(ዘ-ሐበሻ) በተለያዩ ጊዜያት የወቅቱን የሃገሪቱን ሁኔታና የሕዝቡን ብሶት በማቀንቀን በሕዝብ ዘንድ ክብርን የተጎናጸፈው ድምጻዊ መሐሪ ደገፋው “አመመኝ” የተሰኘ ልብ የሚነካ ዘፈን ለቀቀ::

“እያያ በለው”፣ “ፋሲል ከነማ” ፣ “ጣና ኬኛ” የሚሉ ወቅታዊና የሕዝቡን ብሶት የሚያሰሙ ነጠላ ዜማዎችን ለቆ የነበረው መሐሪ ደገፋው ‘አመመኝ’ የሚለው ዜማው በሃገር ውስጥ ግፍና ግድያ እየደረሰባቸው ያሉ ወገኖቻችንን ጨምሮ በሊቢያና በስደት ሃገራት የሚደርስባቸውን በደል ይዘረዝራል:: ያድምጡት::