Pin
Email
Share

ልዩ ዕትም

በመቀሌና በአዲግራት ዩኒቨርስቲዎች የትግርኛ ተናጋሪ ባል ሆኑ በተለይም ደግሞ በአማራ ተወላ ጅ ተማሪዎች ላይ እየተወሰደ ያለውን ለመስማት የሚከብድ አሰቃቂ ግድያና ድብደባ በመስማታችን በሟቾች የፎቶግራፍ ማስረጃ ጭምር በማረጋገጣችን እጅግ ከፍተኛ ሐዘን ተስምቶናል። የ ሐዘናችን ጥልቀትም ለሞቱትና ለተደበደቡት፤ አካለ ጎደሎ ለሆኑት ተማሪዎች ብቻ አ ይ ደለም። ሐ ዘናችን ለትግራይ ሕዝብ የወደፊት እጣ ፈንታ ም ጭምር እንጂ ።

በኢትዮጵያዊነቱና በሐይማኖቱ ታማኛና ጽኑ ከሚባለው የትግራይ ሕዝብ ውስጥ ከአርባ ዓመት በፊት የተፈለፈለው አናሳ የወያኔ ቡድን ሥልጣን ከመያዙ ማግሥት ጀምሮ ኢትዮጵያ አገራችን ን በጎሳ ሸንሽኖ የዘረኝነት መርዝ እየጋተ ያሳደጋቸው የት ግራይ ወጣቶችና ተመሳሳይ የዘረኝነት ልክፍት የተጠናወታቸው አዋቂዎች ጭምር እጅግ ኋላ ቀር በሆነ ወገን ወገኑን የመብላት የእንሰሳት ባህሪና ተግባር ላይ ተነክረው በማየታችን፤ የሚያስከፍለውንም እጅግ ከባድ ዋጋ ም ከወዲሁ በማየታችን ኃዘናችንን እጥፍ ድርብ አድርጎታል ።

የ ትግራይ ሕዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ ጠ ረፍ እስከ ጠ ረ ፍ ድሮም ሆነ ዛሬ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ተከብሮ ኖ ሯል ። አሁን ግን በክልሉ ውስጥ እየተፈጸመ ላለው አረመኒያዊ ወንጀል ምንም አይነት ተቃውሞ አለማሰማቱ ለሚመጣው አጸፋ እራሱን እያጋለጠ ፤ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እየተቆራረጠ እንደሆነ ሊረዳው ይገባ ነበር። በችግርና በእርዛት ወልደው አሳድገው፤ በተሻለ የእውቀት ማእረግ ተመርቆ ያሳልፍልኛል ብለው በክልላችሁ ወደሚገኙት ዩኒቨርስቲዎች የላኳቸውን ለግላጋ ልጆች ገድላችሁ የወላድን ልብ በሚሰብር ሁኔታ ሬሳቸውን ስትልኩላቸው ከንፈር መጠው፤ እምባ አፍሰው አ ን ገት ደፍተው የሚያልፉት ተግባር አለመሆኑን

አልተረዳችሁም፤ ወይም ትዕቢታችሁ ጣራ ነክቷል። ኢትዮጵያውያን በዘመናት ፍልሰት አንዱ ወደ አንዱ አካባቢ እየ ተ ዘ ዋወረ የሰፈረ ወንድማማች፤ አንድ ባህሪ ወይም ወኔ ያለው ሕዝብ

በመሆኑ፤ ዛሬ ልጆቹ በግፍ የተገደሉበት ነገ ደሙን ከማን ላይ እንደሚመልስ ፤ እናንተም የምታጡት አይመስለንም። ምናልባት የወያኔን መንግሥት መከታ በማድረግ ከሆነ በጣም ተሳስታችኋል። የ ወያኔ ቀኑ እየመሸ ከ 11 ኛው ሰዓት ላይ ደርሷል። እንኳን የትግራይን ሕዝብ እራሱን ለማዳን አይችልም። ወያኔ እንደማንኛውም ዘመናቸውን ቆጥረው እንዳለፉ መንግሥታት ነገ ከነገ ወዲያ ይሄዳል ፤ የትግራይ ሕዝብ ግን ከሌላው ወገኑ ጋር ቀሪ ነው። ታ ዲያ ከዚያም ቤት እሳት አለ ብሎ አርቆ ማሰብ አለመቻሉ ከምን አንጻር ይሆን ?

