December 7, 2017 06:24

ከኣስገደ ገብረስላሴ ፣
————————————————————
1 በሃገራችን በተለያዩ መድረኮች በተለያዩ ጊዚያት እች ኣገር ነጻነታን ፣ኣንድነቷን፣ ጠብቃ የመኖር እሴቷን ወደ ኣደገኛ ኣቅጣጫ እዬሄደች ቆይቷለች። ኣሁንም በበለጠ እና በተፋጠነ መንገድ አደገኛ ወደ ሆነው መንገድ እየሄደች እንመለከታለን ፤
እነዚህ የሚከሰቱትን ክስቶቶች ከመቸ ዘመን ጀመሩ ፣በምንስ ምክንያት ተከሰቱ ። የተከሰቱስ ችግሮች መነሻቸው ምን ነበር ? ኣሁንስ ይህ ትውልድ ምን ኣይነት ክስተት ይጠብቀዋል ?
እስቲ የኣሁና የገራችን መጻኢ እድል ከመተንበይ በፊት ከ50 ኣመት በፊት ወደ ኃላ ተመለሰን እስከኣሁን የነበሩ ክስተቶች፣ የስርኣቶች ኣወዳደቅ ውጤታቸው እንመልከት ።
በሀገራችን ለኣስታት 40 ኣመታት የገዛን የረዘመ ዘመን ( ጊዜ ) የሚባልለት የዘውዳዊ ስርኣት ኣገዛዝ ነበር ። ያ ስርኣት የመጣበት መንገድ በዘመኑ በነበሩ የመሳፍንት የስርኣት ለውጥ ህግጋት መሰረት ተከትሎ የመጣ እንደነበር ታሪካቸው ይነግረናል ።
ሰርኣታቸው ግን ለረጅም ኣመታት ሲገዙን ግን ሃገራችንና ህዝቦቻ የሚሸከም የማህበረ ኢኮኖሚ እድገት በዘመኑ ወደ ነበሩ የበለጸጉ ወይ የዘመኑ ስርኣቶችና የሳይንስና ቴክኖሎጂ
እድገት ኣምጥቶ ለመምራት ተሳነው ። እንዳውም ሀገራችን ወደ በለጸጉ ኣገሮች ተከትላ እንደመጓዝ ፈንታ በኣንጻሩ ወደ ኃላ እንደ የጊመል ሽንት ተመልሳ ጸረ ሳይንስ የሆኑ ፣ግጭቶች እንደ የዘር ፣ የእምነት የክልል ፣የቢሄር ፣ የጎጥ ፣የቀለም ፣የኢኮኖሚ ክፍፍል ኣድላውነት ወ ዘ ተ እየሰፉ ግጭቶች እየተስፋፉ መጡ ።ስርኣቱም ይባስብሎ የኣንድ እምነት ኦርቶዶክስ የበላይነትና የኣንድ ቢሄር የበላይነት ኣምላኪ ሆነ ።
በሌላ በኩልም በዘመኑ ለነበሩ ወጣት ትወልድ የበለጸጉ ሃገሮች የትምህርት ፣የሳይንስና የቴክኖሎጂ ፣ የባህል ግብኣት ። የመሳፍንቶች እና የዘውዳዊ ስርኣት ኣጥር ሰብሮ ወደ ኣገራችን በማጥለቀለቁ ። ዘውዳዊ ስርኣትም ሳይወድ በግድ በመግባት ትምህርት ኣሰፋፍቶ እጅግ ቡዙ ዜጎች ተምረው የኣለማችን የእኮኖሚና የማህበራዊ የስርኣቶች ለውጥ በመገንዘባቸው የስርኣት ለውጥ እንደእሚያስፈልግ መገንዘብ የግድ ይላቸው ነበር ። ለዘውዳዊው ስርኣትም መ ጥፈነቱ ኣቀው መጋለጥ ፣መታገል በማድረግ ኣስጨነቁት ማመጽም ጀመሩት ።
