December 13, 2017 23:04

በርዕሴ ያስቀመጥኩትን የወሰድኩት አንድ ምሁር በኦሮሚያ ሚዲያ ኔት ወርክ ቀርበው ሲናገሩ ስለኦሮሞ ሕዝብ የሰጡትን ምሳሌ ነው፡፡ በጣም ገላጭ ምሳሌ ነው፡፡ ኦሮሞ ገዥ እንጂ ተገዥ አልነበረም፡፡ ተገዥ ነበርክ ሲሉት መቀበል ሲጀምር እየከሳ መጣ፡፡  ስለኦሮሞ እኛን ነው የሚመለከተው ብለው ኦሮሞን መደራደሪያ ማድረግ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ እያወረዱት እያወረዱት አምጥተው ዛሬ ላይ ላለው ስቃይ ዳረጉት ለብዙ ሌላ ሕዝብም ሥቃይ ምክነያት ሆነ፡፡  ነብሩም እንደዛ ነበር የሆነው፡፡
ምን ብዬ መናገር እንደምችል አላውቅም ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ በጣም የገባቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ የወያኔ ኦነግና ሻቢያ ሴራ ግልጽ ነበር፡፡ ብዙ ሰዎች እንደነብይ የተናገሩትን በግልጽ እያየንው፡፡ አማራ ያሉትን በጠላትነት ከመጀመሪያው ኢላማ አድርገውት እንደነበር የተመሰረቱበት ዓላማ ራሱ ምስክር ነበር፡፡ ኦሮሞ ያሉትን ደግሞ ከኢትዮጵያ ማንነቱ በማምከን መብት የሌለው በማድረግ መብትህን እኛ እንሰጥሀለን ብለው ታሪክ ፈጥረው ሰበኩት እውንም ተሳካላቸው አመከኑት ከማንነቱ ለዩት ኦሮሚያ የምትባል አገር በተረት ዱሮ እንደሚሰጠን ሰጡት በዚያች ኦሮሚያ በሚትባል የቅዠት አገር ስደት ከረቸሙት፡፡ አማራ ኦሮሞ የተባለውን ጨምሮ ሌሎችን ሁሉ ሲጨቁን የኖረ ነው በሚል በሁሉም ዘንድ እንዲጠላ ዘመቻ ከፈቱበት፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋነኛ ኢላማ የተደረገው የታሪክ ምዕራፍ የሚኒሊክ ሥርዓት መንግስት ነበር፡፡ ይህ ሥርዓት ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ከልብ (የውሸት ያልሆነ) አንድ አድርጎ ያስተሳሰረ በመሆኑ ኢትዮጵያውያንን ለመከፋፈል ዋነኛ ኢላማ ተደረገ፡፡  ጎበናና ሚኒሊክ በጥምረት የመሠረቷትን ብዙዎችንም ከባርነት ያላቀቁበትን ታሪክ እጅግ በሚያዛዝን ሁኔት በፈጠራ ታሪክ ለውጠው በብዙዎች ዘንድ የጠላት ታሪክ ሆነ፡፡ በተለይ ኦሮሞ የተባለው ሕዝብ በከፋ ሁኔታ ወያኔና ኦነግ በፈጠሩለት የታሪክ መርዝ ተመረዘ፡፡ ራሱን አሳልፎ ለሴረኞች ሰጠ፡፡ ለኦሮሞ በምንም አይነት ጎበና ምልክቱ ሊሆን እንዳይችል አድርገው አመከኑት፡፡ ጎበና ዛሬ ላለው ኦሮሞ ስድብ ሆነ፡፡ ሰኚ ጎበና (የጎበና