ከሥርጉተ ሥላሴ 20.12.2014 (ከጭምቷ – ሲዊዘርላንድ።)

„አዋቂ ሰው የጥበብን ነገር በሰማ ጊዜ ያደንቁታል። ዳግመኛም በጥበብ ላይ ጥበብን ይጨምራል። ክፉ ልቦና ግን ከሰማ በኋዋላ ይደፋል። ወደ ኋዋላም ይምለሰዋል። (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፲፭።)

እህስ ቀኒት ባለመቀነቲት – እንዴት አለሽልኝ?
ቀኒት አኩርፋለች። በመንትዮሽ ባላዊ ጭራሮዎች ጨፍረር ብለው ሲዋዘወዙ ታያለች። እሷ ደግሞ ቆፈን አቆዝሟታል። ግራጫማ ሁለት እርግቦች ትንሽ ተራርቀው መልእክት ይጠብቃሉ። ጉማዊ ነፋሻ ጭጎጎት ተጫጭኖቷል። እርግባን ምን አስኝቷቸው ይሆን ፈንጠር ፈንጠር ብለው ያሉት? በማለት መስኮቴ ላይ ቆሜ አስተዋልኳቸው። መለመላቸውን የቆሙው ግንዶች ድርሻችን እንወጣ ብለው በጭራሮቻቸው ኦርኬስተር ከአይዋ ንፋስ ጋር በዝግታ ይደንሳሉ። ውዝዋዜያቸው ግን አንደ ባልስ አይነት ይመስላል። በዝግምታ። እርጋባት ውዝዋዜውን እንደ የመንፈስ ተሃድሶ Medtation የቆጠሩት ይመስለኛል። የሚገርመኝ ከቤቴ ጣሪያ ሥር የነበሩት እርግባን ሰሞናቱን ድምጻቸው መጥፋቱ ነው። እሺ አሁን የት ገቡ ይባላል? ኮሽ አይሌ ጭምቷ ሲዊዝ ለዚህ ለፈርንጆች የገና ባዕል ሁለት ቀን ተኩል ፈቃድ ትሰጣለች። ከትናት ጀምሮ ቢሮዎችና ሱቆች ተከፍተው መደበኛ አገልግሎት ይሰጣሉ። ሌሎቹ ደግሞ ከረፍታቸው ጋር ይሰልቃሉ – ወጋቸውን። እነኝህ ለዬት ያለ ተልዕኮ ያላቸው ናቸው፤ አብዛኞቹ የነፃ አገልግሎት የሚሠጡ ወይንም ከመደበኛው ክፍያ እጅግ በወረደ ዋጋ የሚሠሩ ሠራተኞች ያሏቸው ናቸው። መሰሎቹ እስከ ጥር ሦስት 2018 ድረስ ዝግ ናቸው። ዛሬ ገብያ ወጣ ማለት ፈለግሁ፤ ቤት ያለው ነገር ተለቃልቋል፤ ተሰናዳሁ፤ እናላችሁ የሆነ አንዳች ነገር የጨርቄን ውልብሊት ጎተተኝ፤ ምን ብለህ ነው ደግሞ ብዬ ስጠይቀው፤ የጀምርኩት የነገረ አብይ ጉዳይን አነሳልኝ። እማቀብልሽ ሃሳብ እንዳያመልጥሽ ዓይነት ነው። ቀረሁ። ስለምን? ሃሳቡ በመጣልኝ ሰዓት ቢያንስ መዋቅሩን መሥራት ስላለብኝ። እንደ ቅድመ መሰናዶ ነገር … ቀኒትን አንዲህ እና እንዲያ ልንዘናከትባት ተወሰነላት። እንሆ … ዶር. አብይ አህመድ እባከዎትን ቀኒት ይቀደሱልኝ?
„ … ምክንያቱም ሰው መጀመሪያ የሚቸገረው ካፖርቱን ማውለቅ ስለሆነ ነው ዛሬ። ካፖርት ማውለቅ አንዱ ነጥብ እሱ ነው። የሚታይ ነገሩን ሌላውን አውልቆ  ሰው መሆን። የመጀመሪያው ነገር ካፖርትን ማውለቅ እና ሰው መሆን። በእግር መሬት ላይ መቆም መቻል። የመጀመሪያው ነገር። አንዳንዴ ዶር. ልትሆን ትችላልህ። አንዳዴ ሚ/ር ልትሆን ትችላለህ፤ ጋዜጠኛ ልትሆን ትችላለህ ከሰውነት አንጻር አሱ ትንሽ ነው። ሰውነት ከዚያ የበለጠ ነገር መሆኑን አምነን መቀበል ያስፈልጋል።“  https://www.youtube.com/watch?v=EtKsNqhi_uU
Ethiopia Dr abiy ahmed በመጀመሪያ ካፖርትህን አዉልቅ።
መዳኛ።
የኢትዮጵያ የመዳኛዋ መንገድ ለእኔ ከሞፈር ዘመት አስተሳስብ የፖለቲካ ተጠማኝነት መላቀቅ ነው። ምን ማለት ነው ይሄ? ከሶሻሊዝም ርዕዮት ሙሉ ለሙሉ መውጣት። ከሶሻሊዝም የቅኝ ግዛት ርዕዮት መውጣት እስካልተቻለ ድረስ ዴሞክራሲ ጣዖት ነው። ጣዖትነቱ ደግሞ ድንጋይ ተሰንጥቆ ውሃ እንደ ማፍለቅ ማለት ነው። ዴሞክራሲ በግራው ፖለቲካ ተናካሽ ነው፤ ጠብ ፈላጊ ነው፤ ተንኳሽም ነው፤ እንደ ግራነቱ ሁሉንም ነገር በጥርጣሬ ነው የሚመለከተው። የበጎ ነገር ፍርፋሬ የነጠፈበት ብቻ ሳይሆን እሾሃማም ነው። አዎንታዊነት ዓላማውም ግቡም አይደለም። ቅዱሱ አዊንታዊነት ከነመፈጥሩም አያውቅም። ሁሉን ነገር ከሥልጣን የማማከል ጋር እንጂ ከማህበራዊ ፍላጎቶች፤ ህሊናዊ ፋይዳዎች፤ ከኑሯዊ ችግሮች የመፍትሄ አመንጭነት ጋር የማቀናጀት አቅም የለውም። የግራው ፖለቲካ ውርጭታም ነው። ወዲህ እና ወዲያ የሚመላለሱ የሃሳብ ፍሰቶቹ ጠቃሚ በሆኑ የትውልድ ግንባታ ላይ ያተኮሩ ሳይሆኑ ጨፍልቆ፤ ወይንም ደፍጥጦ፤ ወይንም አስፈራርቶ ግላዊነትን በማኮፎስ ሂደት ነው የሚወራረደው። ኢጎ ለግራ ፍልስፍና ጃንሆዩ ነው። ስለሆነም መንቀል … መንቀል። መትክል የለም። ከመትከል ጋር እውቅና የላቸውም።
በዬትኛውም ሁኔታ የሶሻሊዝም ርዕዮት በሽታ ከህብረተሰቡ ችግር የመነሳት አቅም የለውም። ጥለቱ ጥልጥል ነው። የሚያስረው ነገር ከህብረተሰቡ የሚነሱ ወቅታዊ ሁኔታዎች ሥሙን፤ ዝናውን፤ ሥልጣኑን ተቀናቃኝ ወይንም የሚሸራርፉ ሆኖ ከተገኘ በቀጥታ የጥቃቱ ሰለባ ነው የሚሆኑት። ጉዞው በአረገረገ የመንፈስ አቅም እንጂ ጽኑ በሆነ በቆረጠ የተግባርና የመንፈስ የብቃት ውህድነት አይደለም። ከሁሉ በላይ የግራ ፖለቲካ እጅግ ተጠራጣሪ ከመሆኑ የተነሳ ሁለት እና ከዛ በላይ የሆኑ መልካም ግንኙነቶችን ሁሉ  ከእሱ ድሰቃ ሊያመልጡ አይችሉም። ወይ ይጠቀልላቸዋል ወይ ደግሞ ያጠፋቸዋል። በዚህ ሁኔታ አድጎ ወይንም ለግለግ ብሎ የሚወጡ አዲስ ቡቃያዎችን የማዬት ፈቃድ በፍጽምና ድምስስም፤ ድርምስም ነው። ይህም ማለት ትውልድን መዋጥ፤ ወይንም ማቀጨጭ ዋንኛው መስመሩ ነው። የትውልድን ብልጫነትን ብልህነት የመቀበል አቅምም ሆነ አቅልም የለውም። አደብ አልቦሽ ነው። በመንፈሱ በቃዩን አዲስ የትውልድ የአቅም ማንነት ጨፍልቆ መረማመጃ ወይንም መናጆ አድረጎ መጠቀም ነው የሚፈልገው። ስለሆነም በቀጥታ ከተፈጥሮ እና ከዘመን ጋር በተቃራኒ የቆሞ የእድገት፤ የብልጽግና፤ የግኝት፤ የፈጠራ የጉሮሮ አጥንት ነው። መረጋጋት በእጅጉ ያንሰዋል። ሁልጊዜ ባለበት እንደቆመ ነው እሚያስበው። ያሰረው የእጁ ሰዓት ጊዜን መቁጠሩን እንኳን መቀበል ይሳነዋል። ዕድሜውን እራሱ ቢመለስለት ይሻል። ጥሎት እዬሄደ መወሆኑን ልብ አይለውም። ትልሙ ግትር ነው። ግቡም ገራራና – ያልተገራ። የግራ ርዕዮት ዘመንም እዬተዋሰ መኖርን ነው የሚፈልገው። ምን ማለት ነው ይሄ? ለዘመኑ ድምጽ አድማጭነት አልተፈጠረለትም ማለት ነው። የግራ ፖለቲካ ተናጋሪ እንጂ አድማጭ አይደለም። በሰው ዘመን ውስጥ በአረጀ ማንነቱ ተጥቅልሎ በጉልበቱ ትምክህት ማግሥትን እዬገደለ መኖር የደሙ ሙቀት መቋጣጠሪያ መለኬያው ነው። የሚያሳዝነው ይህን የፈቀዱ የዘመኑ ወጣቶች እንደ ገና መወለድ ከተሳነው መንፈስ ጋር የሙጥኝ ማለታቸው ነው። ለዚህም አብነቱ ይህን ቀንበር ለመሸከም የፈቀደው ጋዜጠኛ አንዱ ጋዜጠኛ ማስረሻ ዓለሙ ነው የኢሳቱ „የማማ“ አዘጋጅ።
ስለሆነም እንደ ዘመኑ የራሱን ፍልስፍና፤ የራሱን የሃሳብ ቋት፤ የራሱን ዕይታ ይዞ የመጣውን የመልካም ነገር ንድፈኛውን የዶር. አብይ አህመድን ዕይታ በቀጥታ የጥቃቱ መጠቃጠቂያ ሰለባ ለማድረግ የፈቀደውም በዚህ ምክንያት ነው። ልክ እንደ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ። እንደ ሌሎችም እኛን ብቻ አድምጡ፤ ተቀበሉን እንደሚሉት የቀጭን ጌታዊነት ትዕዛዝ መጪታ …
የፊደል ገበታ።
ሰው እንደ አደገበት ቤተሰብ ነው ሰብዕናው የሚቀረጸው። ኢትዮጵያን ተጸይፈው ያሳደጉት አንድ ልጅ ቀን እና ወቅት ተንተርሶ ያንኑ ይሁንበታል። በትውስት ማንነት እንዲያድግ ይገደዳል። ንጥረ ነገሩን የሰጠውን የውስጥ ብቃት ማስተዋል ተስኖት እራሱን አሳንሶ ይመለከተዋል። ኢትዮጵያን ግርማው፣ ሰንደቁ፣ ክብሩና ኩራቱ ሆኖ ባደገ ቤተሰብ ውስጥ ያለ አንድ ልጅ ደግሞ ሰብዕናው የሚገነባው በዚህ እራሱን ባለሾለከ፤ ጥገኛ ባልሆነ፤ ንጥረ ነገር በሙሉ እርግጥኝነት መንፈስ „ነኝ“ ብሎ ያድጋል። መሆኑን ያምነዋል። ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ እንደ ነገረን „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ስለተባለ ወይንም ስላልተባለ፤  የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ስለተለበሰ ወይንም ስላልተለበሰ ሳይሆን ኢትዮጵያ የእውቀቱ መሰረት የፊደል ገበታው ሆና አብራው ተጸንሳ፤ ተፈጥራ፤ አድጋ፤ ጎልምሳ ደሙን በደሙ አቅልማ እሱነቱን በረቀቀ ሁልዐቀፍ ህብረ ቀለማት በመገንባት ልዑቅ ማድረጓን ራሱን ውስጡን በመሆን የህሊና አቅሙን በማገናዘብ ይሆንበታል። ውስጡን አናባቢ ነው። ራሱን ሲያው ሚስጢሩን ያገኛዋል። እሱም የሚስጢሩ ቤተኛ ነውና። በደራሽ ነገር ከቶውንም አይናወጽም፤ ወይንም ከጎርፍ ጋር አብሮ አይኩረፈረፍም። ለዶር. አብይ አህመድ ከጽንሰት እሰከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ ኢትዮጵያ የነበረች፤ ያለች፤ የምትኖር ታላቅ ሀገር መሆን የምትችል ስለመሆኗ ሙሉ የሥነ – ምናዕብ ዕሳቤ ያላቸው ዕጹብ ድንቅ ወንድማችን ናቸው። በሳቸው ህሊና ውስጥ እንደ ሽሮፕ በጥብጠህ የምትጨምረው የመርዝ አይነት አይኖርም መቼውንም ቢሆን። እርግጠኛ ሆኜ ነው የምነግርህ ለቤተ መንግሥት ጋዜጠኛው ለማስረሻ አለሙ፤ የአንተን ደግሞ ከትንሳኤ በኋላ ታሳዬናለህ፤ እስከ አሁን ልባችን ሾልኮብን ከሆነ፤ ወይንም እምናያቸውን አምክንዮዎች የምናገናዝብት ጌታው ጭንቅላት ስልብ ሆኖ ከሆነ፤ የቃል አፈፃጸም፤ የመታማን ማተብ ልዩ ሀውልት አሰርተህ ምርቃኑ በርቀት እናይ ዘንድ ከተፈቀደልን ያን ጊዜ 4ኪሎ ላይ እንገናኝ – በቀጠሮ። የዶር. አብይ አህመድ ህሊና ውስጥ ያለው የተስረከረኩ መንፈሶች/ አሉታዊ ዕይታዎችን ማጠቢያ/ ማጽጃ ስልት እንዴት በሃሳብ አስገብቶ ማጽዳት እንደሚቻል ነው የሚመራመሩት። እወቃቸው ሳይንቲሰት ናቸው። ከነገ ወዲያ ዕውን ሊሆኑ የሚችሉ የግሪክ ፈላስፎች የሄዱበትን መንገድ ሳይቀር ለሚተልሙ ጸሐፍትን በማገዝ፤ በማበረታት፤ በማድመጥ እንጠመድ እንጂ፤ ዘራቸውን እንፍልሰው አይደለም የሚሉት። አይገናኝም እኛ ከኖርንበት የፖለቲካ አረንቋዊ ጉዞ ጋር። ለኢትዮጵያዊነት የምህረት ቀን ፍልስፍና ጻድቅ ሰው ናቸው። ለዚህም በቃኝ እስክትል ድረስ በፋክት እሞግተሃለሁ።
መነሻ።
እኮ! የኔዎቹ የቅንነት ርግቦች እንዴት ሰነበታችሁልኝ? ቀኒትን ዶር. አብይ አህመድ ስለጸሐፍት ምን ያስባሉ? ምንስ ይመኛሉ? እንዴትስ ጉዳዩን አጠኑት? ዬት ላይስ ተነሱ የሚለውን መመልከት ከግልብ ጉዞ፤ ከግርድፍ ዕይታ፤ ከሶሻሊዘም ጠብ አጫሪነት እና ግጭት ናፋቂነት ሱስ ወጣ ላላችሁት ቅን ወገኖቼ ንግግራቸውን መሰረት አድርጊ የምለው ይኖረኛል በማህጸነ – ቀኒት። ያሰብኩት ጥቂት ነገሮች ለማንሳት ነበር፤ ነገር ግን ያ ጣፋጭ ልሳንወርቅ፤ እጅግ ሳቢ ለዛ ባለው አንደበታቸው ቃና ተማረኩኝ እና ሙሉውን አቅርቤ እናንተ ደግሞ ስለሁለመናቸው ጥናታችሁን በቅንነት ትለግሡት ዘንድ ወደድኩኝ። አይዋ ወያኔ አንተም ብትሰማኝ እንዴት ደስ ይለኝ ነበር መሰለህ። እና ጡሑፉ ለአይዋ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌስቶ አምላኪዎችም ጭምር ነው። ጥልቀቱ ሰውን ማዳን፤ ተቆርቋሪነቱ ትውልድን በቅንነት መስኖ ማልማት ነው። ህልሙ ኢትዮጵያን አጉልቶ በዕወቀት የማበልጸግ ነው፤ እኔንም፤ አንተንም፤ አንችንም፤ እርስዎንም፤ እናንተንም፤ ሁላችነንም።
በርግጠኝነት የምናጋረው ጉልበታም አምክንዮ ዶር. አብይ አህመድ የተገለጡ መጸሐፍ መሆናቸውን ነው። እንዲህ ዓይነት ወገን ማግኘት በዚህ ዘመን በህልምም የሚታሰብ አይደለም። እንዲህ ዓይነት ልዑቅ ሆኖ ቅን ሰው ኢትዮጵያ በ100 ዓመትም አታገኛቸውም። የትኛውም ወገን በፈለገው ጊዜ ሊያነባቸው፤ ሊተረጉማቸው፤ ሊያመሳጥራቸው፤ ወይንም ሊተቻቸው የሚችሉ በግልጽነት ሰብዕና የተቀደሱ አድህኖ ጠበል ናቸው። በዶር. አብይ አህመድ መንፈስ ውስጥ እያደባና ጊዜ እዬጠበቀ የትኛውንም ወገን ተጠቂ የሚያደርግ አንድም የተንኮል፤ የሸር የተቆለፈበት የሴራ ካርታ የለም። በልጅነታቸው፤ በወጣትነታቸው፤ በሥራ አካባቢያቸው፤ በጉብኝቶቻቸው፤ በትግል ተመክሯቸው ሁሉ የሚያዮዋቸው አመክንዮዎዮች ለሳቸው የመንፈስ ግንባታ ስንቅነት ተጠቅመውበታል። ቅንጣት የአምክንዮ ሽራፊ ጥግ አጥታ አልፈሰስችም። የሾለከ ጊዜም የላቸውም። በሂደቱም ኢትዮጵያን ከነውበቷ የልባቸው ማህደር አድርገዋታል። ስለሆነም ነው ትርጉም ለመሆን ያላቸው አቅም ሆነ አቅል ጎልቶ እኔ በግሌ እንዳዬው ያደረገኝ። አሁን ለእኔ በሰዋዊነታቸው ውስጥ ብቻ ያሉት ፍሬ ነገሮች ብቻ ናቸው የሙግቴ የመነሻ አቅሞች። የተመስጧቸው፤ የጥሞናቸው ቃና Magnet ነው። ይህን ከማንፌስቶ ያፈነገጠ ህይወቴን የመረጥኩትም፤ አንዲህ ካለ የመንፈስ ነፃነት ቅድስና መነሳትን ስለፈቀዱት ነው። በራሴ ውስጥ የሚሰሙኝን የቀጥታ ስሜቶች እንድገለጽ የሚያደርገኝም ይሄው ነው። ድርጎኛ አይደለሁም እንደ ማለት። የሚሰማኝን ለመናገር፤ ለመጻፍ፤ ቅሬታዬን ለመግለጽ የፊትም፣ የኋላም፣ ገፊ ወይንም አነሳሽ ምንም ተለጣፊ ነገር የለኝም። የማራምደው ሰውን ማዕከሉ ያደረገ ሩህርህ የቅንነት ፖለቲካ አቋም ከሥልጣን ጋር ንክኪ ያለው ምንም የመንፈስ ተጠማኝነት የለብኝም። ስለዚህ ሰው ባይከፋብኝ ብምረጥም፤ በምገልጸው ሃሳብ ውስጥ ሰው ፈቅዶ እከፋለሁ ይለብኛል ብዬ የምቆጥበውም ወይንም በመጠራቅቅ ሰንጌ የምይዘው ወይንም በይጄ የማቀርበው የሃሳብ ፍሰት የለም። እንደ ተፈጥሮዬ ግልጽና ቀጥተኛ አቋሜን ነው የምገልጸው። ፈሬ የምሆነው ሃቅን የሳትኩት ዕለት ብቻ ነው። ያ ደግሞ አይሞከርም።
ዛሬ በማነሳው ሃሰብም ውስጥ ቅንነት፤ ተቆርቋሪነት፤ የእኔነት በውስጡ ቃናዊ ተደሞውን ስላገኘሁት ነው። አሁንም ይህ መንፈስ  የእኔ የራህቤ መዳህኒት አድርጌ እወስደዋለሁ። በግራ ፖለቲካ እንደ ጦር የሚፈራው ሚዲያ ነው። የሃሳብ ነፃነት ነው። የጸሐፍት ብዕር ነው። ስለምን? ግራ ዴሞክራሲው የድንጋይ ጣዖት ስለሆነ። ጣዖቱ ደግሞ በሴራ እርሾ ተቦክቶ የተጋገረ አሽዋ ነው።
መድህንነት።
ዶር. አብይ አህመድ እንዲህ ይሉናል „ ሰው ሲፈጠር ሰው ነው። ዕጹብ ድንቅ ፍጡር ነው። ማሰብ ያለበት በዚያው ልክ መጠን ነው። መመለስ ያለበት በዛው ልኩ ነው። ማንነቱን ያጣ ዕለት ብዙ ክፉ ነገር ይሸከማል። ሁለት ሰው ሁነው እዬተጓዙ አንደኛው በጎርፍ ውስጥ ጊንጥ ያያል። ጊንጥ ስትናደፍ በጣም የምታም ነገር ነች። እና ጎርፍ ሊወስዳት ስትሰቃይ ያያል፤ እጁን ዘርግቶ ሊያድናት ሲሞክር ነደፈችው። በጣም ያማል፤ ታውቃላችሁ። አመመው፤ ትንሽ ቆይቶ ሲያያት በጣም ትሰቃያለች፤ አሁንም ድጋሚ ሲዘረጋ ነደፈችው። እና ጓደኛው አብሮት የነበረው „አንተ ሞኝ አልገባህም እሷ ልትገድልህ እዬሞከረች ነው። አንተ ልታድናት ራስህን ታስጠቃለህ ብሎ ነቀፈው።“ ሞኝ ያልገባህ አለው ያኛው ሰውዬ፤ ግን ሸሚዙን ቀዶ ጠቅልሎ ሦስተኛውን ጊዜ ሲሞክራት አዳነት። እና ለጓደኛው አንተ ብዙን ጊዜ ጊንጦች ስታይ ጊንጦችን ትሆናለህ አለው። እኔ ሰው ነኝ፤ የተፈጠርኩት ለማዳን፤ ለማሻገር ለማብቃት፤ ለመርዳት ነው። ጊንጥ ደግሞ የተፈጠረችው ጥቃት የተሰነዘረ ስለመሰላት ለመንደፍ ነው። እሷም ስራዋን ነው የሰራቸው። እኔም ሥራዬን ነው የሰራሁት። ማዳን ሥራዬ ስለሆነ። ለምንድን ነው አንተ እኔን ታጥቀህ ጊንጥ እንድሆን እምትመክረኝ አለው። የእኔ ተግባር ማዳን ሆኖ ሳለ ስትሞት ዝም እንድል ለምን አለው።“
በነገራችን ላይ ዶር አብይ አህመድ፤ እኔን ጊንጥ ነክሳኝ ታውቃለች። አወቀዋለሁ ህመሙን። ስቃይ ብቻ ሳይሆን መርዙ ተበጥቶ ካልወጣ በተለይ የቆላ ከሆነች ጊንጧ ትግድላለች። አዬህ ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ ይህን የመዳኛችን መንገድ ነው አንተ የምትቀናቀነው። ለመሆኑ ከሴራ ፖለቲካ እንዲህ የጸዳ ሊሂቅ ለማግኘት ስንት ዘመን መጠበቅ እንዳለብን ታውቃለህን?!!
