስት የደነበሩት የትግራይ ባንዶች ውለው ሳያድሩ በኤሊባቡር የፈጸሙትን አሽዊትዛዊ ተግባር ላየን ሰዎች ዛሬም ደግሞ በየእግር ኳስ ሜዳው ላይ እየታየ ያለውን ጸረ ወያኔ ትግልና ለግማሽ ምእተ አመት ሲገነቡት የኖሩትን የዘረኝነት ስነኦር መደርመሱን ጭንጋፎቹ እንዲህ ዝም ብለው ያዩታል ብሎ ማሰብ አይቻልም። ይልቁንም በህዝባችን መካከል ያለውን የአብሮነት ድርና ማግ ለመበጣጠስ ከአብሮነታችን ባሻገር ሰብአዊነታችንን ሳይቀር የሚፈትኑ እንዲህ በቀላሉ ተነቅለው የማይጨረሱ የጅምላ ግድያን ጨምሮ ብዙ የመርዝ ሰንኮፋ እየተከሉ እንደሚሄዱ አስቀድሞ በማሰብ በማስተዋል መራመድ ይገባናል።