ዘር) ተባለ፡፡ አዝናለሁ፡፡ ዛሬ ጎበና ቀና ብሎ ቢያይ ጀግኖች ልጆቹ (አርዓያውን የተከተሉት) የሉም፡፡ የጎበና ምድር ዛሬ የምናምነቴ መፈንጫ ነበር፡፡ ጎበና ከራሱ ክልል አልፎ ኢትዮጵያን አንድ ያረገ ጀግና እንደሆነ የኦሮሞ ታሪክ ረስቶታል ብቻ ሳይሆን ጠላት በፈጠረለት ታሪክ ዛሬ ጎበናን እንደጠላት ፈርጇል፡፡ የተስፋዬ ገብረዓብ የቡርቃው ዝምታ ሳይቀር ኦሮሞን ከማንነቱ ለማምከን ትልቅ ሥራ ሆኗል፡፡ የኦሮሞ ጠላት ተስፋዬ ዛሬ አባ ገዳ ተብሎ ጎበና ይረገማል፡፡ እንግዲህ ኦሮሞ በዚህ አስተሳሰብ ነው ነጻነት የሚለው፡፡ ይህ ኦሮሞ ነኝ ለሚል ሁሉ የምለው ነው፡፡
ዛሬ ኦሮሞ ነህ ያሉትን ህዝብ ለይተው በግፍ እየገደሉት ይዘባበቱበታል፡፡ ብዙ ለፐብሊክ መናገር የማልፈልገው ጉዳይ አለኝ፡፡ ብናገረውም ፋይዳ የለውም ለጠላት መጠቀሚያ ከመሆን በቀር፡፡ በሱማሌ ወታደሮች በአረመኔነት የተገደሉትና የተፈናቀሉት አሁንም እሞቱና እየተፈናቀሉ ያሉት ወሬያችን ሆኖ ይሄው ስንት ወር፡፡ አሁን ደግሞ ጨለንቆ ላይ በወያኔ ሰራዊት ደገሙት፡፡ ምን ታመጣላችሁ ነው ነገሩ፡፡ ምክነያቱም አውቀውታል ኦሮሞን የት እንዳደረሱት፡፡ በየአደባባዩ እየወጡ በጮኸ ስልት አደለም፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ይባልልኛል፡፡ ምንን ማለት እንደሆን አይገባኝም፡፡ የምን ሰላማዊ ነው፡፡ በአደባባይ እየገደሉት፡፡ ወያኔ አሁን ያለውን የኦሮሞን ትውልድ ነቅታበታለች፡፡ አዲስ አበባ ልዩ ጥቅም አዋጅ ስታውጅለት ጨፈረ፡፡ የጥላቻ ሀውልት ስታቆምለት ጨፈረ፡፡ የንቀት ንቀት ራስዋም ገድላ ሀውልት ትሰራለታለች፡፡ የቢሾፍቱ ሀውልት ተመረቀለት፡፡  ይህ ሁሉ ስነልቦናውን የምታገጋግጥበት ሥልቷ ነበር፡፡ እግረ መንገዷን በሌሎች እንዲጠላ ሌሎችም በእነዚህ ጉዳዮች ተባባሪ እንዲሆኑ፡፡ ዛሬም የማያረፎ ኦሮሞ ነን የሚሉ በኦሮሞ ሥም የሚነግዱ አያፍሩም፡፡ ትላንት ጨለንቆ ላይ ያለቀውን እልቂት በሚኒሊክ ጊዜ ጨለንቆ ላይ በኦሮሞ ላይ የተፈጸመውን ታሪክ ያስታውሰናል እያሉ ዛሬም አሁን ሕዝብ እየጨረሰ ያለው ሳይሆን ከመቶ አመት ያፉትን ለኦሮሞ ሕዝብ ልዩ ክብር የነበራቸውን ታላቁን ሚኒሊክን በመርዝ ታሪክ ሊመርዙ የሞክራሉ፡፡ ሲጀምር የጨለንቆ የድሮው ጦርነት የተደረገው በሚኒሊክ ሠራዊትና በቱርኮች ይታገዝ የነበረው የሀረሪው አሚር ነበር እንጂ ከነአካቴውም ከኦሮሞ ጋር የሚያገናኘው ታሪክ አደለም፡፡ ወያኔና አጋሮቿ ያ ታሪክ በሕዝብ ሕሊና እስካለ ድረስ መጥፊያቸው እንደሆነ አሳምረው ያውቃሉ፡፡ ለዛም ነው ያንን ታሪክ በጥንቃቄ የዘመቱበት፡፡