ትግራይ ብዙ ምሁራንና ሽማግሌዎች ያሉ ባ ት ክ / ሀገር ናት። ይሁን እንጅ እየመጣ ያለውን አደጋ ቆም ብሎ አለማየት ለምን ይሆን ? የሌላን ጎሳ እንደጠላት ፈርጆ መነሳት ለአገራችንም ለሕዝባችንም ጥሮ እንዳልሆነ የትግራይ ሙሁራን ሊገነዝቡት በ ተ ገባ ነበር። በሩዋንዳና በሌሎች አገሮች የደረሰ ው የዘር ጥፋት በዚሁ ዓይነት መንግሥትን መከታ በማድረግ የተጀመረና የተፈጸመ አሰቃቂና በዓለም አስከፊ ምዕራፍን የያዘ ፍጅት ነው።

እንደሚባለው ወያኔ ዘላለማዊ ገዥ ሆኖ ይኖራል ብላችሁ አስባችሁ ከሆነ እጅግ የተሳሳተ ጎዳና እየተከተላችሁ ነው። እስከ አሁን ድረስ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔን ከትግራይ ሕዝብ ለይቶ ለማየት ሲታገል ቆይቶ ነበር። አሁን ግን ይህን ተስፋውን በልጆቹ ደም አ ቅል ማ ችሁ አጨለማችሁት !! ልቡንም አደማችሁት ! የኢትዮጵያ ሕዝብ ይጠብቅ የነበረውን የተቃውሞ

ድጋፍ ከወያኔ ጎን እንደቆማችሁ በሚያረጋግጥ መልኩ ከአብ ራኩ የ ወጡትን በእምነት ወገኖቸ ብሎ በክልላችሁ እንዲማሩ በአደራ የላከላቸሁን ልጆቹን በላችሁበት።

አሁንም እየሞላ ያለው የእዳው መስፈሪያ ሞልቶ ከመፍሰሱ በፊት ዘርን መሰረት ያደረገ ግድያ፤ ጥላቻ እንዲቆም እና የ ሕ ዝብ አመኔታ እን ድ ታገኙ ወደ ድሮው ክቡር ወደሆነው ኢትዮጵያዊነት

ፍቅራችሁ ትመለሱ ዘንድ የጎንደር ሕብረት ጥሪውን ያ ስተላልፋል ። ቢያንስ በክልላችሁ ውስጥ እየተፈጸመ ያለውን ግድያና ድብደ ባ አስ ቁ ሙ ፤ እናንተም ከጥፋት ትብብር ታቀቡ ። በሰላም

ትምህርት ለመቅሰ ም ከተለያዩ የአገራችን አካባቢዎች የመጡ ተማ ሪዎ ችን ከነ ህ ይወታቸው ወደመጡበት እንዲመለሱ ተባበሩ። ወላጆች ልጆቻችሁን ስላማዊና ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር አብሮ ለመኖር ዝግጁ እንዲሆኑ ም ከ ሩ።

በአጠቃላይ በወያኔ የዘር ፖለቲካ ምክንያት እየመጣ ያለውን አሰፈሪ ሁኔት በመገንዝብ ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት ፤ የኢትዮጵያ ልእዋላዊነት፤ የሕዝባችን ሰላም እና አንድነት የሚያሳስባችሁ ወገኖች ስብስቦችና የፖለቲካ ድርጅቶች ከመቸውም በላይ ልዩነትን ወደ ጎን በመተው በጋራ በመቆም ከወያኔ የጥፋት ጎንዳና ሕዝባችንና አገራችን እንታደግ ዘንድ የዘወትር ጥሪውን ያቀርባል።

በትግራም ሆነ በሌላ አካባቢ በዘር ምክንያት ህ ይዎታቸው ላለፈ ቤተሰቦች መጽናናትን እንመኛለን !

ኢትዮጵያን ከጎሳ ፍጅት እናድናት !!!

ጎንደር ሕብረ ት ለኢትዮጵያ አንድነት

12/12/17