መቀመጫውን አዲስ አበባ ያደረገው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተስተዋለ የሚገኘው ግጭት እንዳሳሰበው አስታወቀ” ኤምባሲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ላይ፣ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተከስቶ ህይወት በቀጠፈው ግጭት ማዘኑን ገልጾ፣ በግጭቱ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ሰዎች መጽናናትን ተመኝቷል” የኤምባሲው መግለጫ አክሎም፣ መሰል ሁኔታዎች በውይይት እና በንግግር እንዲፈቱ ጠይቋል” መቀመጫውን በአዲስ አበባ ያደረገው የአሜሪካ ኤምባሲ፣ በጨለንቆ በተፈጸመው ጥቃት ማዘኑን ባወጣው መግለጫ ላይ የገለጸ ሲሆን፣ ተጠያቂ መደረግ ያለባቸው አካላትም ተጠያቂ እንዲሆኑ የኤምባሲው መግለጫ ያሳስባል” የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አንድ የኦሮሞ ተወላጅ መግደሉን ተከትሎ በጨለንቆ በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞ ላይ የተሳተፉ ንጹኃን ሰዎች በመከላከያ ሰራዊት አባላት መገደላቸው ይታወቃል” መከላከያ በፈጸመው በዚሁ ጥቃትም፣ ከአንድ ቤተሰብ አራት ሰዎች መገደላቸውን ጨምሮ፣ በአጠቃላይ በአስራ ስምንት ሰዎች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ መወሰዱ አይዘነጋም” በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ፣ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የተከሰቱ ተመሳሳይ ሁኔታዎችን ተከትሎ፣ መግለጫ ሲያወጣ መቆየቱ ይታወቃል” ከዚህ ቀደም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ተከስቶ በነበረው ህዝባዊ ተቃውሞ ላይ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹኃን ዜጎች መገደላቸው አይዘነጋም” ኤምባሲው ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫ ላይ፣ ንጹኃንን በመግደል እና በማስገደል ሂደት ላይ ተሳታፊ የነበሩ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ ጠይቋል” ሌሎች ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ተቋማት ደግሞ፣ በሁለቱ ክልሎች የተከሰተውን ተቃውሞ ተከትሎ የተፈጸመው ጥቃት በገለልተኛ አካላት አንዲጣራ ጠይቀው መንግስት አሻፈረኝ ማለቱ ይታወሳል”

BBN NEWS