ክሽፈት።
„ክፋት ስታዩ ያን ለማድረግ የምትሞክሩ ከሆነ ተሸንፋችኋዋል ማለት ነው። የሰው ልጅ በጎን ለማወቅ ያለው ጥረቱ ተሽንፏል።“ አሸምቆ ሰውን መተናኮልን ክሽፈት ነው የሚሉት። ምርኮኛነት ነው የሚሉት ክፋተኝነትን፤ ጊንጣዊ ባህሪን፤ ተናዳፊነት። ለእኔ የሶሻሊዝም ንድፈ ሃሳቡ ሳይሆን ተከታዮቹ ሶሻሊዝምን ገልብጠው ሥራ ላይ የዋሉበት መንገድ የጊንጥ ተፈጥሮ ያለው ሆኖ ነው ያገኘሁት። ጉዟችን ሁሉ በሃሳብ በጊንጥ ብርጌድ፤ በጊንጥ የክፍ/ጦር፤ በጊንጥ ሻለቃ/ በጊንጥ ሻንበል ደረጃ የተዋቀረ ነው። ጋሬጣ ነው። ቅንነትን ማምለክ አልተቻለነም፤ ደግነት መዋጥ አልቻልነም፤ አዎንታዊነትን ውስጣችን ማደረግ አልደፈረንም፤ ፍቅርን ሐሤት ሰጭነቱን አላስተዋልነውም፤ ሰላምን አመንጪው መንገድ የሆነወን የህዝብ ታማኝነትን ለተፈጥሯዊነት መገበር ስለመሆኑ አልተገነዘብንም። ተፈጥሮን አብዝተን ፈራነው። በመንፈሳዊ ሃብቶቻችን ላይ ጦርነት ሰበቀን። ቅንነትን የሚራዱትን ሙሴዎቻችን ለአፍታ በቅንነት የሚይ ዕዝነ ልቦናችን መርከቡ እንኩት እንዲል ፈቀድንለት። ይሄው 42 ዓመት ሙሉ በጊንጡ ሶሻሊዝም መርዝ ከትመናል። ትውልድ እዬታጨደ የወንበር መልስና ቅልቅል ልባችን ጥፍት አድርጎ ላይ ታች ያባዝነናል።
መንገድ።

„ኢትዮጵያ – ሚኒስትሩ በንባብ ለሕይወት ላይ / Ethiopian Minister about Reading and Life, Ato Abiy Ahmed.“
የጸሐፍት እውነታዊ ሰብዕና።
„ … ደራሲያን ሲጽፉ እንጂ መድረክ ሲያሞቁ እንብዛም ስለማይታወቁ፤ በብዕር ቢሆን ብዙ ማድምቅ ትችላላችሁ።“
ዶር. አብይ አህመድ እራሳቸው የጸሐፍት ቀን ናቸው። ይሄ ነፍስ ያለው አገላላጽ አዎንታዊ ጸሐፍት የማንፌስቶ ባርነታቸውን አሽቀንጥረው ወደ ተፈጥሯቸው እንዲመለሱ አለስልሰው የገለጹበት አንደኛው አናት ጉዳይ ነው። እኔም እንዲህ እላለሁ — ለቲፎዞ መነጠፍ ለጸሐፍት ሸክማቸው ነው። ለጸሐፍት ራሱን ችሎ በጸና ማንነት መቆም ደግሞ አውራቸው ነው። መንፈሳቸውን ትውልድ ጠጥቶ፤ መንገዳቸውን ተከትሎ ሲበቅልበት ነው ጌጣቸው። የመንፈስ ማልሚያ መስኖ ሆነው ማስበል ሲችሉ ነው ኑሮን ኖሩት ጸሐፍት የሚባሉት እንጂ ሲታጀቡ ወይንም ሲጀቦኑ አይደለም። ጸሐፍት ንፋስ በመጣ ቁጥር እንደ አልጸና ጉተና ሳያወዛወዙ ነገን በተባ የአዎንታዊ ምናባዊ ፍሬዘር በጽናት ሲያጸድቁ እንጂ የከንቱ ውዳሴ ዲሮቶ ተጠማኝ እንዲሆኑ አይደለም የተፈጠሩት። በመወደድና በመጥላት፤ በክፋት እና በምቀኝት፤ በበቀል እና በቅንነት፤ በፍቅራዊነት (LoveIsm) እና በጥላቻ፤ በሌብነት እና በሃቀኝነት፤ በአዛኝነት እና በጭካኔ፤ በሃዘን እና በደስታ፤ በአግላይነት እና በአቅራቢነት፤ በትውልድ ቀጣይነት እና በጠፊነት ያለውን ልዩነት አበጥረው፤ አንተርትረው በማቅረብ መንሹ መሆን መቻል ነው ጸጋቸው። በባይታዋርነት መሃከል ያለውን የማይገናኝ መንገድ ግልጥ አድርገው፤ ደልድለው፤ አዝርተው የተጣራ የመልካም ዜጋ ቡቃያ አራት ዓይናማ ገበሬ መሆን ሲችሉ፤ አንደ ተሰጣቸው የሰማይ መክሊት ሆነዋል ማለት ይቻላል። ዶር. አብይ አህመድ ይህን ነው እያዋዙ ከንጹህ ልባቸው የመነጨውን ፈገግታ ፍልቀ – ጠሃይ እዬመገቡ ጣል ያደረጉት እንደ መቅድምነት – በብጡልነት።
ክብረት።
„ፓሪስን በንባብ ያስተዋወቀኝን ሰው ከደጅ አገኘሁት፤ በእናንተ መካከል ሆኖ ሃሳብ መሰንዘር ቀላል አይደለም፤ ብዕርና እስክርቢቶ እንድናገናኝ ያበረታታችሁን፤ ከማንበብ ውስጥ ዕውቀት፤ ጥበብ እንደሚፈልቅ መንገድ ያሳኛችሁን ታላላቅ ሰዎች አላችሁ።“
ይህ አክብሮታዊ መንገድ የጸሐፍት ጧፍ ያሰኛቸዋል። አዎንታዊነትን ሰንደቁ አድርጎ የሚነሳ፤ ጸሐፍትን ክብረቴ የሚል ሰብዕና ማግሥታዊነት ጽንሱ ነው። ማግሥታዊነት አጀንዳው ነው። አዎንታዊ ጸሐፍት ውርሳቸው፤ ቅርሳቸው ነገን ማደራጀት ነው። ነገ ከመምጣቱ በፊት ቀድመው የመምራት ጥበብ ነው የተሰጣቸው – ከላይኛው። ነገ ደግሞ ቀጣዩ ትውልድ ነው። ትውልድን በእኩልነት አክብሮ የተነሳ መንፈስ ብርሃን ነው። ብርሃን የጨላማውን መንገድ እንድንደፈረው አቅምና ጉልበት ይሆነናል። ጧፉ – ጧፉን እራሱን ከማክብር ስለተናሳ የጧፉን ቤተ – ትጋት፤ የጧፉን ቤተ – ታታሪነት፤ የጧፍን ቤተ – ንጋት ዕወቅና ለመስጠት እግድ የለበትም፤ እንደ ጧፉ ይጣፍጣል፤ ጥፈጣው በፍውሰት ስክነት ይደርባል። የብሥራት በር ተከፈተ፤
አስተውሎት።
„የመጀመሪያው በንባብ እና በህይወት መካካል ያለውን ትስስር፣ ርዕሱ ዝም ብሎ የተሰጠ ሳይሆን ከጅምሩ የተሳሰሩ፤ የማይነጣጠሉ ነገሮች መሆናቸውን ማመላከት ይፈልጋል። የሰው ልጅ ተፈጥሮን ማንበብ ከመጀመሩ በፊት፤ ከሌሎች የዱር እንሰሳት የማይለይ በተናጠል የሚኖር፤ የማህበር ኑሮ መሻሻል ኑሮ የማያልቅ ጥቃት በዬቀኑ የሚያጋጥመውን ከአደጋም የተነሳ ቁጥሩ ያልበረከተ ህዝብ ነበር፤ የሰው ልጅ ተፈጥሮውን አንብቦ እሳት ከፈጠረ በኋዋላ እሳትን ለመሞቅ፣ በጋራ ለመሰብሰብ ነው ቋንቋ የተፈጠረው፤  የመጀመሪያው ሰውን የማሰበሳብ ሂደት ነው ቋንቋን የፈጠረው“
አሁን ከዚህ እሳቤ ውስጥ አንድ ብልህ ነገር አገኘሁ። ጦማሪ በፈቃዱ ሃይሉ ሃሳብን የመከተል፤ የመግለጽ ድፍረቱን ሆነ ግልጽነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የአሉታዊ ጸሐፍትን ቋት ተከታይ መሆኑ ያን እንደ አንድ የዕወቀት መልዕክተኛ አድርጎም ወስዶታል። አማራን „ግላዊ“ ይለዋል። ይህ ማለት ዛሬ አማራ በ21ኛው መቶ ክ/ዘመን ላይ ሳይሆን የማህበረሰቡ የእድገት ደራጃ እሳት ከመፈጠሩ በፊት በነበረው ዘመን ውስጥ ያለ ማህበረሰብ አድርጎ ነው ጥቃቱን የሰነዘረው። በዚህ መስመሩ ለማጥቃት የሄደበት መንገዱ በቂም ቋጠሮነት የሰከነ ነው። አማርኛ ቋንቋንም አላተረፈውም። በቅናት ምንጥል ያለ የመንፈስ ተዋረድ አዳምጫለሁ፤ እርግጥ ነው በዕድሜው ልክ፤ በእውቀቱ ብቃት መጠን፤ መሬት ላይ በሠራው የሰብዕዊነት የጥናት እና የምርምር ፍልቅ ብቃት ጸሐፊ፤ እንዲሁም የሰብዕዊ መብት ተሟጋች ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው ትውልድን በአቅሙ ሊያበቅል በሚችል ጉልበታም ትህትናዊ አምክንዮ ሞግቶታል። ዛሬ ከሥር፤ ምርኩዙን እለጥፋለሁ። ምክንያቱም አዎንታዊ ተኮር ትውልድን መገንባት ተልዕኮን የተመሰጡት የዶር. አብይ አህመድ ቅናዊ የህሊና መሬትን የማልማት የቤት ሥራ ግዝፈትን፤ ተጋድሎው የሚጠብቀውን የሃላፊነት ደረጃ ማጤን ይቻል ዘንድ። አማራን አልቦሽ ግንጥል ጌጥ፤ ግማሽ ራስ ሹሩባ ነው እና። ሞራሉ ሊጠበቅለት ይገባል፤ ይህ በዬዘመኑ መከራን ግማዱ ያደረገ ማህበረሰብ። እውነት ለመናገር አማራን በማግለል ሂደት፤ ሥነ – ልቦናውን በመፈታተን ተቃርኖ ውስጥ ያሉት ውርዘቶች ጠረኑ ይጎፈንናል፤ በነገረ አማራ የጥላቻ አዟሪት ለተጠመዱ ሊሂቃን ያተኮሩበት መስመር ገፊ ነው። በሉ የተባሉትን ለሚሉ የ21ኛው ክ/ዘመን የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችም ውሃ ያዘለው የተራራ ግብግብ ፈተና ይሄው ነው። በመሆን መጀገን ወይንም በመሽሎክ መሸነፍ።
ወደ ዶር. አብይ አህመድ ፍልስፍና ስሄድ፤ የማደራጀትን አስፈላጊነት ከነምንጩና ጠቀሜታ፤ ከቋንቋ ጋር ያለው መስተዋድድና መስተጻምርን በፍቅራዊ ጥበብ አዋደውታል። ተፈጥሮን ማንበብ እሳትን በመፍጠር የሄዱበት መንገድም፤ ተፈጥሮን በጥልቀት የማዬት ክህሎት በመጸሐፍ ውስጥ እንዴት እንደመጣ የዕድገቱን መሠረት ለማጠዬቅ የሄዱበት መንገድ ዕጹብ ነው። ተፈጥሮን ማንበብ የገዘፈ የእውቅት ህዋስ ስለመሆኑ ነው የገለጹት የትኩረት ቤተኛው። የግድፈታችን ምንጩም ተፈጥሮንና ሂደቱን ለማንበብ አቅም ስለሚያነሰን፤ የምናብ እርቀታችን የታቆረ፤ የተቋጣጠረም እንዲሆን አድርጎታል። ለዚህ ነው ጉልበታም ሃሳብ ተፈሪ የተሆነው። ከጊዜው ጋር መራመድ ያልቻሉ የድንጋይ ትክሎች ጊዜ ያጸደቃቸውን፤ ሂደቱን የተቀበሉ ሃሳቦችን አንጥረው ይመልሷቸዋል፤ ወይንም አጋጣሚ ፈጥረው ድራሻቸውን በፕሮፖጋንዳ ያጠፉታል። እንደ ተፈጥሮ የጉዞ እድገት እኩል ወይንም የሚመጥን የመቀበል አቅም ህሊናችን አለው ግን አይፈቅድም። ስለምን የተጠመደበት የአሉታዊ ሃሳብን ጣዖት ሰንቋል እና።
ሥነ – ጥበብ እና የትውድል ግንባታ ባለርስትንት በሚመለከት እንዲህ ቀምረውታል – ብልሁ።
„ … ሰው እዬበዛ ሲሄድ በንግግር ሃሳብን መግለጽ ብቻውን በቂ ስላልሆነ፤ በስዕል፤ በቅርጽ በኋዋላም በፊደል ሃሳብን „ሸክኖ“ ማቆዬት ለትውልድ ማሸጋጋር አስፈላጊ የሆነው።“
እዚህ ላይ የሥነ – ጥበብ ትውልድን በመገንባት ሂደት ባለሙሉ ሥልጣን ቀዳሚ፤ አውራ፤ እጬጌነቱን እናያለን። በዚህ አገላለጽ ሥነ – ንግግር በማህበረሰባዊ የእድገት ሂደት ቀዳሚው የሥነ – ጥበብ ግንድ ሆኖ እናገኘዋለን። ንግግር ሥነ -ጥበብ ነው። ስለምን? ተስጥዖ ስለሆነ። እርግጥ ነው ተስጥዖውን በክህሎት በሥልጣና ማዳበር ይቻላል። የሥነ – ሥዕል የጥበብ ተክለ ሰውነት ከቀዳማይነት ቀጥሎ ያለ ረድፈኛ ነው። እንዳሻን ልንዳንሰበት የማንችለበት ሚስጢር ያለውም ከተፈጥሮው ነው። አሁን ኢትዮጵያ ያለችው በዞግ ፖለቲካ ውስጥ ነው። አንድ ዞግ ሌሎችን ጨፍለቆ ወጥቷል። ይህ ዓሊ አይባልም። ይህ ዞግ ትግራዊነት ነው። ትግራዊነት ኢትዮጵያዊ ዜግነትን የተዳፈረ ስንኩል የምናብ ብቻ ሳይሆን የህልም ማወራራጃ ሽንክ ዕሳቤ ነው። መንፈሱ ዘር አልባ ነው ማለት አይቻልም። በተሰወረ ሁኔታ ተከታዮች አሉት ድፍን ተጋሩ። ሌሎችም ከዋናው የህይወት ነፍሳዊ አልፋነት መነሳት የተሳናቸው፤ ይህን አስፈጻሚው ደግሞ ካለ አቅሙ በተወጠረው የተጋሩ እጬጌው ኢህአድግ የሚባለው ማህበር ነው። ከ5% ሩቡ የፓርማ አባላት የሥራ አስፈጻሚ ኮሜት ባለሙሉ ሥልጣን ነው። ሲያስፈልግ ደግሞ የጠላ ሰንበተኛውን ዘልሎ ድርጀት ነኝ እያለ ይኮፈሳል። ዕዱሉ ተመቻችቶ ተገኝቷል። ታላቁን ተፈሪ ማንነት ድብዛውን አጥፍቶ በዘመን ጥምዝ አዟሪት መቅኖ ማሳጣት። አሁን ባለው ሁኔታ የትም ቦታ ንግሥና ልዕልና ያለው የብቃት፤ የችሎታ፤ የአቅም፤ የክህሎት ሳይሆን ዞጋዊነት – ትግራዊነት ነው። 95 ሚሊዮን ለአንድ ተማላ የተጋሩ መንፈስ ይነበረከካል። ያረገርጋል። ዓይኑ እራሱ ይፈራል። ተጠቂ ያልሆነ መንፈስ ቢኖር ሥነ – ሥዕል ብቻ ነው። ትግራዊነት ያልፈነጨበት፤ ያልጨፈረበት፤ እንዳሻው ያልጋለበበት አምክንዮ ቢኖር ሥነ – ሥዕል ብቻ ነው። የሥነ – ሥዕል መክሊት አሰጣጡ የጥቂቶች ብቻና ብቻ ስለሆነ ነው። በአፈጣጠሩም ተከታይ ነው። ከሥነ – ሥዕል ቀጥሎ ያለው ቅርጻ ቅርጽ ሲሆን ይህም ቤተ – ሥዕል ስለሆነ ልጁ ነው ብዬ ነው የማስበው። ፊደል እንግዲህ ለሥነ – ንግግር፤ ለሥነ ጥበብ ግንድ የልጅ ልጅ ልጁ መሆኑ ነው በእኔ ግንዛቤ ከዶር. አብይ አህመድ ጥልቅ ትንታኔ ስነሳ። እርግጥ ይህ በማህበረሰብ እድገት ጥናት እና ምርምር ከቀደምቱ መነሻነት ያደረጉት የእውቀት ዘርፍ ሲሆን እኛ ልብ ብለን ያላያናቸውን ጉዳዮች ነው ዶር. አብይ አህመድ ደግሞ የግኝቱን መሰረት ወደ ውስጣቸው አስገብተው በኢትዮጵያዊነት ሥነ – ልቦና ፍልስፍና ልክ ፈትሸውታል። ይህ የአትኮሮታቸው ሁልአቀፍነት ክህሎት ነው እኔን የሚመስጠኝ። እኔ ወደ ውስጣቸው እንዳይ፤ እንድመለከት፤ እንዳስተውል የጋበዘኝ – በፋቀዱ ፋይዳው እራሱ በመርከቡ ወስዶ ከብቃት ውሃ ልኩ አደረሰኝ።
ሰዋዊነት።
„ሰው  ተፈጥሮን ማንበብ ካልቻለ፤ ንባቡን ማጋራት ካልቻለ፤ ህይወት መቀጠል አይቻለውም“
ብዕር ለሚያርዳቸው፤ ብዕር ለሚያንቀጠቅጣቸው፤ ብዕርን እንደ ጦር ለሚፈሩት የግራ ህሊናዎች፤ የሚሊዮኖችን ነፍሶች ገዳዮች ስለመሆናቸው ነው ዶር. አብይ አህመድ የሚነግሩን። እንዲህ አይነት ሽርሸራ፤ ቡርቡር ሰብዕናዎች፤ ሰው የመሆን መለኪያቸውም አንዳች ንጥረ ነገር፤ ለራሱ የማይሆን ንጥረ ነገር የለውም ነው የሚሉን። አንድ ሰው ቢያንስ እራሱን ለማስቀጠል ማንበብ፤ ያነበበውን ማጋራት አለበት። ይህን ባይችል እንኳን፤ አንብበው ለማጋራት የሚሹትን እንቅፋት አይሁን ነው የሚሉት። ዕውቀት የማንበብ ውጤት ነው። ዕውቀት የተፈጥሮ አውታር ነው። በዕውቀት ውስጥ ያለውም ሰዎች በጻፉት ዓውደ ሥርዓት ትምህርት ዲግሪውን አግኝቶ፤ ግን ጸሐፍትን ይፈራል። እነዛ ቀደምቶቹ ይህን ባያድርጉ እሱ ዛሬ ፕሮፌስር፤ ዶር፤ ኢንጂኒር፤ ባለ ማስተር ባለ ኮሌጅ ምሩቅ መሆን ባልቻለ ነበር። ለዚህም ነው እኔ በውስጥ ያለው የድንጋይ ሃውልት ከዘመኑ እድገት ጋር ለመሄድ ያልፈቀደ የተቋረ ወይንም አንድ ቦታ ላይ የቆመ ነው የምለው። የቅራኔው የጦር ሜዳ ያለውም በዚህ የምኽዋር ሰቅ ውስጥ ነው። ክፍተቱን ለመድፍን በሚተጉ ትጉሃን እና ክፍተቱን ሳይደፈን እንደ ተቀዳዳ መጓዝ በሚሹ የሃሳብ ጉጉሶች 40/ ከዚያም ያለፉ ዓመታትን ሁሉን መከራ ከዘነን፤ በመከራ ምንዛሬ ዝርዝርዝሮች የምነቆዝመውም ለዚህ ነው። በቃን! ወያኔ ሃርነትን ስንል፤ በቃህን ሾሻሊዝም! ማለት አልቻልነም። ጋዜጠኞች እንኳን። ሶሻሊዝም የጋዜጠኛ ሰብዕና ጸር ነው። ሶሻሊዝም የነፃ ሃሳብ ፍለቀት አንጡራ ባላንጣ ነው፤ ሾሻሊዝም የምንብ ሩቅ ዕሳቤዎችን ገዳቢ ገደቢስ ጣዖት ነው። አንዱ የዚህ ቁዘማ ቤተኛ ደግሞ የኢሳቱ „የማማ“ አዘጋጅና አቅራቢ ጋዜጠኛ ማስረሻ ዓለሙ ነው።
ማጠቃሻ።
ዶር አብይ አህመድ ህይወትና ተፈጥሮን ማንበብ የሰዋዊነት መለኪያ አድርገው ሲያቀርቡ ማጣቀሻቸውን እንዲህ ሲሉ ነው
“ለዚህም ታወቂው ደራሲ ማክሲም ጉርኪ በንግግሩ ውስጥ ጎልቶ የሚወጣው ጥበብ እና ሳይንስ ህይወትን ለማንበብ ተዋህዶ የሚገኙበት አንድ ሥፍራ ቢኖር፤ እርሱም መጸሐፍ ነው። ይላል“
ከዚህ ላይ በርካታ ቁም ነገሮችን ነገሮችን ማዬት ይቻላል። የዶር አብይን የአንባቢነት ደረጃ፤ አንብቦ የመረዳት ሁናቴ፤ የተረዱትን የመቀበል ክህሎት፤ ክህሎቱን የእኔ ብሎ ቤተኛ የማድረግ ደፋር አቅማቸውን ያሳያል። በሌላ በኩል ታላቁ የብዕር እጬጌ ሩሲያዊው ማክሲም ጉርኪን ስለምን ከዚህ አመጡት ብዬ እኔ ሳስብ፤ ለሴቶች ካላቸው ክብር ነው ብዬ አመንኩ። የብዕሩ እጬጌ ማክሲም እንደ ዕንቁ የሚታይለት „እናት“ የሚለው መጸሐፉ ሲሆን፤ አንደ ተፈጥሯዋ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮ ልዩ ሥጦታ አድርጎ ነበር በመጸሐፉ ውስጥ ያመጣት። ታውቃላችሁ አይደል፤ ቅኖቹ የኔዎቹ— የመጀመሪያዋ የህይወት መምህር፤ አስተማሪ፤ ሐዋርያ እናት መሆኗን። አዎን እናት/ ሴት የመጀመሪያዋ የፊደል ገበታ ናት። ውስጧ ማህጸኗ 12 ፕላኔት አይደለም ያለው 13ኛም አለው። 13ኛው ፕላኔት የእናት / የሴት ርህርህና ይባላል። በዚህ ተፈጥሯዋ ውስጥ ያለች ሴት መድህን ናት። ፈውስ ናት። አማካሪም፤ ተንባይም ናት። ቁልፍ አላት። ስለምን? መፍትሄ አመንጭም ፈጣሪም መጸሐፍ በመሆኗ።