ከዛ በኃላ ዘውዳዊ ስርኣት ደከመ መራመድ ኣቃተው የሰብኣዊና ዲምክራሲያዊ መብቶች ጥያቄዎች ኣንስተው መልስ ባለማግኜታቸው በየኣቅጣጫው ለኣመጽ ተነሱ ። ለኣመጽ እንኳን ተነስተው ቢኖሩም ለለውጥ ቡቁና የተዘጋጀ ፖለቲካዊ ኣደረጃጀት ኣልነበራቸውም ። ቡዙ የተቃውሞ ኣድማዎች ተነሱ በመጨረሻ የዘውዳዊ ስርኣት ቅልብ ቅጥረኛ የነበረ ወታደር መካከለኛ የስልጣን መኣርግ የነበራቸው ወጣት የወታደር መኮኖኖች የሙሁራን ፣የተማሪዎች ፣የወዝ ኣደሮች ፣የኣርሶ ኣደሮች ጥያቄዎች ኣንግቦው ፣ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ይዘው የዜጎች ደም መጠጣት ጀመሩ ። ወታደራዊ ኣዋጆች ኣወጁ ፣የሃገራችን ሃብት በቁጥጥራቸው ወደቀ ። ህዝብ ወደስደት ፈለሰ ። ተራበ ፣በድርቅ ሞተ ። የሀገራችን ኣንጡራ ሃብት ተማጥጦ ወደ ጦር ኣውድማ ፈሰሰ ።
ከዛም በዘውዳዊው ስርኣት የነበሩ ኣፈናዎች ምክንያት ህዝብ መሮት ስለነበር ኣመጹን ፈርቶ ተገዶ ይሰጣቸው የነበረ መብቶች በሙሉ ተዘግተው በሀገራችን ኣንባ ገነን ወታደራዊ ኣገዛዝ ፋሽዥም ሙሉ በሙሉ ኣቆጥቁጦ እጅግን ኣደገኛ የሆነ ፋሽሽታዊ ስርኣት የበላይነት ቦታ ያዘ ። በወቅቱ የነበሩ ሙሁራን ፣ ተማሪዎች በተለይ ደግሞ የነበሩ ከፍተኛ ሙሁራን ፣ እንደዛሬው ያሉ ሙሁራንና ተማሪዎች ፣ ሃገራቸው እየተወረረች በሩቅ ሆነው የበይ ተመልካች ኣልነበሩም ። እነሱ የነበራቸው ደካማ ጎን ግን ጸረ ዘውዳዊው ስርኣት ይሁን የደርግ ስርኣት ትግል ሲያደርጉ ለኣንድነት ፣ለእኩልነት ፣ለቢሄር መብቶች አጠባበቅ የሚሰጡት የነበረ ግምት የወረደ ከመሆኑም በላይ በሚያደርጉት የነበረ ትግል በኣንድ ሆነው እንደመታገል ፈንታ በተናጠል በመደራጀት ኣይንቀሳቀሱም ነበር ።በተጨማሪ እርስበእርሳቸው በመናናቅ በመጣላት በመበታተናቸው ስርኣቶች ነጣጥለው በመምታት ለኣብዛኞቹ ኣከሰሙዋቸው ። ጥቂቶቹ ደግሞ ለወታደራዊው ስርኣት በሁሉም ኣቅጣጫ ነፍጥ ኣንስተው መራራ ፍልምያ በማድረግ ወታደራዊው ደርግ በማስጨነቃቸው ወታደራዊ ስርኣትም ፋሽሽታዊው ተፈጥሮው ኣስገድዶት በመላው ሀገራችን ግድያ ንብረት ማውደም ፣ወጣቶች በግድ እያፈሰ ወደ ጦርነት ማገዳቸው ። በመጨረሻውም ደርግ በጦርነት ተሸንፎ ወደቀ ።
ከደርግ ወድቀት በኃላ የህወሓት የበረሃ ደፈጣ ተዋጊ ወታደር ኣገሪቱ ተቆጣጥሮ የስቢል ኣስተዳደሩ ስልጣን መዋቅር ጭምር በበረሃ ወታደር ተዘርግቶ ያዘው ።
