Posted by | 11/12/2017

“… ከሰሜን እስከ ደቡብ ጫፍ፤ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ጥግ የተነሳው ጥያቄ የፍትህ፤ የዴሞክራሲ ገለመለ ጥያቄ አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ የሥርዓት ለውጥ ጥያቄ ነው፤ መንግሥት ይቀየር ጥያቄ ነው”
ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም ፡፡

ዶክተሩ ይህንን የተናገሩት ዛሬ ሰማያዊ ፓርቲ በአምባሳደር ሲኒማ አዳራሽ “ኢትዮጵያን እንታደግ” በሚል ርዕስ በሀገራችን አሉ! የተባሉ ምሁራን እንዲወያዩበት ባዘጋጀው መድረክ ላይ ነበር፡፡

እንደሚታወቀው ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ስብሰባ ከህብረተሰቡ ጋር የመጀመሪያውን ውይይት በተሳካ ሁኔታ አድርጓል፡፡ከትናንትናው ጋር ለ4 ተከታታይ ሳምንታት የተያዘ ፕሮግራም ነው፡፡ትናንት እሁድ በፕሮግራሙ መሰረት የተያዘው በሀገርም በውጭም ካሉ ምሁራን ጋር ነበር፡፡በጣም በርካታ ምሁራን የተጋበዙ ቢሆንም የተገኙት ግን ሁለት አንጋፋ የታወቁ ምሁራን ነበሩ፡፡በጥሪው ግን የተካተቱት በርካቶች እንደነበሩ አይተናል፡፡ከእነዚህም መካከል፡ፕ/ር መድሀኔ ታደሰ፡ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም፡ሜ/ር ጀኔራል አበበ ተሀይማኖት፡አቶ ክቡር ገና፡ወ/ት ሰሎሜ ታደሰ፡ደ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፡ወ/ሮ ሙሉ ሰለሞን፡ጋዜጠኛ መአዛ ብሩ፡ሙሼ ሸሙ፡አስራት ጣሴ፡ግርማ ሰይፉ፡ልደቱ አያሌው፡ከቀድሞው የደርግ አመራሮች አቶ ፍቅረስላሴ ወገደረስ፡ሻምበል ፍሰሀደስታ፡፡እኔ እንደ አንድ ታዛቢየምለው ነገር ምንድነው ፡ከተጠሩት ሰዎች አብዛኛዎቹ ለእኔ የማፍርባቸው ናቸው፡፡ሰማያዊ ፓርቲ ለምን ይሄን እንዳደረገ ግን እስካሁን እየጠየኩ ነው፡፡ምናልባት በምን አስበውት እንደሆነ አላውቅም ከእነዚህ ሰዎች ጋር ተወያይቶ መፍትሄ ላይ መድረስ ፡፡

ሌላው አሳዛኝም አስቂኝም ነገር ለዚሁ ዝግጅት ሲባል ፓርቲው ፈቃድ ካገኘ በኋላ ሰውን ለስብሰባው ሲቀሰቅሱ የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ተለቃቅመው በአሁኑ ሰዓት እስር ቤት መሆናቸው ነው፡፡በነገራችን ላይ ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በእስይፒ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ሲጠበቅ ፡የረባ የኢንተርኔ ፍጥነት ስለሌለ ልተሳካላቸውም፡፡