ሌላው ዓለምን ማወቅ፤ መፈላሰፍ፤ ነገን ማስጌጥ፤ ማግስትን መግራት፤ ትውልድን በአወንታዊነት አብዮት መገንባት፤ ኑሮን በአቅም ማጣፈጥ፤ ህይወትን ትርጉሙን ሙሉዑ ማድረግ የአወንታዊ ጸሐፍት ሊቅነት ያስገኘው ውጤት ነው ነው የሚሉን ሊሂቁ። ስለሆነም ጸሐፍት የህይወት፤ የኑሮ፤ የመተንፈስ፤ የትውልድ መሪዎች ናቸው ነው የሚሉን። ይህስ አብይ ኬኛ! አያስኝ ይሆን? በዚህ ውስጥ የቀለም፤ የፆታ፤ የዕውቀት፤ የዞግ፤ የዜግነት፤ የቆዳ ቀለም፤ የሃብት ልዩነት፤ የአህጉር፤ የደረጃ ልዩነት አለውን? ከፍና ዝቅ አለን? የክትና የዘወትር አለን? የማንፌስቶ ማህበርተኛነት እና አልቦሽነት አለን? የሁሉም የፍቅር እቅፍ በዚህ እልፍኘ ሃሳብ የእኔ ተብሏል። ለዛውም በአክብሮት እና በጥልቅ ተመስጦ።
ጓደኝነት።
„መጸሐፍ ብርቱ ጓደኛ ነው። መጸሐፍ እጅጉኑ አድማጭ የሆነ ጓደኛ ነው። በምክንያት መከራከር የሚችል ጓደኛ ነው። ከእውነተኛ ከሰው ጓደኛ የሚለዬው ከተከራከረ በኋዋላ የማያማ ቅሬታ complain የማያደርግ መሆኑ ብቻ ነው“
ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ ይህንስ እንዴት ታብጠለጥለው ይሆን? አዬህ ሳታስተውል የማጣጣል አዝናኝ ቆይታዊ ዝግጅትህ ምን ያህል እንደ ጎዳህ እስቲ ከልብህ ሆነህ እዬው። እያስተማሩህ ነው። የህሊና ሰሌዳህን ጣዖትክን ናድ አድርገህ፤ ፍርስራሹም አቧራ ለብስ ስለሚሆን ይህን ደግ ሃሳብ እንዳያውከው አስኳባ ነገር ፈላልገኽ ጠረግ … ጠረግ አድርገህ አድምጠው። ልብ ነው የሚያው ዓይን አይደለም። እዝነ – ህሊናህን ለመልካም ነገር፤ ለአወንታዊነት አሰልፈው፤ በቂም ወይንም በቅናት ቁርሾ ተነሳስተህ ትቢያን ከማልበስህ በፊት። መለወጥ።
የኔዎቹ ናፍቆቶቼ ቅኖቼ … ። ጥቅም የማይፈልግ – ጓደኛ፤ የት ይገኛል? ጓደኛን የሚያደምጥ ጓደኛ፤ የት ይገኛል? ጓደኛን የሚረዳ ጓደኛ የት ይገኛል? ጓደኛውን የምላሽ መላሾ የማይጠይቅ ጓደኛ – የት ይገኛል? ጓደኛ የልብን የሚያወያዩት ጓደኛ የት ይገኛል? ግን በአምክንዮ አቅም የሚከራከር ጓደኛ የትኛው ፕላኔት ላይ እንለመው? የጓደኝነትን ተልዕኮ በጥልቀት ምን ሊሆን እንደሚጋባው ነው ያመሳጠሩልን። የሚያስተምር፤ የሚመክር፤ የሚረዳ፤ የሚመረምር፤ ህሊናን በመልካም ነገር የሚያለማ፤ ሰው ሆኖ ከተፈጠረው በላይ ቅዱስ የሆነ ጓደኛ — ጓደኛ —- ጓደኛ  — መጸሐፍ ብቻ ነው ይሉናል። መጸሐፍት Complain ቅሬታ/ አቤቱታ/ ክስ/ ምሬት/ ስሞታ የማያቀርብ ግን መምህራዊ ጓደኛ ነው ይሉናል።
የአዎንታዊ መጸሐፍ ንጽህና ጓደኝነት ሀሜተኛ አለመሆኑን፤ ሴረኛ አለመሆኑን፤ ሸረኛ አለመሆኑን፤ መንፈሳችን የማያቆስል ስለመሆኑ፤ ሥነ – ልቦናዊ ሞራላችን የማይዳፈር ስለመሆኑ ውለታውን በማድረግ፤ በመሆን አቅም ብቻ የቤት ሥራ የሚሰጥ ስለመሆኑ ነው የሚነግሩን። በትችት ላይ የማይጠመድ ስለመሆኑ ነው የነገሩን። ውለታ ያላደረግነለት ባለውለታ እንደገናም ላደረገልን ውለታ የመልስ መልስ ውለታ የማይጠይቀን ንዑድ ጓደኛ – መጸሐፍ ነው ይሉናል። ውለታ ሰጪ ግን ውለታ የማይቀበል፤ ቅብሎሹን በትውልድ ድርሻ ማዬት የጠማው፤ የራበው – መጸሐፍ።
ከዚህ ላይ „አድማጭነትን“ አንስተዋል። በንግግር ጥበብ ውስጥ አምስት ክፈለ ዋና አካላት አሉት ጥበበ – ንግግር። የእያንዳንዳቸው ልጆች እና የልጅ ልጆቻቸው እንደ ተጠበቀ ሆኖ። ተናጋሪ፤ አድማጭ፤ ንግግር፤ ውይይት፤ ግብረ ምላሽ  በዚህ የንግግራቸው ማዕቀፍ ውስጥ መጸሐፍ ተናጋሪ፤ አድማጭ፤ አወያይ በአምክንዮ ሞጋች ችሎትም አድርገው ነው ያቀረቡት። ስለዚህ መጸሐፍ የቀረው ነገር ሰው መሆን መቻል ብቻ ነው፤ እንጂ ሰውን በመፍጠር፤ ሰብዕናን በማዘጋጀት፤ ነፍስን በማደራጀት፤ ሥነ – ህይወትን በመምራት፤ ሥነ – ኑሮን በማስተዳደር፤ ሥነ – ምናብን በማቀድ፤ በመተግበር እረገድ የህሊና ልዩ አቅም መሆኑን ነው ያመሳጡሩልን። ከሁሉ በላይ መጸሐፍት በቀለኛ አይደሉም ነው የሚሉን። በዚህ ውስጥ በቀለኝነት ለሳቸው ከጥጋቸው አንደይደርስ ግዝት እናደለበት እናያለን። ሰዎች ናቸው የመጸሐፍትን ተፈጥሮ ለበቀል መሳሪያነት የሚጠቀሙበት እንጂ መጸሐፍት ጸሐፊዎች ሰውኛ ከሆኑ ከበቀል በእጅጉ ርቀው በተፈጥሮ መንፈሳዊ መልካም ነገሮች ተኮር አድርገው ነው የሚጽፏቸው – አብዛኞቹ።
ማከያ
መጸሐፍ በስደት ሐገር የናፍቆት ማወራረጃ ጽዋ ነው። ጸበለ ጻዲቅ ነው። ልዩ አጽናኝም ነው እንደ ቤተ አምልኮ፤ ቤተ – ጸሎት፤ ቤተ – ሐሤት  ነው –  ለእኔ። ቤተዘመድ። ከመጸሐፍት ጋር የብቻ መነጋገርን ልቅና ይታያል። ይህ ብቻ መናገር ራሱን የቻለ ፍልስፍና ስለሆነ ዝርዝሩን አልሄድበትም። ለመነሻ ግን ብቻውን ሰው ሲናገር ጠቀሜታ አለው። መጸሐፍት ለእኔ ሰው መሆኔን የሰጠኝ ነው። ቀርፆኛል። የተማሪነት ሆነ የሥራ ጊዜዬ ሙሉውን ማለት የምችለው መጸሐፍ በማንበብ ነበር ያለፈው። ለዚህም ወላጅ አባቴን አባይን አመሰግነዋለሁ። ነፍስኑ ይማርልኝ። አሜን! ከእናቴ ወደ አባቴ ቤት ት/ቤት ሲዘጋ ስሄድ አበይ ከመምህርንቱ በተጨማሪ የቤተ መጸሐፍት ሰው ስለነበር 7 ዓመቴ ላይ ነው ማንበብን ያስጀመረኝ። ይህም ብቻ አይደለም። ትልቅ መዝገብ ገዝቶ በዛ ላይ የደራሲውን ሥም፤ የተጻፈበትን ዘመን፤ አሳታሚውን ድርጀት፤ እርእስ ፍሬ ነገር ወይንም ጭብጡን እና ውበት ያላቸውን አባባሎች ለቅሜ እንድይዝ ያደርግ ነበር። ስለሆነም መጀመሪያ ምልክት እያደረግሁ አነባለሁ፤ ስደግመው ማስተዋሻ እይዛለሁ። እያጠናሁት ነበር እማነበው። ሌላው መጸሐፉን አንብቤ ሳበቃ አጭር ጥቅል ሃሳቡን ስተርክለት ቁጭ ብሎ ያደምጠኝ ነበር። ከሞተ በኋላ ነው ጸሐፊ የሆንኩት። ብቻ አብይ እኔን ሰጠኝ። ሃይማኖታዊ መንፈስን አያቴ መላክብርሃናት፤ ፖለቲካ ህይወቴን ደግሞ ጓድ ገ/ መድህን በርጋ። አበይ ይህም ብቻ አይደለም ከጠረጴዛ ላይ አቁሞ እንዳነብ ያደርገኝ ነበር። ሳነብ የቃና መግራትንም አክሎ ነበር ያስተማረኝ። በዚህ ውስጥ ተናጋሪነትን፤ ድፍረትን፤ በራስ መተማመንን፤ ፍሬ ነገሮችን አትኩሮት እንዲኖረኝ አድርጓል። በውስጤ ተቋም ፈጥሯል፤ ስለምን እናቱ እሙሃዬ ከመወለዴ በፊት ህልም አልማ „ታረኪቱ“ የሚል ስም ስላወጣችልኝ ብቻ ሳይሆን እሱም የቤት ሠራ እዬሰጠኝ ፈትሾኛል። ህሊናዬን እንደ ሌሎች ልጆቹ አያይውም ነበር። አክስቶቼ እንደነገሩኝ አበይ የእኔን አንጎል በሚመለከት ተናጠላዊ ልዩ ህልምና  ዕይታ ነበረው። ግን ምን ይሆናል፤ የልጁ ህይወት በመሰናክል ብዛት የታጠረ እሾኽና አሜኬላ የበዛበት ግን ጽናትን የዋጠ ሆነ።
የመከራ መፍቻነት።
„ብዙ ጊዜ በመከራ ወቅት እንድንሸጋገር በብዙ የረዱን መጸሐፍቶች የእናንተ የሥራ ውጤቶች ናቸውና ዕውቀት ብቻ ሳይሆን፤ ጥበብ ብቻ ሳይሆን፤ በጓደኝነትም ብዙዎቻችን ልንላመዳቸው የሚገቡን በጣም ጠቃሚ ሪሶርስ ነገር፤ ግን ልክ እንደ ውሃ እና አዬር የረከሰ ሪሶርስ ነው። ውሃ ሰው ሳይጠጣ ለጥቂት ቀናት መቆየት ይችላል። ግን ለዘለዓለም መኖር አይችልም። አዬር ደግሞ ሳይስብ ለሰዓታት መቆዬት አይችልም። ሁለቱ ርካሽ የማይገዙ ሃብቶች ሰው ለሞባይሉ የሚያደርገውን ጥንቃቄ ያህል እንኳን አይጠነቀቅላቸውም። ስለረከሱ አንፐርታን ስለመሆናቸው እንብዛም ሰው ባልዩ አያደርጋቸውም፤ መጸሐፍትም እንደዚሁ ናቸው“
ዶር. አብይ አህመድ አዎንታዊ ጸሐፍትን እናድምጥ ነው የሚሉት። ስለምን የችግር መፍቻው ያለው ከእነሱ ዘንድ እንደሆነ ነው አበክረው ነው የሚገልጹት። በዚህ አመክንዮቸው ለመጸሐፍት የሰጡት ልቅና ነፍስ አሳዳሪር፤ ነፍስ አኗሪ፤ ነፍስን አስቀጣይ አድርገው ልክ እንደ ንጹህ አዬር እና ውሃ የሚተከካል አቅም ያላቸው መሆነቸውን ነው። መጸሐፍትን አንግሠን አንድናያቸው ነው የሚመክሩን። እንድንጠነቀቅላቸውም። በዚህ ውስጥ ለአዎንታዊ ጸሐፍትም የሰጠናቸው አክብሮት ከሰው ሠራሹ ሞባይል የምንሰጠውን ዋጋ ያክል እንኳን አልሆነም በማለት ነው ራሳቸውን ጨምረው የሚወቅሱት። የትኛው የፖሊቲካ ሊሂቅ ነው እራሱን ለመውቀስ የሚደፈረው። ሁልጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ሰረገላ ላይ እንዳለ ብጽዕና ነው ራሱን የሚያዬው። ሌላውን ሲያብጠለጥል በራሱ ውስጥ ያ የሚብጠለጠለው ነገር እንዳለ ማዬት ቀርቶ ማወቅ የተሳነ ልሳን ነው የሚደመጠው። መጸሐፍት የጥበብ፤ የዕወቅት መሰረትነታቸው ተፈጥሯዊነት ከሰዋዊነት ውጪ፤ ግን እንደ ሰዋዊነት የተሰጣቸው ድርሻ እንዳላቸው ነው በመንፈሳችን ውስጥ ሃዲድ የዘረጉልን። ለመሆኑ የወያኔ ሃርነት የአሁኖቹ ፖለቲ ቢሮ አባላት እነ ፈርዖኒት ወ/ሮ ፈትለወረቅ ገ/ እግዚአብሄር አንድ የመጸሐፍ ርዕስ መጥቀስ ይችሉ ይሆን? አንበበው የጨረሱትስ? ለነገሩ እኔም ዕብን ነኝ ስለጫካ አፈጣጠር እንኳን በውስጡ ከመኖር እንዴት እንደ እንሰሳ ቀስ እያደረገ እንደቀየራቸው አያውቁትም። አራዊትነቱ፤ ጭካኔውን፤ ዘመንን የማዬት አቅሙ ወናነት የመጣው እኮ ከዚህ ሰብዕና ነው።
የጥሞና አብሮ አደግነት።
„ … በኦርቶዶክስ ሃይማኖት አባቶች ጥዋት … ጥዋት እዬተነሱ ዳዊት መድገም፤ የተለመደ ባህል ነበር። ወንጌልን ለማሰራጨት ብቻ ሳይሆን፤ እምነትን ለማሰራጨት ብቻ ሳይሆን፤ ጥዋት ተነስቶ ቀድሞ ዳዊት መድገም ባህል ነበር። ለአሁኖቹ አገልጋዮች አንድዛ መሆን እርግጠኛ አይደለሁም። በልጅነት ግን ይህን አስተውል ነበር። በእስልምና እምነትም ይህ ባህል ነበር። ጥዋት …ጥዋት ተነስቶ ቁራዕን ይቀራል።“ ቃለ ህይወት ያሰማልን። መንግሥተ ሰማያትን ያውርስልን። የተባረኩ! ምሩቅ – መረቅ!
አዬህ የቤተ መንግሥቱ ባለሙሉ ሥልጣን ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ እኒህ ማስተዋልን የሆኑት የፖለቲካ ሊሂቅ በምን አይነት ግንዛቤ ጨልፍህ ጸጋቸውን እንደ ጋልብከው አዬኽውን? ልጅ ሆነው የልጅነት ጊዜያቸውን ያሳለፉት እንደዚህ አይነት የኢትዮጵያን ልዩ ውበት ምንጫትን በጥሞና በመርምርና በመመሰጥ ውስጥ ነበር። አንተ ግን „ደራሽ ኢትዮጵያዊነት፤ ጎርፍ ያመጣው ኢትዮጵያዊነት“ እያልክ ነበር የተሳለቅክበት። እሳቸው ግን የኢትዮጵያን ጥልቅ የማንነት ተዋፆን ዕንቁነት፤ ርቁቅ ቀለማም የህሊና ብቃት ያዬበት ተመክሮ አጋ ሳይለዩ፤ ክትር ሳያበጁለት፤ ደንበር ሳይሰሩለት በፍጽምና አትኩሮት የኢትዮጵያዊነትን ክህሎት አጣጥመው ጠጥተውታል። ኢትዮጵያዊነትን ተመግበውታል። ኢትዮጵያዊነትን የውስጣቸው አዬር አድርገውታል ልክ እንደ ኦክስጂን። ኢትዮጵያዊነትን መስጥረውታል። አንተ የምትለን ደግሞ ደመነፍሱ የጫካ ተመክሮ ባሰከረው አረመኒያዊ ዶክትሬን፤ „ኢትዮጵያንና ኦርቶዶክስን ከሥሩ ነቅነዋል“ በሚለው ባለዛር ፎካሪው የተጋሩ ማህበር በህሊናቸው የጨመረው አሰር፤ ያልጠራ ጉሽ አድርገህ ትነግረለህ። የኢትዮጵያ ህዝብም ይህን የልግጫ ስበከት ሰረገላህን ተከትሎ ገደል እንዲገባ፤ በጥላቻና በልዩነት ተነሳስቶ የራሱን ጸጋ፤ የራሱን መክሊት፤ የራሱን ፈላስፋ፤ የራሱን ልጅ በቅንነት አንዳይከተል፤ የእኔ እንዳይል ነው ቀበቶህን ታጥቀህ ሃሳዊ መሲህነትህን ጋልቡት የምትለው።
የተዋህዶ ልጆች በማለት ውስጥ ሳይሆን በመኖር ውስጥ የፈጣሪ አማላካችን መልዕክተኞችን፤ ሐዋርያትን፤ ጻድቃን ሰማዕታትን፤ ወንጌላውያትን፤ አክብሮ የሚነሳ፤ የልብ አማላክ ዳዊትን ምስካብ በውስጡ ያስቀመጠ፤ የዕለታዊ ቅዳሴ ምስሶነቱን ያመሳጠረውን፤ራሱም ምስባክ የሆነውን የቅን ወንድማችን የእኛን የዶር. አብይ አህመድን ቅዱስ መንፈስ ማግለል ማለት እምነታችን፤ ማተባችን መበጠስ መሆኑን በማያወላዳ አኳኋን አስረግጬ ልነግርህ እሻለሁ። በንባብ ህይወት ውስጥ ቅድስና፤ ሐዋሪያዊነት፤ ነብይነት፤ ንጽህና፤ ፍልስፍና፤ ድህነት፤ ምህረት የአዎንታዊ ስብከት የመንፈስ ባለሃብትነት የኢትዮጵያ አንጡራ የራሷ የሆነ ብቸኛ ሃብቷ ነው። ሃይማኖታዊ ቀኖናዋ፤ ሃይማኗታዊ ዶጎማው መሰረቱ ይሄው ነው። በእስልምናም እንዲሁ። አንተ ጋዜጠኛውን ማለቴ ነው ከዚህ በሳል ፍልስፍና ውጪ በመሆንኽ ብቻህን፤ እርቃንህን እንደምትቆም እርግጠኛ ነኝ። ያ አድማጭህ 20 ሺህ በዚህ አመክንዮ ብቻ ጥሎኽ ብን እንደሚል እርግጠኛ ነኝ። አሁን አንተ ከባህር የወጣህ አሳ ነህ። ድርጀትህንም አስደፍረሃዋል። ልኩን፣ አቅሙን ሚዛን ውስጥ አንዲቀመጥ ብልህ መንፈሶች ችሎት ላይ ይቀመጣሉ። በተለይም ተዋህዶዎች። ከሃይማኖታችን በላይ ምንም ነገር የለም። ሃይማኖታችን አክብሮ፤ አልቆ የተነሳውን ነፍሳችን ተዳፈረዋል። ህግ ተላልፈሃል።
ናሙናዊነት።
„ያ ..  የማንበብ ባህል በገጠር ውስጥ የቄስ ት/ቤት፤ መድረሳ ት/ ቤት የተባለ ልጆች እዬተማሩ እያነበቡ ስለደራስያን እያወቁ እዬጓጉም እንዲአድጉ ያደርጋቸዋል“
ይሄ ናሙናዊነት ከመሠረቱ የተነሳ ሃሳብ ያለው፤ መነሻውን ያልሳተ፤ እሱነቱን በመሆን ውስጥ ያመሳጠረ፤ እራሱን ለማድመጥ የፈቀደ፤ ምንጩን ያከበረ፤ ውስጡን የተመለከተ፤ በውስጡ ያለውን ፍሬ ነገር የፈተሸ፤ የትውልድን ጥበባዊ ሰንሰለት ያነበበ፤ የተረጎመ ያመሳጠረ የእድምታ ዜማዊ ሚስጢር ነው። ትውፊት። ጀርመን የመዳህኒት ፈላስፋ ናት። ፈላስፋነቷ ምንጩ „መጸሐፈ ፈውስ ነው“ ቻይናውያንም በባህላዊ መዳህኒት የታወቁ ናቸው። ነገር ግን ኢትጵውያን ልቅናውን ቀድመው ተጠብበውበታል። በጹሑፍም አስቀምጠውታል። ጎንደር የዛሬን ባለውቅም ወላጆቻችን በተለይ እናቶች ባተኩስን ቁጥር ሃኪም ቤት አይሮጡም። ወረድ ብለው ቆረጥረጥ አድርገው፤ ቆፈር አድረገው በጣታቸው ለክተው የምንቆረጥማቸው ነገሮች ነበሩ። ወዲያው የሚፈውሱ። አሁን እኔ ልጅ እያለሁኝ ነስር ነበረብኝ፤ መገኛ የሚባል ነበረብኝ፤ ልብ ድካም ነበረብኝ፤ ኩንታሮት ነበረብኝ ግን ቤተሰቦቼ አድነውኛል። ከዚህ ከመጣሁም ሃይለኛ አስም ያዘኝ። የደረቱ – ከባዱ። አሁን የለብኝም። በለመድኩት መንገድ እንደጀመረኝ ታገልኩት ተፈወስኩኝ። ይህ ከዬት መጣ? ከዛ ረቂቅ የኢትዮጵያዊነት ተፈጥሮ። ሃብታችን ተዝቆ አያልቅም። ዕድሉን ሆነ አጋጣሚ ቢገኝ ስንትና ስንት በተሄደ። ለዚህ ተፈጥሮ አክብሮት ብቻ ሳይሆን ዘብ እንቁም ነው የሚሉት ሊሂቁ፤ ወጣቱ ፖለቲከኛ።
የህሊና ድርጁነት ድርቀት ምንጩ … በዶር. አብይ አህምድ የዕድምታ አስኳል።
„በአሁኑ ጊዜ ዕውቀት ደርጅቶ የሚቀርብበት አንባቢ እያገኘ ስላልሆነ፤ በከፍተኛ ደረጃ የሃብት እጦት ብቻ ሳይሆን የጭንቅላት ድርቀትም እያገጠመን ነው“
እሺ! የቤተ – መንግሥቱ ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ … ጉድህን በዚህ አገለለጽ እዬው። ማስተዋሉ ካልተነፈገህ? ከዚህ ጡንቻዊ አመክንዮ ልታመልጥ ከቶውንም አይቻልህም። መማር ብቻውን ግብ አይደለም። መማር ማማር የሚሆነው ውስጡን መዝኖ መነሳት ሲችል ብቻ ነው። ቅን መሆን ሲችል ብቻ ነው። አዎንታዊነትን ማበረታታ፤ ማገዝ ሲችል ብቻ ነው።
„   ጭንቅላት ትልቁን ኢነርጂ ከምንመገበው 25% ገደማ ኦክስጂን የሚወስደው ጭንቅላት ነው። የምንመገበው ምግብ አብዛኛው የሚሄደው ወደ ጭንቅላታችን ነው። የእግራችነን በብዙ ዕጥፍ ጉልበት የሚወስደው ጭንቅላት የሚመግበው መጋቢ ስላጣ ባዶ ሆኖ መኖር የግድ ሆኖታል ኢትዮጵያ ውስጥ።“
ፖለቲካ ሊሂቅ እንዲህ በጥልቀት ችግሮቹን ያጠናል፤ ይመራመራል፤ ይህን ፍልስፍና፤ ይህን የነጠረ ኢትዮጵያዊ ሃብት ባልተወለደ አንጀቱ በሳንጃ የቆራረጠው ጋዜጠኛው ማስረሻ አለሙ ከቶ ከዬት ይመደብ? ኢትዮጵያ ዋና ቢሮዋን ወይንም ማዘዣ ጣቢያዋን እጬጌ ጭንቅላትን ባዶ አደርጋ ህልመኛ መሆኗን ነው ዶር. አብይ አህመድ የሚነግሩን። እርስዎን የፈጣረ ማህጸን ከቶ አንድምን ያለ ነው? ተመስገን!