ህወሓት ኢህኣደግ ስልጣን ይዞ ከተቆጣጠረ በኃላ ልክ ወታደራዊ ደርግ መጀመርያ ኢትየጱያ ትቅደም ያለምንም ደም በማለት ለኢትዮጱያ ህዝብ እንደሸወደው ሁሉ ፣ የህወሓት መሪዎችም ጸረዲሞክራሲ ባህሪያቸው ደብቀው ሁሉም ፖርቲዎች የተሳተፉበት ህገመንግስት በህዝብ ሪፍረንደም ኣጸድቀን በህዝብ የተመረጠ ዲሞክራሲያዊ ህዝባዊ መንግስት እንመሰርታለን ከእንግዲህ ወዲህ በዝህች ኣገር የደፈጣ ውግያ የጥይት ድምጽ ኣይሰማም በማለት በሁሉም ሚዲያዎች ኣወጁ ።
ህገመንግስቱ ተጸጋግኖ ጸደቀ ። ነገር ግን ህገመንግስቱ ሲጸድቅ ህወሓት ኢህኣደግ በገባው ቃል ሳይሆን የጸደቀው ህገመንግስት በማጽደቁ ጊዜ ለህወሓትና ለባኣዴን መሪዎች ደስ ያላሉዋቸው ኣንጋፋ ደፈጣ ተዋጊዎች ከህወሓት መሪዎች ከነበራቸው ቂም በቀል የመነጨ በማጸደቁ እንዳይሳተፉ ተደርገው ጦርነት ኣውጆው ኣጠፉዋቸው ከዛ በኃላ ጸረ ህወሓት ኢህኣደግ ቡዙ የደፈጣ ተዋጊ እና ቡዙ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ፓርቲዎች ተፈጠሩ ።
ቀጥሎ የህወሃን በኣዴን ቡዱኖች ስርኣት ለይምሰል በስመ ዲሞክራሲ ስርኣት ስልጣኑ እያጠናከረ ቀጠለ ። ቀስበቀስ ግን ተደብቆ የቆዬ ጸረዲሞክራሲ ጎሬላ ባህሪኡ እዬተጋለጠ መጣ ። መጀመሪያ ኣውጆት የነበረ ፣በነጻ የመደራጀት መብት፣ የመሰብሰብ ፣ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ፣ የፕሬስ ነጻነት ፣ የነጻ የፓርቲዎች የምርጫ ውድድር ፣ ያገር ውስጥና የውጭ የምርጫ ታዛቢዎች ወዘተ ይሳተፉ የሚለው የነበረ ዘጉት ። የምርጫ ኮሮጆዎች ዘረፉዋቸው ፣ የፓርቲ መሪዎችና ኣባሎቻቸው ፣ ጋዜጦኞች ታሰሩ ተገረፉ ተሳቀዩ ፣ የሞቱም ቡዙናቸው ።
የሀገራችን ኢኮኖሚ ደቀቀ ፣ሙሱና ምዝበራ ተሰፋፋ ፣ ስራ ኣጥነት ተስፋፋ ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ተሰደዱ ። የሀገራችን ሃብት ገዥዎችና ልጆቻቸው ብቻ ልዩ ፍጡራን ሆነው የሚቀማጠሉባት ፣100 ሚሊዮን ህዝቦቻ ሁለተኛ ዜጋ ሆነው የሚቷዩባት ኣገር ሆነች ። በኣጠቃላይ ኣገራችን በዘውዳዊው ስርኣት እና በደርግ ወድቀት ዋዜማ የነበረ የኢኮኖሚ ውድቀት ታዬ ።እታየም ይገኛል። ኣሁን ደግሞ ሃገሪቱ ከደኸዩ ኣገሮች በታች ከመሆናም በላይ በኣሁኑ ጊዜ ከኤርትራ እና ከሱማል ፣ከደቡብ ሱዳን ጋር እኩል ትሰላፋለች ።
ኣገራችን በቢሄር ፣ በዘር ፣በሃይማኖት ፣በጎጥ በኣካባቢነት እየተከፋፈለች የጦርነት ፣የሞት የመተላለቅ ኣውድማ ሆናለች ።