ትላንት አማሮች በአርባጉጉና ጉራፈርዳ ተገደሉ እያልክ የምታላዝን አማራ ነኝ የምትልም የዛሬው በሱማሌና በወያኔ ታጣቂዎች በኦሮሞ ነህ ባሉት ወገንህ ላይ የሚደረገውን ግፍ አእምሮ ከአለህ የራስህ አድርገው፡፡ በጉራ ፈርዳና በደኖ የተደረገውም አድራጊዎቹም ዛሬ የሚደረገውም አድራጊዎቹም የተለዩ አደሉም፡፡ አሁን ይሄ የመላላስ አንድነት የምንሰማበት ወቅት አደለም፡፡ የቁርጠኝነት አንድነት እንጂ፡፡ አማራ መሆንህ እኔ ከኦሮሞ ነን ከሚሉት በላይ ስለኦሮሞ አያገባኝም አትበል፡፡ አዎ የኦሮሞን ሕዝብ ወደ አዘቅት የከተቱትን ኦሞ ነን የሚሉትን በይፋ ልንዋጋቸው ግድ ይላል፡፡ ከወያኔ ይልቅ የኦሮሞ ጠላቶችም እንሱ ናቸውና፡፡ በዘር ከሆነ ኦሮሞ ነኝ ከሚለው ባሌ የመርሐቤቴ አማራ ለሰላሌ ኦሮሞ ዘመድ ነው፡፡ የወሊሶ ኦሮሞ ከሀርር ኦሮሞ ይልቅ ለጉራጌ ዘመድ ነው፡፡  በወገን ከሆነ ሁላችንም የአንደ ግንድ እንደሆነን አውቃለሁ፡፡ የአደም ዘር ነን ማለቴ አደለም፡፡ በቀጥታ ኢትዮጵያዊ የሆነ ነገድ ማለቴ አንጂ፡፡ ከዚህ በፊት አንድታነቡት ዛሬ ሳይንስ ስለኛ ማንነት የሚናገረውን አጋርቻችሁ ነበር፡፡
ቀድሞም ከአባቶቻችን ጠላት ጋር በማበር አባቶቻቸው የኢትዮጵያ ጠላት የሆኑ የባንዳ ልጆች የአባቶቻችንን ታሪክ አስጥለው በእነሱ የሴራ ታሪክ ሲመርዙን ፈዘን ማየታችን ሳያንስ የአባቶቻችንን አጥንት እየከሰስንላቸው ይሄው እየተዘባበቱብን የፈጁናል፡፡ ይገባህ ከሆነ አላውቅም፡፡ አደዋ ለብዙዎች የነጻነት ምልክት የሆነው በገበየሁ ጎራ መስዋዕትነት ነው፡፡ የትግሬ ወያኔ ባንዳ ትግሬዎች አይምሰሉህ የሞቱት፡፡ አቶ ለማ ከልባቸው ይሁን ሲሸውዱን ገና ባይጠራም የተናገሩት እውነት ነው፡፡ በአገር ወዳድነት ወኔ እንጂ ተቀጥረው አልነበረም የያኔዎች አባቶቻችን የአለምን ምዕራፍ የሚቀይር ገድል የፈጸሙት፡፡ ወያኔ እነዛን ባንዳ አባቶቻቸውንንና ጌቶቻቸውን (ጣሊያኖችን) ያሳፈሩትን የጀግኖች ኢትዮጵያውያንን ልጆች ለመበቀል እንደመጡ አስተውሉ፡፡ ለዚህም ደግሞ በግልጽ የፃፉትን ማኒፌስቶ ማየት በቂ ነው፡፡ አማራና ኦርቶዶክስ በዚያች አገር ካልጠፋ ያችን አገር መቆጣጠር አይቻልም ነበር ያለው ጣሊያን፡፡ ወያኔ አማራና ኦርቶዶክስን በማኒፌስቶዋ አስቀምጣ ነው የወጣችው፡፡ በአማራና ኦርቶዶክስ ግን መገደቡ በቂ አልነበረም፡፡ በብሄር ከተሸነሸኑት ኦሮሞን ከእምነት ደግሞ እስልምናን በተጨማሪ ኢላማ ማድረግ በማድረግ ዛሬ እየሆነ ያለውን እያደረገች ነው፡፡