የኢትዮጵያ ሰማያዊ ፈርማሲስትነት።
„ቅድም ኮነሬል እንዳሉት የህንዱ ታሪክ ዛሬ ጁቡቲ አሁን 45 ዲግሪ ሴልሸዬስ ነው። ሙቀቱ። ናይሮቢ ብትሄዱ በጣም ይሞቃል። ካርቱም ይሞቃል። ተፈጥሮ እንደዚህ አድሎ የሰጠንን ሐገር ተገንዝበን ተጠቅመን፤ ለመለወጥ ያልቻልነበት ዋንኛ ሚስጢር ጥበብን የመፈለግ፤ ጥበብ Wisdom የመፈለግ፤ ዕወቀትን የመፈለግ ዝንባሌኛችን ፍራንክ ከመለቃቀም ጋር ሲነጻጸር፤ በእጅጉ የተለያዬ በመሆኑ ነው“
አቤቱ¡ ጋዜጠኛ ማስረሻ ዓለሙ ጉድህ ዝግጅትህ እንዲህ ነው የተዘርከረከው። በምን ትወታትፈው ይሆን? በዞግ? በሃይማኖት ልዩነት? ወይንስ በአምልኮተ የግራ ጣዖት?
ናፍቆቶቼ የኔዎቹ ቅኖች —- ቀደም ብዬ እንደ ገልጽኩት አባቶቻችን ጥበብ ነበሩ Wisdom ፈጣሪዎች ነበሩ። ያን ድጠን ነው „ኢትዮጵያ ገና ያልተሰራች ሀገር ናት የምንለው“ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ደግሞ „እኛ ሠራናት“ ይለናል። ግን በፍጹም ሁኔታ በራሳችን ተኮር የሆነ ጥናት ብንጀመር፤ ተጠቃሚ ለመሆን ብንፈቅድ መሰረትነቱን በመሰረት ማስያዝ ይቻላል። ሌላው ቀርቶ ዶር. አብይ አህመድ እንዳሉት ኢትዮጵያ ሐገራችን ካለምንም የመዳህኒት እግዛ የአዬር ጸባዮዋ ብቻ እንደ አንድ የፈርማሲ መዳህኒት ክኒን ሊታዘዝ የሚገባው ነው። የኢትዮጵያን ልዩ ጸጋ ዛሬ የኦህዲድ ምርጠኛ ስለሆኑ አይደለም፤ ይህ የዛሬ ዓመት ጥቅምት ላይ ያደረጉት ንግግር ነው። በሀገራቸው በኢትዮጵያ ጥልቅ ፍቅር እውነተኛነት ተንከርፎ፤ ተገልብጦ፤ ወይንም በትርፍነት ተለብጦ ወይንም እንደ ቁሮ እንጨት ተቆርሮ ሳይሆን ሁለመናዊ ብቃቷን፤ ጥልቅነቷን፤ ተፈጥሮ የሰጣት ስለመሆኑ ውስጣቸው አድርገው ወደውት፤ የእኔ ብለውት በደማቸው ውስጥ እንዳሻው እንዲዘዋወር ፈቅደውት ነው። አዎን ልዕልት ኢትዮጵያ አዬሯ ብቻውን ፈዋሽ ነው። የማይከፈልበት፤ ደጅ የማይጠናበት፤ ፕሮቶክል የማያግደው የተመረቀችበት የፍጽምናዋ ዕዕማደ ሚስጢር የቅድስት ሐገር ኢትዮጵያ ብቸኛ ሰማያዊ ጸጋ። ክረምቱ፤ በጋው፤ በልጉ፤ ጸደዩ ተመጥኖ በልክ የተቀመመ ቅዱስ መዳህኒት። ኢትዮጵያ በተፈጥሯዋ ፈርማሲስት ናት። ግን ኬሜያዊ ያለሆነ ተፈጥሯዊና ረድኤቷ ነው። ቅመሙ ምርቃት። የማን?  የሰማይ እና የምድር ንጉሥ የእዬሱስ ክርስቶስ ወይንም የአላህ ጸጋና አዱኛን በገፍ ነው የሰጣት/ ያደላት/ ያስቻላት። የተፈቀደላት ናት። ይህን ወደ ጠቃሚ ነገር መሻጋገር፤ ይህን ወደ ብልጹግ ደረጃ እንዲያቀና ቅን ህሊና፤ ብቁ ህሊና ጋር ማዋደድ ተስኖን ነውን ኮረጃችን ይዘን የምነለምነው፤ ለወንበራችንም ናፍቆትም ዓመት ይዞ እስከ ዓመት ለይለፍ ነጮችን ደጅ የምንጠናው። የተሻለ የመንገድ ማህንዲስ ብቅ ሲል ደግሞ በወበራ መዶሻ …
„እንደ ሐገር ዕውቀት የማንሻ ከሆነ፤ እንደ ሐገር ዕውቀትን የማንፈልግ ከሆነ፤ ያንንም ኢንከሬጄ እማናደርግ ከሆነ፤ ሄዶ ሄዶ ይሄ ጥቁር ጠበሳ የሆነው ታሪካችን፤ ተከታይ መሆኑ አይቀሬ ነው“ ረሃብተኝነታችን፤ ኋላቀርነታችን።
በዚህ ውስጥ ብዙ ነገሮችን ማንሳት ይቻላል። የዶር. አብይ አህመድ አገላለጽ ተፈቅዶላቸው ከህትምታቸው በኋዋላ፤ ገብያ ላይ ሆነው የመግዛት ሆነ፤ ከተገዙ በኋዋላም የማንበብ አቅም አለመኖርን ነው የሚገልጹት። ሌላም ውሃ ያዘለ ተራራ አለ፤ ለህትምት ቀርበው በሳንስሩድ የሚቀሩ፤ እንዲሁም ውጪ ሀገር የሳንሱርድ እግዳ የሌለባቸው ታትመው ግን ለህዝብ እንዳይቀርቡ፤ ከህዝብ ጋር እንዳይወያዩ የታጋዱ የህሊና ምርቶች ወይንም ሰብሎችም አሉ። ጭራሽ እርእሳቸውም፤ ሽፋናቸውም የማይታወቅ። ስለምን? የማንፌስቶ ማህበርተኝነት ባለመፍቅድ ምክንያት። ጸሐፍት የአንድ ድርጅት የማንፌስቶ ሎሌዎች አይደሉም። የራሳቸው በህሊናቸው የጻፉት ማንፌስቶ አላቸው። የእኔ የሚሉት ዓላማና ግብ አላቸው። የተደራጁም ናቸው በመንፈስ ማህበር። ምናብ፤ ብራና፣ ብዕርና ማያያጃ ወይንም ማመሳከሪያ። ጸሐፍት የሚያሰኛቸውም በዚህ ንጽህና እና ቅድስና ውስጥ በነፃነት ለመኖር መፍቀዳቸው ነው። መኖራቸው ፈተኛ ገደል ሊበዛበት ይችላል፤ ግን ወደውት እና ተምረውበት፤ እንዲሁም እንደ ተቋም አይተውት ስለሆነ ሰናያቸው ነው። ሰው ፍስሃውን ከምን ይገኛል ቢባል በሚፈልገው ህይወቱ ውስጥ ለመኖር በሚወስነው የብልህነት አቅምና አቋሙ ውስጥ ነው። እርግጥ ነው ፖስተር ተለጥፎ አያለሁ። ቀላማም። ግን አሳታፊ አይደለም ቃልቲ፤ ዝዋይ፤ ካሉት እስረኞች በላይ ጉድጓድ ውስጥ የተቀበረ መንፈስ ነው። ጸሐፍትን የበላይና የበታች አድርገህ፤ ወይንም አቅርበህንና አርቀህ ትውልድ አይገነባም። ምክንያቱም ሚዛኑ የድርቅ ሰለባ ስለሆነ። ተዛነፍ ነው የሚሆነው። ጋድም። ኢትዮጵያንም በጋድሞሽ የማዬት ኩፍኝ ነው። ጸሐፍት ጥበባቸው፤ ሃሳባቸው፤ የህሊና አጀንዳቸው ለህዝብ አንዳይደርስ፤ የተጣለባቸው እግዳ ከህሊና ድርቀት የመጣ ነው። ለዛሬም አይበጅ፤ ለነገም አይበጅም። ይሄን ተሸክሞ መርሂተ መንግሥት መሆን ደግሞ በፍጹም አይቻልም።
በዚህ ላይ ደፍርን ልንሠራበት ይገባል። መስዋዕትነቱ ከጠበቅነው በላይ ከባድ ነው። ግን መጋፈጥ ያስፈልጋል። አሽኳኳነት ትውልድን አላደነም። ለማንም ለምንም ሳይባል ትውልዱን በማዳን የቅድሚ የጦር ግንባሩ ረድፈኞች ጸሐፈት ልንሆን ይገባል። ትውልዱን በፖለቲካ ማንፌሰቶ አስር ቤት ከዝነው፤ ትውልዱ ከጸሐፍት ሊያገኝ የሚገባውን የህሊና ስንቅ የተረኮኮመ፤ የተኮረኮደ፤ ማጣያፊያ ያጠረው፤ በራሱ ውስጥ ለመኖር ያልደፈረ ሃሳብን ፈሪ ተንበርካኪ እያደረጉት ነው። ይህን የምለው በዝም ብሎ አይደለም። የተሸከምነው ጉድና ገመና አለና። ትናንት ብዕራችን ሳይደክም የተሟገትንለት ነፍስ ዛሬ የዛ ሰለባ ሆኖ በማየታችንም ጭምር ነው። በዚህ ውስጥ ሴቶች ስለመኖራቸው፤ ህሊናቸው የሚያስብ ስለመሆኑ ከቁጥር ውጪ ናቸው። እኔ ለዓለም ዐቀፉ ማህበረሰብ ስጽፍ ጨላማ ውስጥ ቁጭ ብዬ ነው ውስጤን እምልክላችሁ ብዬ ነው መልዕክቴን እምጽፈው። ያቺ በጨለማ ውስጥ እንድንኖር ከሚፈልጉት የወንዶች የግራ ዓለም ፖለቲከኞች ጋር ማህበር የገጠመቸው ነፍስም እሷንም ነፃ የማውጣት ትውልዳዊ ድርሻ ስላለብኝ። እሷ ከእግር ብረት ነፃ ነኝ ብላ ይሆናል። አሁን ግን ያላወቀቸው እና ያልተረዳቸው ነገር እስረኛ መሆኗን ነው። „ከድጡ ወደ ማጡ“ እንዲሉ ስለዚህ ፈቅዳና ወዳ መንፈሷን ላሰረቸውም አንስት እህቴ እሟገትላትአለሁ። ተልዕኮዬ ስለሆነ። ወደ እምናፍቀው ዓለም እስክሄድ …
የጸሐፍት ነፃነት ድንጋጌ።
„ይህን ችግር ለማቅረፍ ደራስያን፤ በሰላ ብዕራችሁ ትውልድን  Generationማስተማር፤ የማያውቁ ግን የሚያውቁ  ሰዎች ካሉ እነሱንም መሞገት፤ የእናንተ ትልቅ ሃላፊነት መስሎ ይሰማኛል።“
„ በእናንተ ብዕር ውስጥ ፖለቲካ ሊዳሰስ ይገባል፤ ሃይማኖት ሊዳሰስ ይገባዋል፤ ግብረ ገብንት ሊዳስስ ይገባዋል። በዚህ ሂደት ውስጥ ትውልድ የማዳን፤ እና ይህችን ሐገር የማስቀጠል ሃላፊነት ከማንም በላይ በሚጽፉ፤ ከምንም በላይ ተፈጥሮን ማዬት ማስተዋል፤ ጥበብን ማዬት በሚችሉ ሰዎች፤ ሃላፊነት የወደቀ መሆኑን እንድትገነዘቡ፤ ማሳስብ እፈልጋለሁ“
በዬት አልፈን? በዬት ተሻግረን? አንዴት ብለን? በተለይ ሴት? በተለይም አማራ ሴት? በተለይ ብረት መዝጊያ የሆነ ዘመድ የሌላት ባተሌ አንስት? በተለይ የፖለቲካ ማንፌስቶ ማህበርተኝነት ለማይፈቅድ ጸሐፍት በዬትኛው ሃዲድ? ተሰርቷል አይደለም ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ከዛም ላለፈ የሚሆን የመነሻ ጭብጥ – የእውነት – የመሆን – የትውልድ ድርሻና ሃላፊነትን በቅጡ ያስተዋለ የክንውን ቋት አለ። ግን እንዴት? በዬትኛው መሰላል? ጨለማ። ድቅድቅ። ጥቅጥቅ። ይሄን ገማና ተሽክመን ነው „ፍትህ የሰፈነባት፤ ሁሉንም እኩል የምታሳትፍ ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያ“ ህልም የተቋጠረው። ባልታዬው፤ መሰረታዊ መነሻ በሌለው፤ ከጭብጡ ሊነሳ ላልፈቀደ፤ ላልደፈረም፤ ንፋስ ላይ ሠረገላውን ላሰማራ ሃሳባዊ የምናብ ቅዝፈት ሰለባ የምንሆነው፤ ጸሐፍትን ግዞት ስለተፈረዳባቸው ነው። ሀ ሲጀመር ሁ ይቀጥላልን? ሀ ላይ አይደለንም። መሪነት ሁሉንም አምክንዮ ከጥቃቅኗ አስከ ሰማይ ጠቀሱ፤ ከዳካማው አስከ ጉልበታሙ ክስተት፤ ከእኔ ቢጤዋ ጨርቅ ለባሽ እሰከ ቬሎ/ ካባ ለባሿ አንዲህ በተጠና ከውስጥ ሆነ ባደመጠ፤ የእኔ ባለ መክሊት ይጸነሳል። አቅም፤ ጉልበት፤ መንፈስ ብኩነቱን የሚቆጣጠር ናሙና ላይ አንቴናችነን ማሰራት አለበት። የአቅም ብክነት ሰለባ መሆን አይገባንም።
የህሊና ውደቀት ምንጭ።
„ኢትዮጵያ ውስጥ ወጣቶች፤ ለማንበብ፤ ለማወቅ የሚያደርጉት ጥረት የሳሳበት አንዱ ምክንያት branding ነው። ጸሑፍ መጻፍ ደራስያን አሉ። ሃሳብ አፍላቂዎች አሉ። የፈለቀውን ሃሳብ ከወረቀት ጋር የሚያዋህዱ ሰዎች አሉ። ድርስት ሆኖ ከወጣ በኋዋላ የሚያሳትሙ አሉ። የሚያከፋፍሉ አሉ። መልሶም የሚያነቡ አሉ። ይህ ሰንሰለት ነው። ከዚህ ውስጥ አንዱ ሲበጠስ፤ ጠቅላላ ኢንደስትሪው የሚወድቀው። ይህ ደግሞ እንዳይሆን ቅድም እንዳልኩት አንዱ ደግሞ የbranding ችግር ነው።“
ይህን ሃሳብ እኔ የተረዳሁት አቅምን ተከታታይ የማድረግ አቅም አንሶናል። ተከታታይነቱ በህሊናችን ውስጥ ጥሪት ፈጥሮ መንገድ እንዲሆነን አልፈቀድንለትም። በተጠቃሚዎች አዕምሮ ውስጥ የአጠቃቀም አደረጃጃት፤ አመራር፤ አያያዝ፤ አፈጻጻም ሥነ – ጥበባዊ አስተዳደር ይጎደለናል፤ አንዱ ቢበጥስ ከዚህ የእውቀት ዘርፍ ልናገኝ የሚገባውን የመንፈስ ጠቀሜታ ድርቅ  ይመታዋል። መንዳችንም በጨለማ መጓዝ ይሆናል። የጨለማ ጉዞ ደግሞ ከምንም የማይታደግ ግን ድካመ ገብ እና አስልቺ ይሆናል። ተጠቃሚነታችን ተጠቃሚ አላደርግነውም። ገፍተነዋል። እንደዚህ ነው እኔ ይህን ገለጻ ያዬሁት „branding“ አንዳለ መውሰዱን መረጥኩት። የቃሉን አግባብ በትርጉሙ ልሂድ ብለው ንግዳዊ ፍሰቱ ያመዘንብኛል። ይህም ማለት የንግድ ስያሜውን እንደ  ተጠበቀ ሆኖ ከላይ ካነሱት ጉልበተማም አቅም ጋር ተዋራራሽ ሊሆንልኝ የቻለው አዕምሮን በማሰፋት፤ ዕውቀትን በመሸመትና በማቅናት መካከል ያለውን መስተገባራዊ ህይወት የመተንፈስ ያህል እንዳዬው ነው የፈቀድኩት። እርግጥ ነው የፀሐፍት የዐዕምሮ ምርት ከሁሉም የላቅ የገሃዱም የመንፈሳውውም ዓለም የሚያገናኝ ርቁቅ ጢስም አልባው ኢንደስትሪ ነው።
ሂሳዊነት እና ቅንነት። ቅንነቱና አስተማሪነቱ። መሆን ስለሚጋባው፤
„ጸሐፊዎች አንዱ ማክበሪያ መንግዳችሁ ጸሐፊዎችን ማክብር ነው። የወጣውን  ጸሁፍ ራሽናል ሆኖ ክሪቲሳያዝድ ማድረግ የሙያ ግዴታ ነው። ግን መጸሐፉን በራሱ እዬደነቅን መሆን አለበት። መጸሐፍ የሚደነቅ ነገር መሆኑን እዬተናገርን፤ ማንበብ የሚያስወድስ መሆኑን እዬተናገርን፤ እዛ ውስጥ ደግሞ የሚታዩ ስንክሳሮችን፤ ነቅሶ ማውጣት እና ማረም ተገቢ ነው። ነገር ግን በጋዜጦቻችን የሚታዬው ጸሐፍት ሲሞጋገሱ፤ ሲወዳደሱ ሳይሆን፤ ሲወቃቀሱ ሲረጋገሙ ነው። ነገቲብ ኢንርጂ ደግሞ በራሱ የመደመር እና የማጥፋት ሃይል አለው። ስለምንዘራው ነገር፤ በቃላችን ስለምንናገረው ነገር በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል። እሱን ሰለምናጭድ መጨረሻ ላይ። በቅርቡ በተረጋገጠው የሳይንስ ውጤት የሚያመለክተው ውሃ በተደጋጋሚ ረግመው በምርምር የተረጋገጠ ነው፤ በመጨረሻ በጣም የተራራቅ የሚያስጠላ ሞሎኪውል ሲሆን በአንጻሩ የተመረቀ ወይንም የተቀደሰ/ ብለስ የተደረገ ውሃ ጠበል እንደሚባለው ሞለኪሉ ጥግጊቱ የሚያምርና የሚታይ ሆኗል። ሰው 75% ውሃ ነው። 6% አፈር ነው። 4% እሳት ነው፤ የተቀረው አዬር ነው። በውስጣችን ያለው አብዛኛው ፐርስንት ውሃ በተደጋጋሚ ከምነዘራው ክፉ ቃል የተነሳ ሞለኪሉ ካንሰር፤ ሞለኪሉ ጨጓራ፤ ሞለኪሉ ስኳር እዬሆነ ነው።“
እነሂን ንጹህ ሰው ነው እንደዛ ያብጠለጠላቸው ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ። ቋንቋቸው ወደ ውርስ ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን እየሆነ ነው። „ጥግጊት፤ ሸክኖ“ ሌላው የቅድስናን ህይወት አክብሮ የመነሳት አቅማቸው ይደንቃል። „ጸበል“ ማገናዘቢያ አቀራራባቸው ውስጣቸው ውስጥ ያለውን የአቅም ማሳ መጠን፤ ስፋት፤ ርዝመት፤ ጥልቀት እንድናይ ራዲዎሎጂ ነው ለእኔ። የፋክትም ሰው ናቸው። አክብረው የሚነሱበት አምክንዮ በውስጣችን አክብሮትን እንድናበቅል በሐዋርያነት የሚሰብክ ነው። አሉታዊነትን እጅግ የሚጸዬፉት ብቻ ሳይሆን በምድረ ኢትዮጵያ ማጥፋት ባይቻል፤ መቀነስ እንዲቻል በታታሪነት አጀንዳ አድርገው እዬሠሩበት ነው። ይህ ለሴራ ፖለቲካዊ መስምር አይምችም። ለዚህም ነው ህይወታቸው የሚያሰጋኝ። እንዳያጠፉብን።
„መደመር“  ለአሁኑ የፖለቲካ የመንፈስ ሹምሽር በሚዜነት እንደተጠቀሙበት ሸቀጥ አድርጎ ነበር የነገርን ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ። አይደለም በእሳቸው በህሊናቸው ውስጥ አንቱታን ያገኘ የንግግር ዘይቤ አናባቢያቸው ነው። ተዘውታሪ ነው። እያንዳንዱን ቃል፤ ስንኝ፤ ሐረግ ለቅኖች የህሊናቸው እልፍኝ ነው። የእልፍኙ ንጹሕ አዬር ነው „መደመር“። ከትርምሱ አለም አውጥቶ እንደ ተፈጥሮ ለመኖር የሚያስወስን የበቀለ፤ የጸደቀ መንገድ ነው „መደመር“።
እሳት አደጋውን ስለመከላከል።
„ 4% ፋዬር /እሳት፤ ገበርን እያደረገን፤ ትውልድ የማይከባበርበት፤ እማይዋደድበት፤ ነገን የማያይበት፤ ሀገር እዬሆነ ነው። ባህል፤ ወጋችን፤ ባልዩችን እዬጠፋ ነው። ይህን የማስቀጠል ግዴታ አለብን። ይህ መሆን ስላለበት ነው ዛሬ፤ በጣም አጣብቂኝ የሆነ ጊዜ ቢሆንም ይህንን ዕድል፤ ላለማጥፋት በእናንተ መካከል፤ ልገኝ የወሰንኩት።“
ቅድሚያ መሰጠት ያለበት ለትውፊታችን፤ ለዕሴቶቻችን፤ ለፍቅራዊነት መሆን ይገባዋል። ከሁሉ በላይ ወደ ራሳችን የምንመለከትመበትን አጋጣሚ ለመጠቀም ሲወስን እሳት አደጋውን መከለከል ትውልዳዊ ድርሻ ስለመሆኑ በአጽህኖት ነበር የገለጹት። ትወልድን በአዲስ አወንታዊ አብዮት ወደ ራሱ የመመለስ ታላቅ ተልዕኮ ይዘው ነው የተነሱት።
በጸሐፍት ውስጥ ያለው ዘር ጉልበታምነት።
„ከዚህ ውጪ ደራስያን ብዙ ጊዜያቸው የመከበር፤ የመደመጥ ዕድላቸው በጣም አናሳ ነው፤ በቅርቡ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት መጥተው በነበረ ጊዜ ንግግር ሲያደርጉ በአፍሪካ ማዲባ ብለው ፕ/ ማንዴላን ያነሱ ነበር፤ ሲያነሱ ስለ ትግላቸው፤ ስለፖለቲካ አመራራቸው አላነሱም፤ ማዲባ እንደዚህ ብሏል ነው ያሉት። ጹሑፋቸውን ነው ሜንሽን ያደረጉት፤ ኦባማ ጥቁር ከለርም ስለላቸው ብዙም አልገረመኝ ነበር፤ በቅርቡ የኮሪያ ፕሬዚዳንት ፓርክ ሲመጡ ኤዩ ባደረጉት ንግግር መልሰው ማዲባን ኮት አድርገዋል። ኮት ሲያደርጓቸው የእሳቸውን የአስተዳደር ሥርዓት አንዲህና አንዲያ ነው አይደለም ያሉት። በመጸሐፉ እንዲህ ብሏል ነው ያሉት። ስለዚህ ዛሬ በቂ ክፍያ ላይከፈላችሁ ይችላል፤ ላትወደሱ ትችላላችሁ፤ ሳልጠራጠር የምናገረው ግን ሁሌም ሊያስወሳ የሚችል ሥራ ጥላችሁ ታልፋላችሁ።“
ተመስገን! የናፈቀኝ ይህ አይነት የአዎንታዊነት ምናባዊ ዓለም ነበር። የጽናት፤ ብዕር ከ እስር ከእግር ብረት የሚወጣበት የምህረት ዓዋጅ። እርግጥ ነው እስረኛ የህሊና ምርቶች ቀናቸውን ጠብቀው የሚወጡበት ዕለት እንዲሰጣቸው ተንበርክኬ እጸልያለሁ። ውዳሴ ምን ሲሰራልን። ገንዘብስ ቢሆን ምንድን ነው „ገንዘብ የሃጢያት ሥር ነው“ ትውልዳዊ ድርሻ ነው – መጻፍ። ከሁሉ በላይ እያንዳንዱ ልጅ ሲወለድ መልዕክት ይዞ ስለሚወለድ ያን ነው ተግባራዊ ለማድረግ የምንጥረው፤ መመስገን፤ መከበር ካለበት ሰጩ መዳህኒዓለም አባታችን/ አላህ ብቻ ነው። እሱ የሰጠንን መልዕክት ላይ ማዕቀብ መጣሉም እኛን ሳይሆን ፈጣሪን እዬተፈታተኑት ስለመሆኑ የብዕር ሰብል አጋቾችን እግዚአብሄር አምላክ ከማንፌስቶ አምልኳቸው አውጥቶ ምህረት ያውርድላቸው ነው እኔ በግሌ እምለው።