2 ኣሁን ባለው የሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ
ምን ኣደጋ ሊከሰት ይችላል ፤
—————————————————–
ከላይ እንደተቀመጠው ኣንድ ስርኣት ኣርጅቶ ሲበሰብ ኣወዳደቁ እንዴት እንደሚሆን ወደ ሩቅ ሳንሄድ የዘውዳዊው እና የደርግ ስርኣቶች በስብሰው እንዴት እንደወደቁ ተመልክተናል ።
እንግዲህ የነዚህ ኣፋኞችና ዲክታቶሮች ኣወዳደቅ ይህ ከሆነ ፣የህወሓት ኢህኣደግ ኣዋደደቀም እንደዚሁ ኣንደኛ ወደ ስልጣን ኣወጣጡ በበረኸኛ ኣስተሳሰብ የተነከረ በታጠቀ የበረሃ ወታደር በሃይል ስልጣን የጨበጠ ነው ። ሁለተኛ ከጅምሩ የደርግ የመሰረታዊ ድርጅት ኮሚኒስት ሀይል የኣስተዳደር መዋቅርና በወቀቱ የነበረ ስቢል የቢሮክራሲ መዋቅር ነቃቅሎ ጥሎ ፣ምንም የኣስተዳደር እና የስቢል ኣመራር ሳይንስ የማያውቅ በረኸኛ በጦሮኝነት ትምክህት ልቡ ያበጠ የኣስተዳደር መዋቅር ከቤተ መንግስት እስከ ቀበሌ ተዘርግቶ ስልጣኑ ተቆጣጠረው ። በቃ ኣገሪቱ ባልታወጀ ወታደራዊ ኣስተዳደር ወደቀች ። የኢትዮጱያ ህዝቦች
ከደርግ ስርኣት ተላቀቅን ብለው ተደስተው ነሮው ቡዙ ከቁስላቸው ሳያጋግሙ ፣ወይ ሳይራመዱ በጦርነት የደነዘዘ በበረኸኛ ኣስተሳሰብ የሰለጠነ ወታደራዊ ዲክታተራዊ ስርኣት እጅ ወደቁ ።
ይህ ስርኣት ለይምሰል ህገመንግስት በተራቀቀ ተንኮል የተመረዘ አጸደቀ ። ሃገሪቱ በህዝብ የተመረጠ ህዝባዊ መንግስት እንመሰርታለን በሚል ሽፋን ከቀበሌ እስከ ፈደራል ፓርላማ በህወሓት ኢህኣደግ ካድሬዎች የሚመራ ምክርቤት የኣስተዳደር መዋቅር በስለላ የተጠላለፈ ተዘረጋ ። ስቢል ማህበረሰብ ንቁ ናቸው ለስልጣኔ ኣስጊ ናቸው የሚሏቸው ሙሁራን ኣገለሉዋቸው ራሳቸወና ቤተሰቦቻቸው ተፈናቀሉ።ለስደት ተዳረጉ። ሌላው የተማረ ማህበረሰብ ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ ሳይወድ በግድ ኣገልጋይ ሆነ ። ወጣቶች ህጻናት በውሼት መዝሙር ደነዘዙ ።
በሃገሪቱ ማንም ዲክታቶሪያል ገዥዎች በስልጣን ለመቆየት ወይ የስልጣናቸው እድሜ ለመራዘም ሲሉ እንደሚሰሩት ሁሉ መሰረተልማት በሃገራችን ተገደው የሰሩት መሰረተልማትተስፋፋ ።
ህዝቡ በነዚህ ሳይንሳዊ ጥናትና ብስለት በሌለበት የተሰሩ መሰረተ ልልማቶች በውሼት ኣንሳፈፉት።በንሮው ግን ለውጥ ኣላመጡም። ለኣለም ማህብረሰብ መንግስታትም በሙሉ ኣዳናገሩበት ።በኣንጻሩ ግን ህዝብ ደኸዬ ፣ያልተመጣጠነ ኖሮ ሰፋ ።የሀገራችን ሀብት በህወሓትና ህወሓት ራሱን ኣስመስሎ በሰራቸው ተቀጥያ ፓርቲዎች እጅ ወደቀ ። ከቀበሌ እስከ ቤተመንግስት የተዘረጋ ባለስልጣን የሃገራችን ሀብት በሙሱና መዘበረው ። እች ኣገር የልጆቻቸው ፣የዘመድ ኣዝማዳቸው ፣ የስርቅ ሸሪኮቻቸው መናጠጫ ወይ የሚቃማጠሉባት ኣገር ሆነች ።