ሌላው የሚያሳፍረው ዛሬም ድረስ ትግሬ ወያኔን ድርድር ምናምን እያሉ የሚየሽቃብጡ ናቸው፡፡ ወያኔ ወያኔ ነው፡፡ ትግራይ ያለው ትግሬ ተሸውዶ ወይም በወያኔም ባያምን ተገዶ ሊሆን ይችላል ከትግራይ ውጭ ያለው ትግሬ ግን ምን አልባት ከጥቂቶች በቀር ወያኔ ለመሆኑ ብዙ ጊዜ አይተንዋል፡፡ ወደልቦናችሁ ተመለሱ አይባሉም፡፡ ወደልቦናው የሚመለሰው ሳያውቅ የሚያደርግና ስብዕና ያለው  ነው፡፡ ወያኔ ትግሬ ግን ስብዕና የሌላቸው አረመኔዎች የተሰለፉበት ነው፡፡ አንዳንዶች ቀድሞ ወያኔ የነበሩ አሁን ከወያኔ ውጭ ነን በሚል የሚሰጡትን አስተያየት አፋቸውን ከፍተው ሲያደምጡ አዝናለሁ፡፡ የወያኔ መሥራችና የማኒፌስቶዋ አርቃቂ የነበሩት አንደነ አረጋዊ በሬሄ ያለው ዛሬ ጭራሽ ዋና የኢትዮጵያና የሕዝብ ጉዳይ ሆኖ የወያኔ ጠላት ነኝ በሚል ተሰልፏል፡፡ ምን አልባት በግል ጥቅም አለመጣጣም ከወያኔ ቡድን ወጥተው ሊሆን ይችላል፡፡ በአላማ ግን አንድ ናቸው፡፡ ይልቁንም የወያኔ የውስጥ አርበኛ በመሆን የሚሰሩ እንደሆኑ ማሰብ እንዴት ብልህነት ነበር፡፡ በቅርቡ የወያኔ ዘራፊ ጀነራሎች ጻድቃንና አበበ የሚባሉ እንዴት ለወያኔ እየሰሩ አንደሆነ ከጽሁፋቸው የተረዳሁትን ለጠቁም ሞክሬ ነበር፡፡ ለዘመናት የወያኔ የክት ሰው ሆነው ሲሰሩ የነበሩትን ፕሮፌሰር መስፍንን የአትላንታውን ንግግራቸውን መሠረት በማድረግ የወያኔ የክት ሰው እንደሆኑ ለጠቁም ስሞክር ከአንዳንዶች የተሰጠው አስተያየት በጣም አሳዝኖኛል፡፡ ይሄን መጻፍ የፃፉ እንዲህ ብለው ወያኔን በድፍረት የተናገሩ ምናምን ይሉኛል፡፡ እውነታው ይህን ከአልተናገሩ ሰውዬው ምኑን የክት ሆኑ፡፡ ሊነቃ ይችላል እኮ፡ ወያኔና መስፍን ይግባባሉ፡፡ ለመሆኑ ያኔ መስፍን የቅንጅት ዋና ሆነው የከወኑትን ድራማ መለስ ብለን ማስተዋል እንችል ይሆን? ወያኔ ከጫካ ሳትመጣ ጀምሮ ባለውለታዋ ናቸው ሰውዬው፡፡  አረና ምናምን ብለው ፓርቲ የመሠረቱትንማ ማንነታቸውን ያየንው እኮ በበቀደሙ የወልዲያው ችግር አልነበረም ከዚህ በፊት መተማ ላይ በሆነው እንጂ፡፡
ዛሬ ኦሮሞ ነኝ አማራ ነኝ ሌላም እያልክ እራስህን የሸወድህ ሐቁ ይሄ ነው፡፡ ስነልቦናህን ለወያኔ አታስበላ፡፡ ለማና ሌሎች በንግግር ብቻ ሰልችቶናል፡፡ የኦሮሚያም ይሁን ሌሎች የክልል ፖሊሶች ተባባሪ እንደሚሆኑ ይገባናል፡፡ ግን ስልጣን አለን የሚሉት አሁንም በአፍ ለጥንቃቄ እያሉ ለበለጠ ጥቃት እየዳረጉን ነው፡፡ ትንሽ ቢጀመር  የወያኔ ሰራዊት እንደሚፈረካከስ እናውቃለን፡፡ መላላስ አያስፈልግም፡፡
ልዑል እግዚአብሔር ኢትየጵያንና ሕዝቦቿን ይታደግ! አሜን!

ሰርጸ ደስታ