„ይሄ ብቻ አይደልም የፓርክ ንግግር፤ ሎሬት ጸጋዬንም አስታውሷል። ሎሬት ጸጋዬን ደፍረን መናገር የምንችል ኢትዮጵውያን ስንቶቻችን እንደሆን አላወቅም? ከእናንተ ማህበር ውጪ ስንወጣ እሳቸው ሲናገሩት ስሰማ ግን በጣም ነው ያስደመመኝ። ለካስ የኛው ሎሬት በእኛ በቂ ክብርና ውዳሴ ባያገኙም ለዓለም ያተረፉት፤ ያፈለቁት ዕውቀት ነበረ የሚል መልዕክት አስተላልፎልኛል“
ዶር. አብይ አህመድ፤ እኔ አለሁኝ። ደፍርን ለምንናገረው ቀንበሩ ከባድ ነው። ድፍረቴን ግን የሰጠኝ አምላኬ የተመሰገነ ይሆን፤ በሳንክ ብዛት ባልቀጥልበትም አሻራዎቹ ግን አሉ። በሥሜ ቢፈልጉት ያገኙታል። በዚህ ዙሪያ የገጠሙኝ ፈተናዎች፤ ዳጦች፤ ጨቀጨቆችን – እወዳቸዋለሁኝ። ክሱም የሐሤቴ ማህተም ነው። የመኖሬ ሚስጢር ስርትፊኬቴ ነው። ባለማህተም ነው አለ ከእጄ የተከስስኩበት ሰነድ። ለቅኔው ልዑል ለብላቴ ጌታ መንፈስ መቀበል ብቻ ሳይሆን ታማኝነቴንም ፈቅጄለታለሁ። ስለዚህ ከተጠያቂዎች ውጭ ነኝ። አሁንም ተመስገን። የአማራና የኦሮሙ ሙሁራን ስብሰባ ላይ ኢንጂነር ሚኬኤል ሽፈራው የሚባሉ ሊሂቅ አስተያዬት ሰጪ „አስገራሚ ሚስጢራዊ ክስተት“ ሲሉት ከመቀመጫዬ ተነስቼ ሻማ ነበር ያበራሁት። የፍቅሩን ዲካ በእኔ እና  በእሱ መንፈስ መካከል ያለው ሃዲድ ርቁቅ ነው። ትልቅ ነው። ሃይሌም፤ አቅሜም ምንጩ የሆነኝ የብላቴው መንፈስ ነው። ተስፋዬን በቀጣይነት ነው እመራምደው በመጻፍ ህይወት ውስጥ። በር ሲዘጋ በመስኮት፤ መስኮቱ ሲዘጋ በጣሪያ፤ ጣሪያ ሲዘጋ ደግሞ በምድር በታች። አሁን ተመስገን ነው የሃሳቤን የመስኖ ቦይ የሳተናው ድህረ ገጽ በሚገርም ቅንነት እያስተናገደው ነው። ያለምንም ተዕቅቦ …. ይህ ቸርነትን የጋሼ ጸጋዬ ታቦት ስለት ያሰመረልኝ ነው። በሌላ በኩል „የማለዳ ኮከቦች“ ላይ የብላቴ ሥራዎች ጎልተው እንዲወጡ የሚደነቅ ጥረት እያደረጉ ነው። ለዚህም ነው የምወዳቸው ብቻ ሳይሆን የእኔ ነው የምለው የፈጣረውን ባለቤት ገጣሚ ፍጹሜ አስፋውን። አዘውትሬ ነው የማስበው – እሱን። መወለድ ቋንቋ ነው። ሥጋነት የህሊና ድንግልና ብቻ ነው – ለእኔ።
ጋሼ ጸጋዬ አንደ እንግሊዙ „የሶኔት“፤ አንደ ጃፓኖች „ሃይኩ“ እንደ ተፈጥሯችን „ስምንትዮሽን“ ህገ ቅኔ የተጠበበልን የቅኔ ፈላስፋ ነው። ፍልስፍናው በጋሃዱ ዓለም እና በመንፈሳዊ ዓለም ንጹህ ድልድይ የቀዬሰልን የሥነ ቋንቋ የምህንድስና ተቋማችን ነው።  ሎሬቱ የዕውቀት ጉልላት ፕላኔታችን ነው።
ምናባዊ ፍልቀት።
„ይህ ግን በምናብ ተጉዞ ደመናን አልፎ አዳዲስ ያልተዳሰሱ እውቀቶችን፤ ማፈለቅ ካልቻለ፤ ኢማጅነሽን ፓዎራችን ሳንገታ መጓዝ ካልቻለን በሀገር እድገት ውስጥ በሀገር ኢኮኖሚ ውስጥ ፊክሽን ብቻውን በቂ አይደለም። Wright brothers አዬር ፈጠሩ ሲባል ሰምቻለሁ። ግን አልፈጠሩም። Wright brothersሳይሆኑ ከ1000 ዓመት በፊት የግሪክ ፈላስፎች አዬርን ከነዲዛይኑ ፈጥረዋል። ግን አልበሩበትም። ስዕሉ ዛሬም አለ። እነሱ ኢማጂን ያደረጉትን፤ በዋኋላ ላይ Wright brothers ሪያላይዝድ አድርገውታል። ኢማጅኔሽንና ሪአላይዜሽን የማይነጣጠሉ፤ ወንድማማች ናቸው። ኢማጅን ሳይደረግ ሪያላይዝድ ስለማይደረግ። በግሪክ ፍልስፍና ዘመን ውስጥከ ከዖሽን በታች ሃብት ሊገኝ እንደሚችል ፈላስፋዎች ኢማጅን አድርገዋል። ኦሽን በግሪክ ትልቁ ነዳጅ፤ ምግብ፤ መዳህኒት ያለበት መሆኑ ተረጋግጧል። በብራዚል፣ በህንድ፤ አሜሪካና ኩባም፤ ካስታረቀቸው አንዱ ድልድይ በኦሽን ግራፊክ የተደረገው ጥናት የጋራ የምርምር ሥራ ነው። ይሄ ኢማጅን የተደረገው አንግዲህ ከሺህ ዓመት በፊት ነው። ስለዚህ ዛሬ ኢማጅን እምታደርጉት ነገር፤ በሆነ ጊዜ ትውልድ ወደ ተግባር ቀይሮ ከድህንት፤ ከችግር ብዛት ሊላቀቅ የሚችልበትን መሆኑን ማሰብ ያስፈልጋል። ከዚህ አንጻር ሁለት ሰዎች ማንሳት፤ ማስታወስ ጥሩ ነው የሚሆነው፤ አንደኛው „የይሁን ዓለም“ ደራሲ ይኑሩ አይኑሩ አላውቅም  ከ25 ዓመት በፊት በአቶ ደጉ በሚባሉ ሰው ተደርሷል። በመቸቱ በሳተሳሰቡ፤ በቀረጻቸው ካራክተሮች ኢማጅነሪ የሆነ የያኔን ወይንም የዛሬን በሙሉ የማያሳይ ወደፊት የሚያሳይ ጹሑፍ ነበር።“ ይህ ምናባዊ በርቀት የማሰብ ብልህነት በዓለም ዐቀፍ ደረጃ ያገኘውን ተቀባይነት ጠቅሰው በቅርቡም የምናባዊ ሃሳቦችን „በዴርቶ ጋዳ፡ መጸሐፍ በደራሲ ምስብህከ ወርቁን፤ ድንቅ የርቀት የምናብ መነጸር መቃኘቱን በተደሞ ግልጸዋል።
„እንደኒዚህ አይነቶችን የማይጨበጡ የማይዳሰሱ የኢማጅኔሽን ሃሳቦችን ማቆዬት ይገባል፤ እኛ ዛሬ ባንረዳው፤ ባንጠቀምበትም ትውልድ ነገ ወስዶ ችግር የሚፈታበትንና ካለበት ሁኔታ የሚሸጋግርበት ስለሆነ መጸሐፍ፤ ብሄርን ከብሄር የሚያገናኝ ድልድይ ነው፤ ባህል ከባህል የሚያገናኝ የሚያሰተሳስር ድልድይ ነው“
ዶር አብይ አህመድ „ዴርቶ ጋዳን“ በጸጋዬ ራዲዮ ሙሉን ተርኪያዋለሁ አንድ ወጣ። የሆነ ሆኖ ከዚህ ላይ መሠረ ያለው አመክንዮ ነፃነት ለፀሐፍት መስጠት እንደሚገባ ነው ያወጁት። አጋጣሚውን ቢያገኙ ያበረታታሉ፤ ብዕርና ብራና የመጀመሪያ ነፃ የሚወጡት ናቸው። ይህ እንግዲህ ለዘመናት የተማጣንበት ግን አገላጋይ ሃኪም ያልተገኘለት ኢትዮጵያን በአራት ማዕዘን የኢጎ ሳጥን ቆልፎ ፍዳዋን ሲያስከፍል የኖረ የመከራ ቀንበር ነው። አፍ ያለው የቅርጭጭት መቃብር። በተጨማሪም ዴርቶ ጋዳን ሲያነሱ መነሻ ያደረገው የጭበጡ ምኸዋር በብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን እና በሳይንቲስ ኢንጂነር ቅጣው ላይ ሆኖ ማሳው ጣና ነበር። ይህ ደግሞ እሳቸው የተመሰጡበትን ረቂቅ የግንዛቤን አቅም ያሳዬናል።
በተረፈ ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ ይህንስ ህሊናህ እንዴት ይሆን ሊያስተናግደው የሚደፍረው? አቅማቸውን እዬሰረከርክ ስተቦረቡረው ህሊናዬን ቁስልስል ነበር ያደረከው። የማስተዳደር ጥበቡም ግሎባላዊ ነው። ተምረውታል። ኢትዮጵውያን የምናባዊ ፈላስፋዎችን ዕውቅና ዘክሮ፤ አክብሮ የተነሳ ጭብጥ ነው – አንዲህ በቀልድና በቧልት ያረስከው። ስለምን? ዶር. አብይ ለ4ኪሎ ወንበር ብለው አይደለም ኢትዮጵያን የሚወዷት፤ በቅብ ማንነት የሚያረግድ አይደለም የሳቸው ስብዕና። ለእናት ሀገራቸው ያላቸው ፍቅር ከቅድስና በላይ ነው። ለትውልዱ ያለቸው ህልም ድንግል ነው። ውስጣቸውን ሲወዱት ጣዕሙን አጣጥመው፤ በቃናው ውስጥ ፈልቀው ነው። ውስጣቸው ምንድን ነው? የቀለሙ ዓይነትስ? ቀለሙ ውሃማ ነው። ያ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት ነው የማይሰለች፤ ለሁሉ ነገር መነሻና መድርሻ ነው። ስለሆነም ከራሳቸው የመነሳት አቅም ያላቸው ናቸው ዶር አብይ አህመድ ማለት። ይህ ጥልቅነትን በአትኩሮት በህብር የመጥለፍ አቅም፤ ይህን ውበታዊ የህሊና ብቃት የማያያዝ ማስተዋል ከቶ ከዬትኛው የፖለቲካ ሊሂቅ ይሆን ያዬኸው፤ ያዳምጥከው? ለመሆኑ አንድ የሥልጣን ህልመኛ ሊሂቅ „ዴርቶ ጋዳን“ ያነበበ ይኖራልን? አለን? አዬህ በዛ ውስጥ ትውልድ የማይተካው ደግና ሩህሩህ ሳይንቲስት ኢንጂነር ቅጣው ታሪክ አለ። ይህን አቅም የመቀበል ከዬት መጥቶ፤ በሥጋ ተለይቶን እንኳን የሚያባትተው ይኖራል። አድንቆ መነሳት አልተለመደም። ስለዚህ ለእኔ አዲስ ምዕራፍ ነው። ኢጎ ካለሸነፈኽ በስተቀር አንደረታሁህ ይገባሃል። ጨንግፈኽ ሆነ ዘንጥለኽ ያቀርበከው ሰብዕና ውስጡ ምንም ምን እንደሚል እስቲ አጣጥመው። ትእዛዝ አይደለም ትህትናዊ ማሳሰቢያ እንጂ።
የመጸሐፍት ድርሻ።
„ መጸሐፍት ሰውና ሰው እንዲከባብር እንዲዋደድ የሚያደርገ ትልቅ ሃብት ነው። ሃብት ይዘን ደሃ ተብለን እንዳንቀር፤ ብዕሮቻችሁ ስለተው ባህላችነን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ፤ አንድነታችነን የሚያጠናክሩ፤ ሰላማችን የሚያጎሉ ከሆነ እኔ ካለጥርጥር ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው ኢትዮጵያ ትልቅ ሐገር ናት! ምንም ጥርጥር የለውም ቅድም ከተባለው ሳይሆን ከማንም የተሻለ ጭንቅላት፤ ከማንም የተሻለ የማደረግ አቅም፤ እኛ ውስጥ አለ። እኛ ያጣነው ዊዝድም ነው። ጥበብን ፍለጋ ነው። ጥበብን የፈለግ እንደሆነ። ለዛም እምንደመር ከሆነ፤ ካልምንም ጥርጥር ቅድም እምናውሳቸው ጥቋቁር ታሪኮች በቅርቡ ይፋቃል የሚል ሙሉ ዕምነት አለኝ።“
ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ ዶር አብይን አህመድን መንፈስ የቀረጽክበት ቾክህና ሰሌዳው „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ መስሏሃል። ዝበቱ ይሄ ነው። ዝግቱም ይሄ ነው። አንደበትህ ውይብ የሆነው እዚህ ላይ ነው። እያነበቡ አይደለም አንደ አባይ ፏፋቴ ማለቂያ፤ ማብቂያ በሌለው የልህቅና ጉልበታም ውስጥነት አመክንዮ ጰጵሰው ነው።
ልድገምልህ አንድታጣጥመው „እኔ ካለጥርጥር ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው ኢትዮጵያ ትልቅ ሐገር ናት!“ ምንም ጥርጥር የለውም ቅድም ከተባለው ሳይሆን ከማንም የተሻለ ጭንቅላት፤ ከማንም የተሻለ የማደረግ አቅም፤ እኛ ውስጥ አለ።“
አልተሸነፍክም? በጠራራ ጸሃይ ነው ብዕሬ የዘረረችህ 0 ለስንት? አንተው መዝነው። አንዲህ ዓይነት ራስ እግሩ ጥበብ – ትህትና – ርህርህና – አሰባባሰቢ፤ አግባቢ፤ ፍቅር ልጅ ኢትዮጵያስ ሆነች የኦሮሞ እናት አትወልድም ያለህ ከቶ ማን ነው? ማን?! መልስ አለህን? ማይክና ሥልጣን ተመጥኖ፤ ተለክቶ ሲሆን ያምራል። ነገ ሌላ ቀን ነውና …
ትልም፡፤
„ሳይንስና ቴክኖሎጂ በዚህ ዓመት፤ ከመንግሥት በጀት ውስጥ ፈንድ በማፈላለግ ስድስት ላይብራሪዎች፤ በክልል እያደራጀ ነው ያለው። ከላይብራሪ ጋር ተያይዞ እኛ ያለን ፍልስፍና ኦፕን ላይብራሪ የሚባል ነው፤ በቅርቡ ቢሯችን ለመጎብኘት ስለሚፈቀድ ትጎበኙን አላችሁ“
ወስጥን ለማስነበብ መፍቀድ መታደል ነው በራሱ። ለዚህም ነው ስጀምረው ዛሬን ዶር. አብይ አህመድ የተገለጡ መጸሐፍ ናቸው ያልኩት።
የፍላጎት ተነሳሽነትን በትህትና የማዬት አቅም።
„ …. ጽንሰ ሃሳቡ የሚነሳው መጸሐፍ መስረቅ፤ እና ለተለያዬ ነገር ቀዶ መጠቀም፤ በዬትኛውም ዓለም ነበር። እኛም ጋ ይኖራል። ግን ሳም ሃው ያነን ሪስክ መሸከም መቻል አለብን። የኋዋላ ኋዋላ ቀዶ የጠቀለለበት ሰው ሳይቀር ገዝቶ ዶኔት ማድረግ ይጀምራል። ይህ እንዲሆን ደግሞ መጀመሪያ አብሌብል ማድረግ ያስፈልጋል። እኛ ቆልፈን መጸሐፍን ካልፈረምክ፤ መታወቂያ ካለመጣህ እያልን እያቀብን ሳይሆን አንብበው ስትፈልግም ስረቀው ችግር የለውም በኋዋላ መልስህ ዶኔታ ታደርገዋለህ፤ ምክንያቱም መጸሐፍ ሰርቆ ማስቀመጥ ቦታ ማጠበብ ነው ዛሬ፤ …. ዋና ዓላማው የዕውቀት ትራንስፈር ማድረግ ነው። እዛ ማህል የሚገኝ ንግድ አይደለም“
„ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም“ ቅድመ ሁኔታ ለማንኛውም የህይወት ዘርፍ ጠቃሚ አይደለም። ነፃነት መስጠቱ ነው ትርፍ አስገኝው ሃይል ነው የሚሉት። ተመስገን! ህይወት ነው። መንፈስ ቅዱስ የቀረበው መንፈስ ቅዱስ። አብይ ኬኛ! ይቀጥላል …
ቅንነት ብሄር አልቦሽ ነው።
አዬህ ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ ከእኒህ ቅን ሰው መንፈስ ውስጥ ሁላችንም አለን። የደረጃ፤ የእርክን ልዩነት የለም። ሁላችንም በዶር. አብይ አህመድ መንፈስ ውስጥ እኩል ቦታ አለን። እኩል ይወዱናል። እኩል ይሳሱልናል። እኩል ለመንፈሳችን ይጠነቀቃሉ። አይደለም እኛ ሥልጣን ያለው የትግራይ ሥርዕዎ መንግሥት የሥነ – ልቦና ልዕልና ያላቸው ምርጥ ዜጎች ሳይቀሩ እሳቸው የሚያዮቸው በፍቅር ውስጥ ነው። እናድናቸው ነው የሚሉት። ቅንጣት ታክል የበቀል፤ የሰናፍጭ ታክል የጥላቻ መንፈስ የለባቸውም። ስለምን? በቅንነት ውስጥ ዞጋዊነት ስሌለ። „ለማውያን“ ብለህ ስታብጠለጥላቸው ጠረኑ ውርዘቱ ከመታመኩ የተነሳ ዕምል ነበር። ቀለሙ ከመዛጉ የተነሳ ውይብ ነበር። አዬህ አቅም ብናዋጣ፤ አይዟችሁ ብንላቸው፤ ጽናት ብንሰጣቸው ወያኔ ሃርነት አሁን እነዚህ ብርሃኖች ከተሸነፉ በእጥፍ ድርብ የወያኔ ሃርነት ትግራይ በቀሉን ያወራርዳል። አድብቷል፤ ሥራውን እዬሰራ ነው። እርዱ ይቀጥላል። ቢያንስ ከተደላደለ ቦታ ያለ ሰው እንዴት እሳት ውስጥ፤ በመድፍ በተጣረ ውስጥ ገሎ፤ ሰርቆ፤ ዘርፎ ከማይጥግብ አውሬ ጋር ሆኖ እዬተጋፈጠ ከጎኑ መሰለፍ ያቅታል። በመንፈስ አይዟችሁ ማለት። አጅግ ነው የማዝነው። አሁን ያለው ቅራኔ ነገ ከሚመጣው የሃይል አሰላለፍ እና ግብዕቱ ጋር ሲነጻጻር አይመጣጠንም፤ ነገ ትውልዱ በማያባራ እልቂት ውስጥ ይሆናል። በጡንቻ በእጥፍ የኦሮሞ ልጆች ይጋዛሉ፤ በሽምቅ ውጊያ ደግሞ ሺዎችን አጓጉዞ ስለማያዘልቀው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ቤተሰቦች የህዝቡ ቁጣ እዬናረ ከሄደ በቀጥታ በትግራይ ልጆች ላይ ያነጣጠረ ሊሆን ይችላል። ፍቅርን እምታመጣው በሃይል አይደለም። በፍጹም። ከጫፍ እስከ ጫፍ በእነሱ ምክንያት የትግራይን ቃና ማዳመጥ የሚፈልግ አንድስም እንኳን ነፍስ የለም። ይህን ማሻሻል የሚቻልበትን መንገድ ነበር እነዚህ ብላቴናዎች ጥረት ያደረጉት። የፍቅርን ግማድ ነበር የተሸከሙት። ግን በግራ በቀኝ ተወጠሩ። እራሱ አልገባኝም ለመከላከያ ምስክርነት እንዲቀርቡ የተፈለገበት ምክንያት። ለምን መጠራቅቅ እንደሆን? ምን ለማትረፍ? አላውቅም። ሊገባኝ አልቻለም? ጭንቀቸውን እና ጫናቸውን ማርገብ ሲጋባ በዬቦታው ወጠርናቸው። መጀገን ያቃተው ጀግና ሁኑ ይላል። ቃልን አስተካክሎ በመጥራት የሚሊዮንን ሞራል መጠበቅ ሲጋባ ያን ማደረግ ያልቻለ በጋመ እሳተ ጎመራ ውስጥ ለሆነ ነፍስ በዬለቱ አጀንዳ ይሰጣል። እኛ 42/ 20/ 10/ ዓመት ያልሠረነውን …
„አናስደንግጣቸው“ ብሎን ነበር የፋክት ጸሐፊው ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና። ግን ጆሮ ብቻ ሳይሆን ዕዝነ ህሊናችን እራሱ ተስልቧል። ድንግል ትጠብቃቸው። አብይ ኬኛ! ይቀጥላል …
እንደ ምርኩዝ።
የማንበብ ፍቅር በድህነት ውስጥም እንዲህ ይገለጻል።
ታዳጊ ወጣት ያሬድ አፍወርቅ ጫማ ጠርጎ ነው የሚተዳደረው። በዛች መከራ በደለቃት ኮሳሳ ጎጆው ውስጥ እዚህ ውጭ ሐገር እንደምናዬው ቤተ መጸሐፍት አለው። አሁን በዚህ የንባብ ህይወት ዝግጅት ላይ ጥልቀት ያለው መንፈስ አዳምጫለሁ። ምኞቴ በዚህ በታዳጊ ወጣት ሥም የተሰዬመ አንድ ዕውቅናው የላቀ ቤተ መጸሐፍት ክበብ ነገር ማደረጀት ቢቻል እንዴት አብነት በሆነ። ዶር. አብይ አህመድን የተኩት ሚ/ር የቤት ሥራውን ልሰጥ እንሆ በትህትና ወደድኩኝ። መቸም አዲሱ ሚር/ በተባ መሬት ላይ ሆነው ነውና ተግባራቸውን አህዱ ያሉት። አሳማረውላቸዋል ዓውደ ምህረቱን።

ማንበብ ሙሉ ሰው ያደርጋል–መጽሀፍ በነጻ የሚያስነብበው ወጣት ያሬድ አፈወርቅ ወጣት ያሬድ በባህር ዳር ከተማ በሊስትሮ ስራ ይተዳደራል፡፡

Branna Radio Oct 11 2017 Discussion with Befeqadu Z Hailu Part One በፈቃዱ ኃይሉ ጋር የተደረገ ውይይት ክፍል አንድ

Befekadu Hailu part 2 በፈቃዱ ኃይሉ ክፍል ሁለት
አቤቱ አምላኬ ሆይ በተስፋ ውስጥ ክፉ ነገር አደራህን እንዳታሰማኝ!