ሀገሪቱ በተሳሳተ የፈደራሊዝም ኣወቃቀር ከፋፍለው ሆን ብለው ዜጎች በተራ የወሰን ግጭት እረስበእርሳቸው እንዲተላለቁ በማድረግ ዜጎች ድሮ ባለፉት ኣፋይኝ የነበሩ ስርኣቶች እንኳን በመላው የሀገራችን ክልሎች ዘረው ሰርተው የሚኖርባት ቤተሰብ የሚመሰሩቱባት ፣የሚነግዱባት ፣የሚማሩባት የነበረች ፣ዛሬ ይቅርና ሊኖርባት ቤተሰብ ሊመሰረትባ በጎደና ሲያልፍም የሚገደልባት ፣ለዜጎቻ ሲኦል ሀገር ሆና ኣለች ።
የኣሁኑ ሃገራችን ዜጎቻ የተለዬ ሃሳብ ፣ይዘው የማይኖርባት ፣የተማረ ሃይልሰው በኣጠቃላይ የህዝባችን 75 % የሆነው ወጣት ስራ ኣጥ ሆኖ በጎዳና የወደቀባት ወጣት ትወልድ በሁሉም የሃገራችን ኣቅጣጫ ተሰዶ በሳሃራና በባህር የሚያልቅባት ለዜጎቻ ንሮ ሲኦል ሆና ኣለች ።
ባገር ውስጥ ያሉ ዜጎች ዲሞክራሲያዊ ጥያቄ ሲያነሱ ኣሸባሪ ፣ዘረኛ ፣ የእገሌ ፓርቲ ነህ በግለጽም የኦነግ ፣የጉንበት ሰባት እየተባሉ ቡዙ ዜጎች በጥይት ተቀልተዋል እየተቆሉም ይገኛሉ ።በዚሁ መክንያት ወታደራዊ ኣገዛዝ ብቅ ጥልቅ እያለ ቆይታል ። መጨረሻውስ ?
3 ከላይ ከተዘረሰሩት የሃገራችን ችግሮች
ወዴት ኣቅጣጫ እየወሰዱን ነው ?
———————————————-
የህወሓት ኢህኣደግ ስርኣት እንደ ያለፉት ስርኣቶች ኣርጅቶ በስብሶና ላሽቆ ልክ በታሪክና በኣይናችን እና በእድሚያችን ያዬነው የፋሽሽታዊው ደርግ ኣወዳደቅ የሚያሳዩት ምልክቶች ኣይነት ዘልበድበድ እያለ፣ ኣንድ ያዝ ኣንዱ ለቀቅ ጀምሮ ግርጭቶች መፍታት ኣቅቶት የኣገሪቱ ኢኮኖሚ ኣሽቆልቁሎ የዶላር ምንዛሪ መውደቅ ፣የሸቀጦች ዋጋ መናር እንዲሁም ማጣት ፣የኑሮ ወድነት ሰማይ መሰቀል ፣ሊመልሳቸው የሚይችል የህዝብ ጥያቄዎች ከቁጥጥሩ ወጭ መሆን ፣ በሁሉም የሀገሪቱ ከልሎች የተቃውሞ ፈንጅ ተቀብሮበት በኣንድ ክርቢት ለመቀጣጠል የቀረችበት ፣ ፍጹም መራመድ እየተሳነው ከ100 ሚሊየን ህዝቦች ፣ ከስርኣቱ ሳራተኞች እና ከዝቅተኛ ወታደሮች ፣ከፓርት ኣባላቱ መፍረስና መክዳት ለዚሁ ፈጽሞ ሊፈርሱ የማይገ መቱ ከህወሓት ኣባላት ብቻ ወደ ሁለት ሚሊዮን ኣባላት ፓርቲ የፈረሱ መሆናቸው ምንያህል ከሁሉም እንደተነጠለ ያሳያል ። ፣ የሃገራችን ሃብት የወረሩ ስቢል ሌቦች ፣ሙሶኞች ፣ሃብት የደለቡ የመንግስት ባለስልጣኖች እና የፓርት መሪዎች ፣ጥቂት መካከለኞ እና ከፍተኛ የጦርና ፣የፖለስ መኮኖኖች ነባር የድህንነት ቡዱኖች ይዞ መቆም ኣቅቶት ነቅነቅ እያለ በመስቀልኛ መንገድ ቆሞ ወደሞት መቃብር ጉድጓድ ወይ ወደ የለዬለት ፋሽሽታዊ ጭፍጨፋ ለመጓዝ ሙሉ ዝግጅት ኣድርጎ ይገኛል።
ወደ ወታደራዊ ፋሽሽታዊ ኣገዛዝ መንገድ ሊሄድ ይችላል ያልኩበት ምክንያት ፣
1 የህወሓት ኢህኣደግ ስርኣት አመሰራረት
አመጣጡ ከደፈጣ ውግያ የተነሳ ስልጠናው
ኣስተሳሰቡ ወታደር መኖሩና ከደርግ ወታደራዊ ስርኣት ልዩነቱ ደፈጣ ተዋጊው ከበረሃ መፈጠሩእና በደሞዝ ኣለመኖሩ ፣ የደርግ በለደሞዝ መኖራቸው በከተማ መፈጠሩ ነው ። በተረፈ ሁለቱ ገዳዮች ኣሳሪዎች ኣሳቃዮች መኖራቸው ።
2 የደርግ ስርኣት ከተቆጣጠረ የደፈጣ ለብስ በሱፍና ካራባታ ቀይሮ ስልጣን ከላይ እስከ ታች በሞኖፓል ይዞ ሃገራችን ለ26 ኣመት በወታደራዊ የሰለጠነ በረኸኛ ኣስተሳሰብ ጨፍጥጦ የገዛ ነው።
3 በደፈጣ ተዋጊ የተቋቋመው 100% በህወሓት ኢህኣደግ የፓርላም ኣባል በተነገረው የተባለው የፈደራልና የክልሎች ፓርለማ ስለሚወሰን ነው ።
4 ደግሞ ባለፉት ኣመታት በኦሮሞና በጎንደር ግጭቶች ምክንያት ወታደራዊ ኣስተዳደር ታውጆ ቡዙ ኣሰቃቂ እርምጃ መወሰዱ
5 አሁን ደግሞ ግልጽ የሆነ ለስሙ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ምኒስቴር የሆነው ከሃገር መከላከያ ፣ከፓሊስ ፣ከድህንነት የተሰባሰቡ የድህንነት እና ጠበቃ በሚል ሽፋን ወታደራዊ ኣስተዳደር ተቋቁሞ ታውጇል ። ይህ ራሱ ወደ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት የሚወስድ ነው ።
6 ኣሁን ደግሞ ከጭንቀት የመነጩ ሊሆኑ ነው የሚባሉ ከህወሓት ኢህኣደግ መንደር የሚናፈሱ መረጃዎች ይሰማሉ ።እነሱም የህወሓት ኢህኣደግ ኣንጋፋው ቡዱንና የጦር የፓሊስ የድህንነት ቡዱኖች የተሰባሰቡበትት የዙምባቤ ኣይነት የታወጀ መፈንቅለ መንግስት ኣድርገው እች ኣገር ዳግም ወደ ወታደራዊ ፋሽሽቲ ስርኣት እንዳያገባት የሁሉም ግምገማ ነው ።
እንግዲህ ይህ ኣደጋ ዝብለው በሩቅ ሃገራቸው ወደ ጨለማ ስትገባ የበይ ተመልካች እየሆኑ ያሉ ሙሁራን ፣ያገር ሽመግሌዎች ፖለቲኮኞች በጽሞና ቢመለከቱት እና ማስታገሻ ቢያደርጉሏቸው የተሻለ በሆነ ።
ከኣስገደ ገብረስላሴ ፣
መቀለ
29 / 03 /2010