አቤቱ አምላኬ ሆይ ማስተዋሉን እንደሰጠህን እንጠቀምበት ዘንድ ልቦናችን ክፈት! አሜን!
ኢትዮጵያዊነት የፊደል ገበታ ነው!
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።፡መሸቢያ ጊዜ።

ክፍል – አምስት፤ አብይ ኬኛ! ለቅኖች ብቻ።  አብይ ክስተት ነው ለመቅድመ – ጠፈር   (ሥርጉተ ሥላሴ )

December 31, 2017 19:18

ክፍል – አምስት፤ አብይ ኬኛ! ለቅኖች ብቻ።
አብይ ክስተት ነው ለመቅድመ – ጠፈር
ሳይንቲስቷ ለኢትዮጵያም!
ከሥርጉተ ሥላሴ 01.01.2018 (ከአደብማዋ ሲዊዘርላንድ።)
„የሰው ልጅ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ (ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፱)
„ፍቅር በማካፈል ሰላምና ፍቅራችን በዝቶልን መኖርን እንፈልጋለን። እናንተም እንደ ኦሮሞ ህዝብ ለጋሽ ህዝብ ስለሆናችሁ ብር ብቻ ሳይሆን ሳቃችሁን እና ፍቅራችሁን እንድትልግሱን እንጠይቃለን።“ (ዶር. አብይ አህመድ።) „እንጠይቃለን?“ ይገርማል የትህትናው ርስት ዕሴት አዱኛው የልብ ነው፤
ቀኒት ቀን ወጣላት።
አንዲህና እንዲያ ስትባትል ኗራ
ተለቅልቃ በነጭ በጋራ ተራራ
ተመርምራ ሳታውቅ በዕውቀት ተፈርፍራ
ተጠቅልላ ነበር ክስተቷን ተወራ።
ስለተመስጌንም ዛሬ እንዲህ ስገራ
በተስፋ ብርሃና ነባቢት ሲደራ
ዋልድባ ቦረና በአብይ አርጎ በራ
ጉማጉም ተገፎ ይሄው ሆነ ብራ!
አለኝ።
እንሆ ሙሉ ወርዴን በመቀነት አደግድጌ ለጥ ብዬ አጅ ነሳሁ ለቤተ – መንግሥቱ ጋዜጠኛ ለማስረሻ አለሙ። ስለምን? ትንሳኤን ይዞ በአዲስ ዓመት በድል ኮሮጆ አንቀጻትን ሊያሰቆጠርኝ ስንቅ ስለቋጠረልኝ። ለዛውም በርህሩህ ልቦና እና በኮስታራ ሃሞት፤ እኔንም አማራውን ለዛውም ጎንደሬዋን ሊያቅፈኝ፤ ሊደግፈኝ አለሽ ብሎ ዕውቅና ሊያሳፍሰኝ በተስፋ አሹልኮ መፈክር ሊያረገኝ ስለሆነ።
ቢከፈት።
ወንድም ጋዜጠኛ ማሰረሻ አለሙ አንተ ባትኖር በውስጤ ክስተት ገፋ አድርጌ አልሄድበትም ነበር። ስለ አቶ ለማ መገርሳ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ስጽፍ ብዙ አልተጻፈላቸውም፤ አልተነገረላቸውም እንጂ ከጎናቸው ዶር. አብይ አህመድ መኖራቸውን እሰቡት በማለት ለበስ አድርጌ ነበር ያለፍኩት። ካሰኘህ ሙግቱን ግን ተአባቶቼ፤ ተጥንተ – ተጠዋቱ  በተጠዬቅ ደሜ ተኑረንበታል። ተንጠባጣቢ ውራጅ ሳይፈልግ በነጠረው ንጥሩ ሙግቱ ሆነ መርታቱ ተዚህም አለ። እንዲህ የተከደነው ሲሳይ ተከፍቶ ይገለጥ መዝገቡ ይነበብ ተባለለት፤ እልሃለሁ አቶ ወንድም የቤተ- መንግሥቱ ሊጋባ። ከቶ „ወንድም“ ማለት ካለደረጃዬ ተንጠራራሁ ይሆን? እንደ መዳፈርስ ትቆጥርብኝ ይሆን፤ ከሆነ ለጥ ብዬ ይቅርታ እላለሁ … ነገ መግቢያ የለኝም እና፤ የዜግነት ርቦና ሲሶ … እያመሰን ተዚህም። ህም።
አዬህ 40 ዓመት ሙሉ ዜግነትን መሰረት ያደረገ የመንፈስ የውሃ ልክ ውቅር አልነበረንም። እርሾ አልቦሽ ነበር። በደርግ ጊዜ ጨቋኝና ተጨቋኝ የሚል ነበር። ጨቋኞች እኛ ነን የሚሉ አማራዎች ሳሉት ባለ ሁለት አፉን ማረጃውን – ለራሳቸው። አሁን ደግሞ ጨቋኙ የአማራ ብሄር እሱን በማጥፋት ነው፤  አሁንም ከዛ መሠረተ ሃሳብ ተነስቶ አንድ አናሳ ብሄረሰብ ዘለግ አድርጎ ሌሎችን በአጃቢነት አሰልፎ ተነሳ፤ ወያኔም ዲሞክራሲ አብዮት በጎሳ ዶክተሪን ነው፤ ደርግም ያራምደው የነበረው በመደብ ላይ አንቱ የሆነ ዴሞክራሲያዊ አብዮት። ልዩነቱ ይሄኛው ትግራዊ ዜግነትን ይዞ አሸናፊ አድርጎ መውጣት፤ በሂደቱ ሌሎችንም አቅም እያሳጣ እስከ አስኬደው መንገድ ድረስ መጓዝ፤ ካላዋጣውም ወደ ተነሳበት ተመልሶ የታላቋ ትግራይን ሪፕብሊክ መመሰረት። ይህን ለማድረግ „ኢትዮጵያ“ እያለ የሚነስተውን አማራን ጥርግ አደርጎ ማጽዳት። ዛሬ ካለንበት ደረስን።
የአደራ ማህደር።
ለእኔ ውጪ ሐገር ሁለት ተቋማት ብቻ ከዚህ የወጡ ናቸው። ማለት ዜግንነትን መሰረት ያደረጉ ለናሙና የሚጠቀሱ።  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ስደተኛው ቅዱስ ሲኖዶስ እና የስሜን አሜሪካ ስፖርት ድርጅት። ታስታውሳለህ አይደል? የዘንድሮ የስሜን አሜሪካ የስፖርት ፌስታ ላይ የብዕሩን ለዛ የምወድለት የህግ ባለሙያው አቶ ተክለሚኬኤል አበበ እንደ እብድ ነበር ያደረገው። በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ማለት ሆነ በጠቢቡ ቴወድሮስ „ኢትዮጵያ እና  በአጤ ቴወድሮስ የጎንደር የግጥም ስንኛት።“ ወልድያ በጥጋባቸው የተጋሩ ኮበሌዎች በፈጠሩት ችግር የመቀሌ ወጣቶች ምሽቱን ቀውጢ ሲያደርጉት፤ አዲግራት ላይ ዩንቨርስቲውና ማህበረሱ አደራውን በልቶ ታሪክ ይቅር የማይለው ግድፈት ውስጥ ሲጨመሩ፤ ትዝ ያለኝ ልጅ ተክሌም አጋጣሚውን ቢያገኝ ጠቢቡን ቴዲን ሆነ ተከታዮችን ምን ሊያደርግ ይችል ይሆን ያሰኝም ነበር። ልጅ ተክሌ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ በሚመለከት በ2013 የጎንደሬዎች „ማህበር“ አድርጎ በዘለፋ ነበር የፃፈው። ግን አባቶቻችን ባለፈው ዓመት በነበረው የሃሳብ ጉስጉስ ዘው አሉን? አላሉም። የእነሱ ተልዕኮ የእግዚአብሄርን የሰማዬ መንግሥት ህግጋት ማስፈጸም ነው። ስለሆነም ልጅ ተክሌ የተነሳባት የጥላቻ መንፈሱ መቅኖ አጥቶ ቀረ። ይህ የአደባባይ ሚስጢር ነው። አባቶቼ ዶግማቸው የሰማይ እንጂ ምድራዊ ሆኖ በገሃዱ ዓለም እንደምንተራመሰው የሃሳብ ልቃቂት በዝብርቅነት የሚዘፈቁ አይደሉም። የእኔን ሃሳብ ይዘው ባለመነሳታቸው፤ ያን ሃሳብ ወግነው የተሰጣቸውን ሰማያዊ ጸጋ ባለመዳፈራቸው እነሱን በጠራ ሰማይ ላይ የሚያበሩ ክዋክብት ሆነው እንዳያቸው አድርጎኛል። ይሄ ነው ቅድስና። ይሄ ነው መንፈሳዊነት። ይሄ ነው የተዋህዶ ሚስጢር ድንበር አልቦሽ፤ ወሰን አልቦሽ መክሊትን በትጋት መከወን ማለት። ስለዚህም ነው ዛሬ በሁለተኝነት እነሱን ያከልኩት። ዝንፍ አላሉም። በፍጹም። በዚህ ጽናታቸው እንዲቀጥሉም መንፈስ ቅዱስ ይርዳልኝ። አሜን! እንደ ገሃዱ ዓለም ሰወች እንደ እኛ እንዲሆኑ ፈቃዴ አይደለም እና። ምድራዊ ቤት ምናቸውም አይደለም? ተመስገን!
እነኝህ አካላት ውጪ ሐገር ሆነው ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያዊነት ዜግነት አጥፍቶ ቢቻል ትግራዊነትን ባይቻል ደግሞ „ድህነትን“ ዜግነቴ ነው ብሎ እንደ ተነሳው ወጣት ጦማሪ በፍቃዱ ሀይሉ ማድረግ ነበር። ተሳከቶለትማል። ውሉ ጠፍቶ ድክረቱም ይሄው ነው። ስጋት፤ ፍርሃት ተናኝቷል። ነገር ግን ኢትዮጵያ አምላክ አላት እና አንድ ነብይ አስነሳ አብይ የሚባል። የመጀመሪያው ተቋም በ40 ዓመቱ የኢትዮጵያዊነት ዜግነት የጨለማ ዘመን፤ ዜግነትን ማዕከል አድርጎ የተነሳ ህላዊነት። ልቅናው ከዛሬ ላይ የተነሳ አይደለም ከመነሻው የተነሳ ነው። እያንዳንዷ ጥቃቅን ነገር በትርጉሙ ውስጥ ቤተኛ ናት እንኳንስ ኢትዮጵያዊው ሰው፤ ኢትዮጵያዊው ጫካ፤ ዱር ገደል፤ ሸለቆ፤ አየር፤ ገዳማት፤ ቅርሳት ዜጋ ነው ለዶር አብይ አህመድ። ማዕከሉ ሰው፤ ሩጫው ሰውን ሰው በማድረግ ኢትዮጵያን አኩል ማድረግ – ከሰለጠኑት። እኩል ለማድረግ ከስንት ሺህ ዓመታት በፊት የሥነ – ክዋክብት፤ የሥነ ቀን አቆጣጠር የጠፈር ጥበብ ተማራማሪዋን፤ ሞጋች ሳይንቲስነቷን፤ ፈላስማዋን ኢትዮጵያን ውስጥ በማድረግ ነው ዶር. አብይ አህመድ ፈለግ ህይወት የሆኑት። ወደ ኦህዲድ ዶር አብይ አህመድ ሲሸጋገሩ  የተሰጣቸውን ሰማያዊ ጥሪ በመያዝ ስንቁን አዳጉሰው፤ አደራጅተው ነው። በአጭር ጊዜ ነው የተሳካው። ልክ እንደ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መሠረት። የእልፎች የመንፈስን የደም ማዘዣ ጣቢያ ማግኘት ቻሉ።
አግልሎ፤ ጠልቶ፤ ወግኖ የተነሳውን መንፈስ ሁሉ ተጸዬፉት። ያን ፈራጅ ለይ ስንኩል መንፈስ ማድመጥን ነፈጉት። አንተ እዬተዋጋህ ያለኸው በአምሳሉ ለሌላ 27 ዓመት በማግገለ ላይ ቁጭ በሉ እያልከን ነው የምትሰብከው። አትችልም። „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ የእንደ ገና መወለድ ጽኑሱ ከታማኙ ቤት መምህራዊ የማሳመን አቅም መርጌታነትን ከዶር አብይ መንፈስ ፈቅዶ መስተዋድድ በመሆኑ ነው።
„ሰው ከሌለው በደመቀው ከተማ በቀትር ብትጓዝ ይጨለምሃል፤ ትፈራልህ“
ይልሃል የአብይ መንፈስ። አንተ የምትከተለው የተማረና ያልተማረ፤ ሴትና ወንድ፤ አማራና ትግሬን አግለህ ነው እሱ ደግሞ ይዟት የመጣት ሊቅ „ሳይንቲስት ለመሆን ሰው መሆን ብቻ ይበቃል“ የምትል ነፍስን ነው።
„ራሳችን ስንጠይቅ ስንመለከት ምን ይታዬናል? ድመት ሆነን አንበሳ ነው የሚታዬን? ወይንስ አንበሳ ሆነን ድመት ይታዬናል? ወይንስ ሰው ሆነን ሰው ይታዬናል፤ ስለሳይንስ ስናወራ፤ ሳይንቲስት ለመሆን ሰው ብቻ  መሆን በቂ ነው።“ የአብይ ክስተታዊ መንፈስ እንዲህ ዓይነቶችን ሊቃናተ አንስትን ለማድመጥ ይፈቅዳል። የእናንተው ለብዕር ምርት እንኳን አስቁሙ፤ እገዱ፤ እንዴት እንዲህ ዓይነት ጹሑፍ ታወጣላችሁ ወዘተ ወዘተ … ለዛውም በሞፈር ዘመት ሄዳችሁ … ሁሉንም መጠቅላል ትሻላችሁ። ከቤተኞቻችሁ ማን ድርሽ ሲል። በሰው ቤትም አራጊ ፈጣሪ መሆንን ታልማላችሁ።
የዶር. አብይ አህመድ የህሊና ምናባዊ ጉዞ እና የዛሬ 40 ዓመት ከቆማችሁበት ፈቅ ለማለት ላልተፈቀዳችሁ የግራ አራማጆች ልዩነታችሁ የዛሬ 200 ዓመትም አይገናኝም። ድልድዩ ተሰብሯል። የማዝንው አንተ ከዛ የተረፍክ የዛሬው ትውልድ ሆነህ በዛ ውስጥ መሆንህ ነው። እኔ ደግሞ ስላዬሁት፤ ስለሰለጠንኩበት፤ ስለመረመርኩት፤ ስለሰራሁበት፤ በተሰበረ ድልድይ ወይንም ባለቀ ባትሪ ውስጥ እዬዳክርክ መሆንህ ማሳዬት ትውልዳዊ ድርሻዬ ነው። ዝም የምለው የነፃነቱ ትግሉን ሞራል ለመጠበቅ እንጂ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በሻብያ ልብ ተገጥሞለት ሂደቱን የጀመረው በአማተር ጫካዊ ትውና ነው። አሁን ዘመን ተገልብጦ በእውቀት ላይ በተመሰረት ጊዜ እዬጠበቀ በሚፈነዳ አስደንጋጭ ቦንብ፤ በሰለጠነ ብልጣዊ ዘዴ ያልተከለሰ ሂደቱን እያስተዋልን ነው። ከዚህ አፈንግጦ ብርሃን ጨረሯን ስትልክ ግርዶሽ ያሰኛል ካል ግን በልክህ፣ አቅምህን አውቀህ ትራመድ ዘንድ ይህ የብዕር ቦንብ ይላክልሃል፤ አልሆነም ካልክ ደግሞ በሰነድ፤ በድምጽ የተደገፉ አመክንዮችን ይዘን እንሞግትሃለን፤ አዬህ በችሮታ የሚገኝ ዜግነት የለም። ዛሬ ዜግነቴን ከትግራይ ሥርዕዎ መንግስት እለምናለሁ፤ ነገ ደግሞ በበታችን ስሜት ከሰመጠ፤ ሁሉንም ሥልጣን ከውኖ በአንድ የሃሳብ የበላይነት ባሰላ እጅግ አናሳ ቁጥር ካለው ብሄረሰብ ተንበርክኬ እኔም መለመን፤ ወጣቶቼም በዛ ሥር ወድቀው እንዲማቅቁ ስለማልፈቅድ እሞግተሃለሁ።
ለዚህ እኮ ነው ዶር. አበባ ፈቃደን የምትፈሯቸው። ባለፈው ከአቶ እያሱ አለማዬሁን ቃለ ምልስ አድርጋችኋዋል፤ ዶር ነገዴ ጎበዜን ግን አላደረጋችሁም። ለዛውም መንፈሳቸው ቤተኛ ነው የሚልም ሰምቻለሁ፤ የሆነ ሆኖ ዶር. አሰፋ ነጋሽን ግን ስለምን አትሞግቱትም፤ ለምን? አቶ እያሱ አለማዬሁ ጉራጌ፤ ዶር ነገዴ ጎበዜ እና ዶር. አሰፋ ነጋሽ አማራ ስለሆኑ ብቻ። ለዚህ ሌላ ሎጅክ ላምጣ ብትል አሁንም እሞግትሃለሁ ፋክት ከእጄ አለና። አዬህ አሁን እኔ የምጽፈው ለሳተናው ሙሉውን ተመችቶት አይመስለህ። የማይመቸው አለ፤ ግን ዴሞክራሲ የማይመችህንም ለማድመጥ መፍቀድ ነው። ዴሞክራሲ ሰሌዳ ላይ መጻፍ አይደለም። ከራስህ ነው የሚጀመረው። ሌላው ጋዜጠኛ ሰውን ማዕከል፤ እውነትን መሪህ ብታዳርግ ይህ የሚያቅት አስፈሪ አይሆንም ነበር። እማንታዘብ ይምስለሃልን? የማናይ ይመስልሃልን? የማናስተውል ይመስልሃልን? ሦስቱንም በአካል እኔ አውቃቸዋለሁ። ለሚያምኑበት ዓላማ አቅማቸው አይበላለጥም። በጽናታቸው ውስጥ ሙላት በመጣ ቁጥር ዘንበል ቀና የሚሉም አይደሉም። እውነቱን ብነግርህ ድፍረት ያንሳችኋዋል። ደፋሮች ብትሆኑማ እንደ ጋዜጠኛና ሰብዕዊ መብት ተሟጋቹ  እንደ ሙሉቀን ተስፋው እንደ አደረገው ጦማሪ በፈቃዱ ሀይሉን መድረኩን ከፍታችሁ በትህትና ትሞግቱ ነበር። ድፈረት አይሸመት በሶሻሊዝም ዲሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት የዛር አዟሪት። መጫን – መጨፍለቅ – መዳጥ – ማፈን፤ ወያኔ ሃርነትን በመተቸት አምክንዮ ሚዛን ውስጥ መስታውት አልቦሽነቱ ስልስልም ድርቅ የመታውም ለዚህ ነው። በራስ ላይ ምን ጎደለ ጉድፌ ምንድን ነው ማለት ማን ይድፈራት? በነፃነት ሀገር ነፍስ ነፃነት አግኝታ በቅላ ማደግ አትችልም። በዬአመቱ ጉግስ።
ከዚህ እንድትወጡ ባለፈው ዓመት በተከታታይ ጹሐፎችን ጽፌያለሁ። ሃብት የመንፈስ እንጂ የከረባት ወይንም የገበርዲን አይደለም። ዛሬ ምንያህሉ መንፈስ እዬሸሸ፤ እዬቀነሰ፤ ተስፋ እያጣ፤ ጥግ እዬፈለገ ስለመሆኑ „ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው“ ከለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደ ደገፈ ሌላ ማሰረጃ ማቅረብ አይቻልም። በላፈው ዓመት ስጽፍ ዲሞክራቶች መሸነፋቸውን ያወቁት ዘግይተው፤ ከተሸነፉ በኋዋላ ነው ብዬ ሁሉ ነበር። ግን ትቢያ ላይ ያለች ሴትን ማን ያድምጥ? የወረቀታችሁ ማህበርተኛ ስላልሆነች የምታመልኩት ዲግሪም የላትም፤ በዛ ላይ አማራ ጎንደሬ። እንሆ „ሰው የዘራውን ያፍሳል።“ የሰሞኑ ስብሰባዎች የወንበሮች እንጂ የሰው አልነበሩም የሆላንዱንም የሙንሽኑንም ተመልከተው። ለዛውም ሙንሽን ዜግነትን ማዕከሉ ያደረገ የቅኖች፤ የተግባር አንበሶች መንደር ነው። እነሱንም በአካል አውቃቸዋለሁ – የተግባር ሰውነታቸውን እመሰክርላቸዋለሁ። ቦታ ጠፍቶ ተሳታፊ እንዳልተመለሰ፤ ያን ያህል ክፍት ቦታ ሳይ ደንግጫለሁ። ያ ሁሉ የመንፈስ ሃብት በአመራር የስልት፤ የጥበብ፤ የተመክሮ አያያዝ ማነስ ተናዳ …. አዝናለሁ … የሚያሳዝነው ይህ መንገድ አሁንም ያዋጣናል ተብሎ መቀጠሉ ነው። ውጪ ሀገር የአቅም ጥገኝነት ልመና፤ ሀገር ውስጥ የአቅም ጥገኝነት ልመና፤ ለመሆኑ የአንተ፤ እምተኮራበት፤ ደረትህ ነፍተህ በዬዓመቱ በዙር እምትፎክርበት አቅምህ አድራሻው የት ላይ ነው? የሃሳብ የበላይነት ከኖረህ የሰበሰብከውን እያፈሰስከው ሳይሆን እዬጨመርክበት፤ እያሰበልክ ድል ላይ መሆን ነበረበት … በስተቀር „ማሰሪያ የሌለው ልጥ“ ነው የሚሆነው … በአቅሙ ውስጥ ሌላ ያልታቀደ ሃሳብ አቅም እያገኘ ሲመጣ አንተን የበጠበጠህ ይሄ ነው። „ወትሮ ነበር እንጂ ….“ አዬህ ያን ያህል የተራራ ያህል ንቀት አያተርፍም። ትዕቢተኛውን ወያኔን እዬታገልን ሌላ ትዕቢት ለመሸከም መታቀድ አይገባም ነበር። በችግር ውስጥ የችግርህን አቃላይ መስመር እንጂ የችግር አጣብቂኝ ማቀድ የተገባ አዋጪ መንገድ አይደለም። ይህ ነው ያልገባህ የወርቅ እንክብል ፍሬ ነገር። ያን ጊዜ ካስተውስከው ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል ብያለሁ። የወያኔ ሃርነት ትግራይ የሰሞኑ የዝባዝንኬ ድሪቶም ይህንኑ ያዬሁበት። በዛ ውስጥ ፍሬና እንክርዳድን መለዬት የዶክትሬት ማዕረግ ባለድግሪነት አይጠይቅም። ቅንነት ብቻ እንጂ።
ክስተት።
ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ የነገ የ4ኪሎ መንበር ባለሙሉ ሥልጣን፤ ካለ ትንሽ ራፊ ጨርቅ የጠቀጠቃቸው ዶር. አብይ አህመድ የሀረርን ተፈጥሮ ተክነውበታል። መቼስ አይካድ ነገር ሐረር ኢትዮጵያ መሆኗ። ኢትዮጵያም የሐረር፤ ሐረርም የኢትዮጵያ የፍቅር ነፍስ። ስለፍቅር ኢትዮጵያ መምህርነቷ ሥረ – ትውፊት እንዳለው፤ በፍቅርም ተፈጥሮ፤ በፍቅር መርህ አፈጻጸም፤ በፍቅር ዶግማ እናት ኢትዮጵያ አብነቷ ዝልቅ ሰለመሆኗ ዶር. አብይ አህመድ የገለጹበት ትሁታዊ፤ ክብረታዊ፤ ሰናያዊ፤ አትኩሮታዊ፤ እራስን ዝቅ ያደረገ መሳጫዊ ንግግር ለማዕልቲት ማህሌት ትቆም ዘንድ እንዲህ ወደድኩኝ።
አንዱን አቅርበህ አንዱን አርቀህ፤ አንዱን ቤተኛ አድርገህ አንዱን የእንጀራ ልጅ አድረገህ፤ አንዱን ንቀህ ሌላውን አልቀህ፤ ለአንዱ ትውልድ የሥነ – ልቦና ጤንነት ተጨንቀህ እና ተጠብበህ ለሌላው ደግሞ ጠቅጥቀህና አጎሳቁለህ፤ አንዱን የደም ፍርፋሪ  እንጥብጣቢህን አጠራቅመህ አጠጋግተህ ሌላውን ደግሞ በባይተዋርነት ገፍተህ – ገፍትረህ – ገርፈህም ኢትዮጵያ ማለት ከፓስተርነት አያልፍም። አንተ ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ እራስህ የፖስተር ፍቅረኛ ስለሆንክ በሰውኛ ቋንቋ ባልፈተሽክው፤ ወይንም ባልመረመርከው፤ ወይንም ሂደቱን በጥሞና ልትታደምበት ባልፈቀድከው አግላይ፤ ወጋኝ ፖለቲካ አንደበተ መንበር ላይ ሆነህ „በሰው ቁስል እንጨት“ እንዲሉ ታቆስለናለህ፤ ከዛም ባለዘመኖች፤ ከዚህም „የመላዕክታን ጉባኤ“ የሚሰልቁን፤ እንዲሁም ሥነ – ልቦናችን በዬአመቱ በቤንዚን አርከፍክፈው የሚያነዱት አልበቃ ብሎ። መቼስ አዘኔታ አልፈጠረልህም። እስቲ ትንሽ ብንስቅ ምንህ ይቀነሳል? ደስ ቢለን ተስፋ ብንደርግ፤ ዜግነታችን መለኪያ ሲሆንልን እንይ ብለን ብናስብ ምን ይገድህ ነበር? አለመማር ወንጀል ሆኖ ስታጣጥሉት፤ ስታብጠለጥሉት፤ ወልቃይት መወለድም ውሽክ ማድረጊያ የማቃለያ ቅመም ስታደርጉት የላሊበላን ውቅር ፍልፍል ድንጋይ ውጤት መስህብነት አታስታውሱትም? የአድዋን ድል ትዝ አይላችሁም? ስንቱ?
አዬህ … መሪነት ምንጩ ከንጹህ ልብ ይቀዳል። ርህርሄ ስላልከው ሳይሆን ስትሆንበት አንተነትህን ያስነብባል። ርህራሄ ቤተኛ እና ገረድ ሠርተህ አይደለም። መሪነትን ውስጥህን በውስጣቸው በፍቅር ተሸሙኖ፤ በማህባዉ ጸዳል የፊት ጸዳላቸው ወጋገን በያለንበት የተስፋ ማህጸን እንዲሆኑልን የፈቀደንላቸው ዶር. አብይ አህመድን ገጻቸውን ብቻ ዛሬ ለመነሻ በመረጥኩት ርዕሰ ጉዳይ ላይ እያቸው። „ ዛሬ ታምራላችሁ“ በማለት የሊቀ – ሊቃውነቱን የምርምር፤ የርቀት ምናባዊ ምልሰትና የወደፊት ትልም የሆነውን የልቅና ጉባኤ ሲፈክቱ አስተውለው። „https://www.youtube.com/watch?v=5bzcyojnaMY Science Conference (የሳይንስ ጉባኤ)“
ከልብህ ሆነህ። የሚነግርህ፤ የሚያጫውትህ፤ የሚስብህ ማዕዛና ጣዕማዊ መልዕክት አለው … ዜግነታዊ ሰውኛ አለው። ውስጠህን በፍቅር ጥሪኝ ይደባብሳውል፤ ያበባብለዋል፤ ያቆላምጠዋል፤ መካራው ጠንቶበት ትራስ ውስጥ ተንተርሰኸው እንዳደረ ጨርቅ ኩፍትርትር ያለውን ነፍስ ውስጡን ፈቅዶ ቧ አድርጎ ከፍቶ ፏ እንድትል፤ ስጋት እንዳይኖርብህ፤ ጥርጣሬ እንዳያባዝትህ ዕድሉን በአዲስ ብሥራት ይከፍታል። ግን ይህ የሚታይህ የቅንነት ቤተኛ መሆን ሲቻልህ ብቻ ነው። ለማንፌስቶነት ማህበርተኝነት ሞትም ጉዳያችሁ አይደለም። መጋጋሉን ብቻ ነው የምትፈልጉት። ሥልጣን ወንበር አሁኑኑ! ይህም ድሃ ወገንህን አስፈንጥረህ ሳይሆን የእኔ ሃብት ስትለው። ያለተማረውን ሥጋህን አቅርበህ እንደ ተፈጥሮው ስታጣጥመው፤ ለዛው እንዲስብህ ስትፈቅድለት፤ እንደ አቅሙ ስተቀበለው ነው። አካለ የታመመ፤ በሽተኛ ቢሆን ሥጋህ – ደምህ – ነፍስህ  -መንፈስህ ስለመሆኑ ስታቀፈው፤ ልብሱ ቆሻሻ መሆኑን ሳትጸዬፈው ነው፤ ይህንም ታደልኩበት ስትለው ብቻ ነው። ነገ ድምጹን እኮ ታልማለህ አይደል በቀጥታ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፤ ስለህዝብ አክብሮት ፍቅር እንዲህ ይላሉ ዶር. አብይ አህመድ … እነሆ …
„ወደ ሐረርጌ የመጣነው በአሁኑ ጊዜ ዓለም እያጣች ያለችውን ፍቅር እናንተ ዘንድ በብዛት እያመረታችሁ ስለሆነ እንዳታክፈሉን ብለን ነው። ምክንያቱም ባሁኑ ጊዜ ፍቅር ማጣት የአገር ችግር ስለሆነ። በአለም ሆነ በአገራችን ችግር እንዲፈጠር ምክንያት እዬሆነ ያለ የእርስ በርስ ፍቅር ማጣት በሐረርጌዎች ዘንድ በብዛት እያመረተ ነው። ወደ እኛ እንድታስላልፉልን፤ ኤክስፖርት እንደታደርጉልን እንፈልጋለን። ምክንያቱም እዬበላን ተርበናል። እዬጠጣን ተጠምተናል። ያለውን ፍቅር በመካፈል ሰላምና ፍቅራችን በዝቶልን መኖር እንፈልጋለን። እናንተም እንደ ኦሮሞ ህዝብ ለጋሽ ህዝብ ስለሆናችሁ ብቻ ሳይሆን ሳቀችሁን እና ፍቅራችሁን እንድትለግሱልን እንፈልጋለን።“
https://www.youtube.com/watch?v=rZj7KffGJa8
Dr Abiy Ahmed Called for UNITY in Oromiyaa Oct 18, 2017
ኢትዮጵያ የፍቅር ትምህርት ቤት ናት ነው የሚሉት። ፍቅርን ከእናቴ ጠብቼ ግን አልሆንኩበትም እርቦኛል፤ ጠምቶኛል እና እባካችሁን አጥቡኝ እያሉ ነው። እኔም በ2015 በዚህ ላይ አትኩሮት ያለው መልዕክት ነበር ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የላኩት። ፍቅርን በትምህርት ቤት እንደ ቁጥር፤ እንደ ቋንቋ ትምህርት ልጆች በት/ ቤት መማር አለባቸው ነበር ፕሮጀክቴ፤ በዶር አብይ አህመድ ህሊና ዕውቅና ይሄው አግኝቷል። ያን ጊዜ የቀድሞው የተባበሩት መንግስታት ጸሐፊ መልሱን ሲጽፉልኝ እስኪ ለሀገርሽ መንግሥት አማካሪያቸው ብለውኝ ነበር። ለማን? ለዬትኛው መንግሥቴ? አንድ ቀንጣ ነፍስ ለመንፈሴ ይሄ ነው የምለው አለነበረም። እግዚአብሄር ይመስገን ፍቅር የራበው፤ ፍቅር የጠማው፤ የፍቅር ናፋቂ ለዛውም የፖለቲካ ሊሂቅ ተገኘ በሀገሬ መሬት  በኢትዮጵያ። ስለዚህ ከዚህ በላይ ለዓለም ፈዋሽ መንፈስ አለ አላልም። ህልሜን ለዛውም በሥጋና በደሜ ውስጠት እነሆ አዬሁት። አገኘሁት። ተስፋዬ ተንሰራፋ ትንሳኤ ይሄ እንጂ የኮሮጆ ቁጥር ልመና ደጅ ጥናተኛ አይደለም። ፍቅር በመታመን ማህጸን እንጂ በቃላት ካብ አይሸመትም። ፍቅር የገቡትን ቃል በመፈጸም እንጂ በኪዳኑ ዝግ ስበስባ አይመጣም። ለዛውም እኔን ተጸይፈህኝ?
የምርምሩ ምጡቅ ጥበብ የቅኔ ጉባኤ ብርቅ አቀራረብ።

Tech Science TV Program Episode 39
የእኔ ቅኖች አጅግ የምናፍቃችሁ የሐገሬ ማሮች … ይህ የኢትዮጵያዊ ሥነ – ምርምራዊ አመክንዮዊ ጉባኤ ከሰርከኛው፤ ከወትሮኛው ዘዬ በእጅጉ የተለዬ ነበር። ውስጠ – መቅደሱ የታደመበት ሥነ – ጥበብ መጥምቁ ዮሓንስን ተከትሏል። እኔን ያግባባኝ መንገድ የዚህ ጉባኤ የዕልፍኙ ስፋት፤ የግድግዳው የቀለም ጸጥታዊ ስበት፤ የወለሉ ንጽህና ውበትና ማራኪነት፤ የወንበሩ ምቾትና ደልዳላነት፤ የድምጽ ማጉያው ጥራት፤ ድምቀትና ዘመናዊነት አልነበረም። እኔን የማረከኝ ወይንም እኔን ሳብ ያደረገኝ ብልህ ብሂል አለ። ህንፃውማ ተዚህም አለ። አዳራሹም እንዲሁ። ቀለማም ውበቶችም አሉ በአይነት ተዚህ ተሲዊዚዬ። ቤቴም ቤተ መቅደሴም በራሴ የቀለም ውበት ንድፍ የተጠበበች ስለሆነ ከጸጥታዋ ጋር ልኳን ጠብቃ ግን ተናፋቂነቷ ልባዊነት ነው። ስለዚህ ማርኮቴ ሌልኛ ነው። ቀደምቷ ሐገር ኢትዮጵያ የጠፈር ቀደምት ሳይንቲስትነቷ ተባ፤ ኢትዮጵያ ዛሬም አንደ ትናንቱ በጥበብ አውደ ምህርት፤ በልቅና ሠረጋላ የአደራን ዕዳን በአደራ ጥራት ለማሰቀጠል የጉባኤው ባልድርሻ የሆነው ዜግነታዊነት ሳይንስና ቴክኖሎጂ የተነሳበት ዓላማ እና ግቡ፤ የነገ የትውልዱ በኸረ ጭንቀቴ ስለሆነ ድርጁነቱ በመሪነት በህብሬነት መስከኑ ነው ትንፋሼ የሆነው። እርግጥ ዛሬ ዶር አብይ አህመድ ከድርጅቱ ውስጥ የሉም። በነበራቸው አጭር ቆይታ ግን ኢትዮጵያዊ ዜግነትን በጽኑ አለት አማካሉት ለመጀመሪያ ጊዜ ከ27 የእንግልት ዘመን። ኢትዮጵያዊ ዜግነትን ታቦት ቀረጹለት። ኢትዮጵያዊ ዜግነት መፍሄነቱን በተጋድሎ አበሰሩት። መሰረትን በህሊናቸው ሰንቀው፤ ሃሳብን ዕውን አደረጉት፤ የአባቶቻቸውን አደራ በአደራ አበቀሉት በንጽህና ቅንነት። በሌላ በኩል ይህ ብቃት ታሪካችን ስለሆነ በቅጡና በወጉ የህሊናቸው ለምነት በቅኝት ዘክርን ነገን በውል አናስበው ዘንድ የተስፋ ኪዳናችን ጽንሰት ስለሚያፋፋልን ነው የመረጥኩት። ጥቂት የአትኩሮት አውደ ምህረቶችን ለመነሻነት ባነሳሳስ?
ዓላማው ሆነ ግቡ ኢትዮጵያ ከጥንት አስተዛሬ በኢትዮጵያ የመንፈስ ጥሪት ከመነሻው ብቻ የተነሳ መሆኑ ዕጹብ ነው። ኩረጃ የለበትም። ወይንም ቅጂ አይደለም!
የጥብብ ልቅናው አወቃቀር ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቅ ብሄራዊ ጉባኤ በቅኔ ውበት፤ በሥነ – ግጥም ነግሦ፤ ውስጥን አናቦ፤ ከተልዕኮው ጋር ተናቦ፤ ከህሊና ተደርሶ – ለህሊና አድርሶ፤ ባንጎል ታስቦ – ተሰልቶ – ተደራጅቶ – ተሰብሎ፤ ሊሂቅንን ከእውነት ከልባዊነት አብቅሎ አህዱን … ክለቱ እያለ ርቱ ሲል እጬጌውን ኢትዮጵያዊነትን በውስጥ ስለወስጥ፤ ስለተስፋ ሆንክን ስለማለት አብሥሮ፤ ችሎት በማሆን ማለሙ ሲሳላ መቸቱ ልዩ ነው፤

Ministry of Science and Technogy(MOST), Leadership and Motivation Program
በወንዶች ዓለም ሴቶች ያላቸውን ዕምቅ ሃብት አናይ ዘንድ ዕውቅና ሰጥቶ ለዚህ ስላበቃን፤ የሰማዮዋ ጠሐይ መሬት ላይ ወርዳ ሃብታችን እንደትሆን፤ የእኛ እንድንላት፤ እኛም አለንበት፤ ቤተኛ ነን እንል ዘንድ ለዚህ ስላበቃን የሰማይ ታምር ነው፤ ክብሩ ይስፋ አማኑኤል አባቴ። አሜን!
የኢትዮጵያ የሳይንቲስትነት አቅም ጥልቅነት የመነሻውን ቀደምትነት ይህ ጉባኤ ስለ አጰጰሰው፤ ኢትዮጵያዊ ትውፊትን መርጆ ህላዊነቱ እንዲሆን ስለፈቀደ ከገድል በላይ ነው – ለእኔ።
የዶር. አብይ ትርጉም የህሊናቸው ልሳነ – መሬት፤ የነባቢነታቸው ሥናዊ – አምክንዮ፤ ክህሎትን በልቅና፤ ልቅናውን በኪናዊ እኛነት፤ እኛነቱን በነጠረ ማግስታዊነት ባዘቶ፤ ወርቅና ፈትሉን አስማምቶ በምለስት ቃኝቶ አሸምነ። ስለሆነም ሙቀት ፈጥሮ ሙቀት እንዲሆነን ቅኖች ከልባችን ፈቅደን። ስለምን? ነፍስ ፈጥሮ፤ ነፍስ ሆኖ፤ ነፍሳችን ስለመለሰልን – የቅኖችን። መሪትነት በዚህ መስመር ይመጣል ተብሎ ብዙም ባይታሰብ „ጊዜ ገቢረ ለእግዚአብሄር“ እንሆ ሆነ። ተመስገን! ጊዜ ታሪክን ይሠራል።
„ከእርምጃ ወደ ሩጫ አብረን አንሩጥ!“  ነው የሚለው መራሂ ግብሩ ወይንም የማዕዶቱ እልፍኝ ማህንዲስ። ለዚህም ጥልቀታችን በልቦና ሙሉዑነት፤ በደምና በሥጋችን ውስጥ ዘልቀን እናይ ዘንድ ሲፈቅድልን፤ አደብ ገዝተን፤ በተደሞ ሆነን፤ አርምሞን አስብከን ለውስጣችን ውስጣችነን አንተርሰን፤ በሚስጢራችን ረቂቅ ተሰጥዖ መፈረሽ የኛ ፈንታ ነው። የቻላችሁ፤ የወደዳችሁ ሚስጢርነታችን፤ ረቂቅነታችን ስለምን ስለመሆኑ ጊዜ ወስዳችሁ ታዳምጡት ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃችኋዋለሁ። ዶር. አብይ አህመድ አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አቅምን በአቅም አደራጅተው እርግጠኛ የሆነ ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ለመፍጠር ያደረጉትን ጥረት በዚህ ውስጥ ማዬት ይቻላል። የቤት ሥራውን ለእናንተው ለእኔዎቹ ለቅኖቹ እሰጣለሁ። የተወያዮችን መንፈስ በምን ሁኔታ፤ በአክብሮት አንደ ተቃኙትም መጨረሻ ላይ የሰጡትን ጥቅል የማጠቃለያ ሃሳብ፤ በህሊና የቃለ ጉባኤ ጸሐፍትነታቸውን ስተመረምሩት የአዳምጭነታቸውን፤ የአትኩሮታቸውን የማሰብ አቅማቸውን፤ የማወራረስና የማዛማድ ተደሟዊ ጸጋቸውን ማዬት ትችላላችሁ፤ ደጋግማችሁ ስታዳምጡት። ፍሬዘሩን፤ ፍሬ ነገሩን መስህብ ውሉ ይገለጥላችኋዋል። ስለሆነም ዛሬ እኔ በዚህ ዙሪያ ከዶር. አብይ አህመድ ጥቂት ነገር ብቻ አንስቼ በልዕልቴ፤ በመራሂተ በወ/ሮ ጽዮን ተክሎ የመንፈስ ቅድስና ላይ ትንሽ እልና የሚያሰጋኝን ነገር አንስቼ ዕለቱ በርቱ ይከዋናል።
„ሳይንቲስት ለመሆን ሰው ብቻ መሆን በቂ ነው።“  ከመራሂተ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ።
ይሄ ነው የዶር. አብይ ጥልቅ ሚስጢር። በወንዶች ዓለም የሴችን አርቆ የማሰብ፤ የማስተዋል፤ የምርምር ማዕክልነት የማዬት፤ ሴቶች በምናብ ተጉዞው ከለምንም የመገናኛ ዘዴ በስሜት ለስሜት ሃዲድ የመዘርጋት ቀያሽ ርቁቅ ተፈጥሯዊ የግንኙነት ብቃት እዳላቸው፤ መጠበብን አስመልክቶ ከውስጣቸው የተቀበሉበትን ምልከታ፤ ለማስረጃነት መሬት ላይ ክንውኑን ማዬት ያስችላል። ሴቶችን ከውስጥ መቀበል አትራፊ ብቻ ሳይሆን፤ ትውልድንም አጽዳቂ ስለመሆኑ ያሉትን በመሆን ቃላቸውን ያከበረቡት መታመንን ያበለጸጉ ብቸኛ ታላቅ ሰው መሆናቸውን ማዬት ያስችላል። ለሴቶች አቅም ዕውቅና መስጠት፤ የሴቶችን የእውቀት ሃይል ማመን። ውስጣቸውን መውደድ። ምናባቸውን ማፍቀር በተጨባጭ ያሰዬናል ይህ የዶር አብይ አህመድ እርምጃ። ስለሆነም ከዶር. አብይ አህመድ መንፈስ ውስጥ የእኩልነታችን፤ የአቅማችን፤ የብቃታችን፤ የማድረግ ተስጦዖችን፤ የመፍትሄ አመንጭነታችን ትንሳኤ እንዳለንም ቅኖች በድፈርት እንዲህ እንናገራዋለን። እንሰብከዋለን። የሴቶች የሰማይ መንፈሳዊ ባለጸግነት በታማኝነት በማብቀል የመጀመሪያው ሐዋርያችን ናቸው እና የእኛ ዶር. አብይ አህመድ። በህልም አለም መኖር ለገለማን፤ ላንገሸገሸን ግዕፋን ሴቶች አብይ ብሌናች! አብይ ህሊናችን! አብይ ክስተታችን ነው! አብይ አዲስ ቀናችን ነው! አብይ አዲስ ዘመናችን ነው! አብይ አውራችን ነው! ተመስገን!
የእኔ የተግባር ልዕልት ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ ተወዳጅ የሚያደርግ የአቀረረብ ልቅና፤ የልሳን ጣዕም፤ የሰብዕና ክህሎት፤  የአገላለጽ ውበት፤ የድምጽ ቅኔዊ ቃና ዜማዊ ምትሃቱ ማረከኝ እና ሙሉውን እንዲህ አቀረብኩት። ስታዮዋቸው ደግሞ ተመስገን ትላለችሁ። እርጋታቸው አንዳች ሳቢ ነገር አለው። አዎን በርግጥም ሙሉዑ አቅም ሀገር ቤት አለ። ትውስት የማይፈልግ። እንዲህም ይላሉ መራሂተ ቅኔ ወ/ሮ ፅዮን ተክሉ …
„ራስን መገምገም በምን አንጻር ማደረግ አለባችሁ፤ በእነዚህ ኢንተሌጄንስ ውስጥ እራሳችሁን የቱ ጋ ታገኙት አላችሁ?  ማናችንም አድገን አልጨረስንም! የትዮኞቻችንም ፉሊ ዴቮሎፕ አላደርግንም! ሁልጊዜ ፐርሰናል ዴቨሎፕመንት የሚቀጥል ነገር ነው! ስለዚህ እኔ ሳዬው የትኛው ነው ሚሲንግ ፒስ ከእኔ ውስጥ የጠፋው ነገር ምንድን ነው? ከባጠቃላይ ሲብል ሰርቨንት ውስጥ ምንድን ነው የጠፋው? ከኢትዮጵያኖች ምን የጎደለ ነገር አለ? አሁን ወደ ራሳችን እንድንመለከት እፈልጋለሁ፤ አስተማሪዎች ነን፤ ለምንድነው ልጆቻችን ማብቃት ያቃተን፤ ተማሪዎችን። አለቆች ነን ለምንድነው ሰራተኞቻችነን ፉሊ ማድረግ ያቃተን፤ ያልቻልነው። እነዚህን ነገሮች አንድንጠይቅ፤ ራሳችን ስንጠይቅ ስንመለከት ምን ይታዬናል? „ድመት ሆነን አንበሳ ነው የሚታዬን? ወይንስ አንበሳ ሆነን ድመት ይታዬናል? ወይንስ ሰው ሆነን ሰው ይታዬናል? ስለሳይንስ ስናወራ፤ ሳይንቲስት ለመሆን ሰው ብቻ  መሆን በቂ ነው። ማሰብ፣ ሃሳብን ማደራጀት፤ በምክንያት ማስቀመጥ፤ ከዛ በኋዋላ ደግሞ ማስተላለፍ።“ ይሄ በዬትኛውም መንገድ ብትሄዱ፤ ሳይንቲስት ያደርጋችኋዋል። Max Black የሚባል ሳይንቲስት / ፈላስፋ/ ስለሳይንስ ሲናገር ምን አለ? ሳይንቲስቶች፤ ንጹህ የጠራ ምናዐብ አላቸው አለ። ማለት ያልተዛባ፤ ያልቆሸሸ፤ ያልዘገጠ ታውቃላችሁ ቆሻሻ የሌለበት፤ ያነን የጠራ ምናዐብ አዲስን ሃሳብ ለማፍለቅ ካለው የሚቀንሱ ሳይሆኑ፤ ጥበባዊ የፈጠራ ምንዐብ ያላቸው ሰዎች ሳይንቲስቶች ናቸው። እና አብረን እንዴት ነው የምንሮጠው? ስንሮጥስ መሮጥ ብቻ ነው የምንፈልገው? ወይንስ መድረስ የምንፈልገብት ቦታ አለ? ለመሮጥ ምን ኢኪዩብመንት ያስፈልገናል? ሰው አንድ ቦታ ለመድረስ ሲፈልግ፤ መጀመሪያ ራሱን ማዘጋጀት አለበት፤ ስለዚህ ርምጃችን ወደ ሩጫ አንዲቀየር፤ ሩጫውም ዝም ብሎ መንገድ ላይ ማህል ላይ የሚቀር ሳይሆን እስከምንፈልግበት ድረስ መሮጥ እንድንችል የሚያደርግ ነገር ያስፈልገናል፤ ማለት ነው። ስለዚህ የሳይንስና የቴክኖሎጂ ጉዳይን ቀለል ካደረግነው ችግር የመፍታት ጉዳይ ከሆነ፤  እጃችን ላይ ያሉት ትሎች እኛ ራሳችን ሰው መሆናችን ማሰባቸን አይምሯችን፤ ይሄ ሃርድ ዌር የተባለው ነገር ኢንባይሮመንታችን ያሉት  ያላቸው ነገር ለመፍጠር ለመፈልሰፍ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለመሮጥ በቂ ናቸው።“
ቢስ አይይብን። እያንዳንዱ አረፍተ ነገር ልዩ አቅም፤ ሃይል ይሰጣል። ተስፋን ያፋፋል። ያነሳሳል። ሙቀት ይሰጣል። አይዛችሁ ይላል። በተለይ በዝምታ ውስጥ ማሰብ ለሚወዱ፤ በጸጥታ ውስጥ ማግስት ለሚያሳስባቸው፤ በመመሰጥ ውስጥ ደርሻ ለሚሞግታቸው አጽናኝ ነው። „ድመት ሆነን አንበሳ ነው የሚታዬን አንበሳ ሆነን ድመት? ወይንስ ሰው ሆነን ሰው ይታዬናል?“ ይገርማል። ይደንቃል። እንኳንም የኔ ሆኑ። „ሰውነታችን ማዕከል አድርገን እንነሳ ነው“ ቢሆንማ ነበር ግን አልተቻለም። ለመሆኑ ሰው ስስ ወይንስ ድርብ ነው?
„ሳይንቲስት ለመሆን ሰው ብቻ  መሆን በቂ ነው።“ ይህ አገላለጽ የቀስተዳመና ፓርቲ የተመሠረተበትን፤ በኋዋላም ቅንጅት ያዘከረውን፤ ከዛም ግንቦት 7 የቆመሰበትን፤ አሁን አሁን ደግሞ ኢሳትም የተጋባበትን ሰውን በዲግሪው ብቻ የመለካት የፕ/ መስፍን ወልደማርያም ከፋይ ዕሳቤ የናደ ብቻ ሳይሆን የደረመሰም ነው። የኢትዮጵያ ሳይንቲሰት፤ ፈላስፋ ዓራት ዓይናማ የሀገር መሪዎች፤ የሃይማኖት መሪዎች የነበራት ሐገር ናት። ምስክሮቹ እኛው ራሳችን መኖራችን በቂ ነው ኢትዮጵያዊ ተብለን። ኢትዮጵያ ተብላ። እንኳንስ „መጸሐፈ ፈውስ“ እነ ፋሲል፤ ላሊበላ፤ አክሱም፤ በርካታ ገደማት እያሉ። አባቶቻችን በዲግሪያቸው ተለክተው፤ በሰርትፊኬት ተመዝነው ሳይሆን በሥነ – አዕምሯቸው የልቅና ብቃት እስከ 500 ዓመት ብንቆይ እንኳን እንሱ የሠሩትን ዕጹብ ድንቅ ተግባር መከወን ቀርቶ የእውቀት ዓውደ ምህረቱ ሳይቀር ዛሬ ወርዶ ቁልቁል የጦርነት ቀጠናው ምክንያታዊነት ሆኗል፤ ለሰሚውም ግራ ግራር።
ያ  የአባቶቻችን ልቅና ትውፊት፤ ዕሴት፤ አስተምህሮት ዛሬ በለጸጉ፤ ለሙ፤ አደጉ ከሚባሉት ዩነቨርስቲዎች ተመርቀውበት አይደለም። አልነበረምም። ዛሬ ካለ ወረቀት በራስ እራስ አስተዳደር የመሳተፍ ዕድሉ የለም። ስንቱ ህዝብ ተምሯል ሲባል ደግሞ አንኳንስ ኢትዮጵያ ውጪ ሐገርም ዕድሉ ከሌለ የለም ነው። ስለዚህ ይህ ማህበረሰብ ባለቤት አልቦሽ ስለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ሥነ – ልቦናው ስበብ አስባብ እዬተፈለገ ተቀጥቅጧል። ይህን ቅጥቅጥ ነው ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ በመንፈስ ልዕልና ህክምና የፈወሱት። ብሩክ ነፍስ። „ማናችንም አድገን አልጨረስንም!“
ይህ የወ/ሮ ጽዮን ተክሉ ፍልስፍና እያዳመጥኩ አንድ ነገር ሞገተኝ። ለመሆኑ „የመጀመሪያው ኮንፒትር በማን ተሰራ?“ ብዬ አሰብኩኝ። ለእኔ የመጀመሪያው ኮንፒተር ፈጣሪ አምላክ ነው ብዬም ተቀበልኩት። „እንዴት?“ ብዬ አሁንም እራሴኑ ሞገትኩት? ሰውን እንደ አምሳሉ አድርጎ ሲፈጥረው ተፈጠረ ብዬ መደምደሚያ ላይ ደረስኩኝ። አሁንም „በምን ሂሳብ?“ ብዬ ተጠዬቅ አልኩት እኔኑ፤ አዎን ትልቁ ኮንፒተር የሰው ጭንቅላት ነው ወ/ሮ ፅዮን ተክሉ እንዳሉት። ትልቁ ኮንፒተር በሥነ – ዕዕምሮ ዋና ማዘዣ ጣቢያ ሆኖ ሌሎች ደግሞ አሉ ብዬም በመለጠቅ አሰብኩኝ። ልክ ሂሳብ ማስያ፤ ትኬት መቁረጫ፤ የስኳር ደም መጠን መለኪያ፤ ሞባይል፤ የሙቀት መጠን መለኪያ እነዚህ ሁሉ እኮ እንደ አቅማቸው ኮንፒተር ናቸው። ስለዚህም ልብ አንድ ኮንፒተር አለው፤ ሳንባ፤ እንኩላሊት፤ አንጀት፤ ማህጸን፤ ጨጓራ፤ ጣፊያ እያልን ስንሂድ ሰው በብዙ ተፈጥሯዊ ኮንፒተር ተገነባ ነው ብዬ አሰብኩኝ። እነኝህ የሰው አዕምሮ የሠራቸው ሳይሆኑ በፈጣሪ ረቂቅ ጥበብ የተሠሩ ናቸው፤ በእጃችን ያሉት ሞባይል ኮንፒተር ግን የሰው ልጅ የሥነ – ዐዕምሮ ሁለተኛ ደረጃ የፈጠራ ውጤቶች ናቸው። የሚያገናኛቸው ለእኔ ሁሎችም ሃይል ሰጪ/ ደጋፊ የሚስፈልጋቸው ስለመሆኑ ሲሆን፤ ባትሪ፤ ኤለትሪክ ሃይል፤ ምግብና መጠጥ ንጹህ አየር፤ ሲበላሹ/ ሲታመሙ በሂደት የመጠገን፤ ሲያበቁ ደግሞ ወይንም ከአግልግሎት ውጪ የመሆን፤ የማራጀት እጣቸውም በተመሳሳይነት ማዬት ይቻላል። ስለዚህ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ ያሉት ነገር ከልብ የሚገባ ነው። ሰው ሥነ – አዕምሮውን ማሰራት ከቻለ ሳይንቲስት፤ ፈላስፋ መሆን ለመቻል የሚያገተው አንዳችም የሰርትፌከት ማነቆ ነገር የለበትም። በዚህ መስተጋብር የቅርብና የሩቅ ወገንተኛ እና ነጣይ አስተምኽሮችን መፍጠር ከሰውነት ፍልስፍና ከፈጣሪ ሰውን የመፍጠር አቅም ጋር መፈታታን ይሆናል። ማኽከነ!
„ዋልድባና ቦረና የጠፈር ምርምር መሰረተ ሃሳብ ብቻ ሳይሆን፤ እጅግ ሞጋች አምክንዮ ባለሀብቶች ናቸው።“
„ካለንደር ስል በሥነ ፈለክ ሳይንስ Astronomical Science በቦረና እና በወላድባ አካባቢ የተገኙት መረጃዎች አንደሚያመለክቱት፤ ኢትዮጵያም ከራሽያም፤ ከአሜሪካንም በፊት በስፔስ ሳይንስ የጠለቀ እውቀት ያላቸው ወላጆች የተሻለ ዕውቀት እንደነበራቸው የሚያመላክቱ መረጃዎች እዬተገኙ ነው። ለምሳሌ በቦረና ተማርን የምትሉ ሰዎች የውለደት ቀናችሁን የምታከብሩት ተሳስታችኋዋል፤ ግንቦት ስምንት ዛሬ እና ግንቦት ስምነት በሚቀጥለው ዓመት የተለያዩ ስታሮች፣ ጋላክሲዎች፣ ኮኮቦች የሚያርፉበት ስለሆነ በፍጹም ቀኑ አንድ አይደለም። የሚል ተማርን የምንል ሰዎችን የሞሞግት /ቻሌንጅ/ የሚያደርግ ሃሳብ ያነሳሉ።“
የዶር. አብይ አህመድን ሃሳብ ለማጠናከር ትንሽ የመጀመሪያው አብርንታት ዋልድባ ገደም የተመሰረተበት ዘመኑ ቀደምትነትን በጠረፍ ምርምር ዕይታ ጉልበት ይሰጠዋል ብዬ አስባለሁ። ቅደመ ዓለም፣ ማዕከለ ዓለም፤ ድህረ ዓለም የሁሉ ጌታ መዳህኒተ ዓለም ሥልጣን ነው። ዋልድባን በሚመለከት አባታችን የገደመው ገዳም ነው የሚል ቃለ ህይወት ነው ያለው። እከሌ በሚባል ንጉሥ ተገደመም የሚል ታሪክ የለም ይላሉ የቤተክርስትያን ሊሂቃን። በሁለተኛ ደረጃ የኢትዮጵያን ህላዊነትንም አመክንዮ አባቶቻችን እንዲህ ነው የሚገልጹት ..
„አትዮጵያ በ፫ ሺህ 3000 ዘመን ነፃነቷን ጠብቃ ተቀምጣለች እዬተባለ የሚነገረው ፩ኛ (1)ከሰብታህ ጀምሮ እስከ ጲኦረ ድረስ የነበረውን ፭፻፰ (508) ዘመን፤ ፪ኛ (2) ከትንሹ ሳባ ጀምሮ እስከ ንግሥት ሳባ ወይም እስከ ንግሥት ማክዳ ድረስ የነበረውን ፰፻፶፪ (852) ዓመት በድምሩ ፩ሺ፬፻፲፪ (1412) ዓመት ሳይጨምር ከቀዳማዊ ሚኒሊክ ጀምሮ አስከ አሁን ያለውን ጊዜ ብቻ በማሰብ ነው እንጂ፤ ኢትዮጵያ የምድሯና የባህሯ የአዬሯ ዳር ድንበር ታወቆ መንግሥቷ ተቋቁሞ ነፃነቷን ተጥብቆ መኖር ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የአለው ዘመን ፬ሺ፫፻፺፫ ነው (4393) ነው“
በዬትኛውም ንጉሥ ሥም ወይንም ፈቃድ ተገደመ የማይባለው አብርነታት ዋልድባ ገዳም ቀደምትነቱ በፈጣሪ በራሱ እንደተገደመ ነው አባቶቻችን ያቆዩልን። „ይህ ገደም የተገደመው ፬፻፹፭  (485) ዓ.ም ስለሆነ ይህ ገዳም የሚለው ቃል የተነገረው ገዳሙ ከመገደሙ ፬፻፹ (480) ዓ.ም በፊት  ነው ማለት ነው።“ አባቶቻችን በአጽህኖት ይህን ጽፈውታል።
ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ ከዚህ ጥልቅ ሚስጢር ለመነሳት የፈቀዱትን ዶር አብይ አህመድን ስትዘነጥል ስንት ነገር እናዳናጋህ ማዬት አለብህ፤ በማንፌስቶ ፍቅር ብቻ ሰው አይለካም። ሰው አይመዘንም። በጣም ተለላለፍክ – በድፍረት።
የኔዎቹ ቅኖቹ ከላይ ያነሳኋቸው የዶር አብይ አህመድን መሠረተ ሃሳብ ለማፋፋት የተጠቀምኩበት ማስረጃ ግማሹን በድምጽ ስለሰራሁት እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ በዚኸው በሳተናው ማሳ አቀርብላችሁና ፈቅዳቸሁ፤ ወዳችሁ የማንነታችን ጥልቅነት የራሳችሁ ለማድረግ ትተጋላችሁ ብየ አስባለሁ። ጉዳዬን ስከውን። ይሄ ነው የዶር አብይ አህመድን የአዲስ ዘመን ልዩ ክስተት እንድንላቸው እምንፈቅደው። ይሄ ሚስጢራዊ እራስን የማዬት ማሾነት ነው ተቀናቃኝ ሆኖ የወጣውን የጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ ሃሳብ ልሞግተው ያነሳሳኝ። ኢትዮጵያ ቀደምት የሥነ – ጠረፍ ሳይንቲስት መሆኗ፤ ብቻ ሳይሆን ዛሬም ሳይንቲስቶች ያልደረሱበት ግን በኢትዮጵውያን ቀድሞ የተሠራ የህሊና ተግባር መሆኑን እናያለን። በዬአመቱ ቀኖች ሲመጡና ሲሄዱ፤ የክዋክብቶች ተጽዕኖ በአፈጣጠራችን፤ በባህሪያችን በብቃታችን ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዖኖ እነሱ ቀድመው አይተውታል። ጠፈርን እጅግ በሚገርም ምጥቀት በመንፈስ ቅዱስ ሃይልም ተማራምረውታል። ምርምሩ ደግሞ መሬት በራሷ እንዝርት ስትዞር የሚያመጣውን ቀናዊ፤ ወራታዊ፤ ወቅታዊ ሁኔታ ደግሞ በሌላ መንገድ አይተውታል። ይህ ኢትዮጵያን የእኔ ያለ ሁሉ አንጡራ ሃብቱ ነው። አንገቱን የማይደፋበት፤ እሱነቱን በርግጠኝነት በደም ማህተም የሚትምበት። ገና አለም ተመራምሮ ያልደረሰበትም ቅምጥ የምርምር ቅርስ  በእጃችን አለን ነው የሚሉት ዶር አብይ አህመድ። ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው ያመጣው ጉርፍ ነው የምትለው ዕሳቤ በዚህ ወድቆ እንዳይነሳ ሆኖ አቧራ ለብሷል ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ።
ይልቅ አሁንም በእኔ መንፈስ ውስጥ የሚመላለሱብኝ፤ የሚሞግቱኝ አብይ ጉዳዮች አሉ። የኮከብ ባህሪያትን ማጥናት አትኩሮት አለኝ። ይሄን ዛሬ ስለተነሳ ሳይሆን ሀገር ቤት እያለሁ „አዕምሮ“ ጋዜጣ ላይ „ ጋዜጠኛ አብርሃም ጉዝጉዜ“ የሚባል ዬዩንቨርስቲ መምህር ይመስለኛል የሊንዳን የኮከብ መጸሐፍ ይተረጉመው ነበር። ቅዳሜ ጥዋት ከድል ገብያ ገብርኤል ሜክሲኮ አደባባይ የሚቀድመኝ አልነበረም። ሂጄ እምገዛው ለኮከብ ትንተናው ፍቅር ስለነበረኝ ነው። የእኔን ኮከብ „ንጹሃን“ ብሎ ነበር የጀመረው። ዝርዝሩ ውስጥ „ቤት መቀመጥ አይወዱም“ ይላል። ይሄ ደግሞ የእኔ ሰብዕና አይደለም። የማይስለቸኝ ነገር ቢኖር ቤት መቀመጥና ጸጥታ ነው፤ ዘም ማለት። በጸጥታ ማሰብ እፈልጋለሁ። ሰው ቤት መሄድ አልደፈርም፤ በሁኔታዎች አስገዳጅነት አልፎ አልፎ ስሄድ ሲጨንቀኝ እዛው ሆኜ መጸዳጃ ቤት ከፍቼ ለረጅም ጊዜ በመስኮት እቆማለሁ። ስለሆነም ከእኔ ሰብዕን ጋር በፍጹም ሁኔታ የማይመስል ነበር። ጋሼ አብርሃምን ሞገትኩት ያን ጊዜ ሥርጉት እርቂሁን ይባል ነበር የብዕር ሥሜ፤ በለገዳዲም ጹሑፎች ይቀርብ ነበር በዚህ ሥም፤ እርቂሁን የአርበኛው የእሚታዬ ሥም ነበር። እና አንዲህ ብዬ ጻፍኩለት „ዟሪ“ አይደለሁም። ከሰው ጋር ቀጠሮ ከኖረኝ ራሱ ምክንያት ፈልጌ ነው የምቀረው። ሳስበው እኔ በተወለድኩበት ወራት የተወለዱ ልጆች የሰዓት ልዩነትም አለው። ስለዚህ በወል እምንጋራው ባህሪ ሲኖር የተወለድንበት ሰዓት፤ በውስጡ ባሉ ሰከንዶችም የተጠጋጉ ፕላኔቶች፤ ኮከቦች ተጽዕኖ ልዩነት ያመጣል ብዬ ነበር የጻፍኩለት። በአንድ ቀን ውስጥ እንኳን 24 ሰዓት አለ። በ24 ሰዓት ውስጥ ደግሞ ወደ 440 ሰከንዶች አሉ። በስከንዶች ውስጥም ልዩነት አለ። በአንደኛው በሶስተኛው እያለ ስለዚህ ምርምሩን አንዳለ መቀበል ብቻ ሳይሆን፤ አንደ መነሻ ወስዶ ክፍልፋዮች የሚያመጡትንም የለውጥ ድምፆች በጥልቀት መርመርምር አስፈላጊ ነው ብዬ ስለማምን ነበር ለጋሼ አብርሃም የጻፍኩለት። እሱ በእውነተኛው ስሜ አግኘቶ ሊያወያዬኝ ፈልጎ ነበር፤ እኔ ደግሞ ቁጥብነቴ ቃላት የለውም። አልደፍረውም እንደዚህ ዓይነቱን ነገር። እንኳን ያን ጊዜ በወጣትነት ዛሬም በሙሉ ዕድሜ ችግር አለብኝ። ስለዚህ ሳንገናኝ ቀረን። እሱ ፈልጎ ነበር ክርክሩን፤ እኔ ደግሞ ፈቃድ አልሰጠሁትም።
የሆነ ሆኖ የዶር አብይ አህመድ ራስን ማዬት፤ ራስን ማስጠጋት፤ ራስን መዋጥ፤ ራስን እንደ ንጹሕ አዬር መማግ፤ እንደራስ ለመኖር መደሰት። አንዳለኝ ለመኖር መሆንን መወሰን። በመሆን ውስጥ ራስን በመቀበል በውስጡ መጽደቅ ከተፈቀደ በራስ መተማመን አቅሙ በራሱ መንገድ ሙሉዑ ሰብዕናን ያጎናጽፋል። የተመጣጠነ ስብዕና ደግሞ እንዲህ መሬት ይዞ በጽናት እንዲቆም ያደርጋል። ሌላ የተመሰጥኩበት የሀገር የአደራ ባለ ዕዳ ከፋይነት፤ ከእናታቸው ለሰፈር ከሚልኩት የቅመሱልኝ፤ ከጎረቤት በመልስ ከሚጣው የሐሤት ቅብብል ጋር እንዴት እንዳወደዱት ከታምር በላይ ነው። ይኑርልን። አትኩሮታቸው አጅግ መጠነ ሰፊ ነው። በዚህ መሃል ግን  ስጋት አለብኝ … እንዳይነጥቁን …
ሰለስጋት።
መቼም ይህን ብቃት ኤርትራዊው አቶ በረከት ስምዖን ለደቂቃም ከጥቃት ሳት አይሉለትም። የሳይንቲስት ኢንጂነር ቅጣው እጅጉ ሞት፤ የአቶ አንዱ ዓለም አራጌ የዕድሜ ልክ እስራት፤ የአርበኛ አንዳርጋቸው ተላልፎ መሰጠት፤ የአቶ በቀለ ገርባ እስር፤ የዶር መራራ ጉዲና እስር፤ የአቶ አሰፋ ጨቦ ሞት ከአቶ በረከት ስምዖን ኢትዮጵያን ከመሰለል ተልዕኮ ጋር የተዋዋለ ነው። ስለምን? ኢትዮጵያ በበቀሉ ብቁ ልጆቿ መብቀል፤ ማበብ፤ መለምልም ይህን ማዬት አይፈቅዱትም። የሻብያ ሰላይ ናቸውና።
ታዲያ ይህን ብቃት እንዲህ በቸልታ የሚታይ ይሆናልን? አይመስለኝም። አሁን ደግሞ ጠቢቡ ቴወድሮስ ካሳሁን ኤርትራ ናፈቀችኝ እያለን ነው።  „አይጥ ለሞቷ የድመት አፍንጫ ታሸታለች“ በሰላም ቢመለስ እንኳን የአንጀት በሽታውን ተሸክሞ ነው። ትዳሩም – ፍቅሩም – ህይወቱም ምስቅለቅል ነው የሚለው። ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ሌላ በሽታ የለባቸውም። ኢትዮጵያ ናት በሽታቸው። በዶር አብይ አህመድ የህይወት ጉዳይ ያንዣበበው አደጋ ከኤርትራ አስከ ኢትዮጵያ መረቡን የዘረጋ ነው ብዬ ነው እማምነው። እንዲህ አላሰቡትም የሴራ መርበኞች ዶር. መራራ ጉዲና፤ አቶ በቀለ ገርባ ሲታሰሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ኢትዮጵያዊነት ልቅናው ጎልቶ፤ ተደማጭነቱ ደምቆ የሚወጣ ወጣት ብቁ ኢትዮጵውያን ይኖራል ተብሎ አልታሰበም። አሁን ባልተሳበ ሁኔታ፤ ባልተሳበ ፍጥነት በዬደቂቃው የመንፈስ ጥሪቱና ለውጡ ከተገመተው እና ከተጠበቀው በላይ ነው። ሂደትን የሚጠበቁ የሁለመና ማስከኛ መቋጠሪያ ውሎችም በትቅቅፍ በአዎንታዊነት ችግኛቸው ለምለም ነው። ነገ ለሚያስፈራን አብሶ መከላከያ ውስጥ በራሱ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ውስጥ የዶር አብይን መንፈስን ለመጠበቅ የፈቀዱ ወገኖች መኖራቸው መልካምነቱ ሊመሳጠር የሚገባው ከዚህ አንጻር ነው። ይህ ብሄራዊ ስሜት ብቻ ነው የምህረት መሰላል። ይሄንን ማድመጥ ያስፈልጋል። ምክንያቱም ልብ ከሸፈተ መሰብሰብ አይቻልም። ዶር. አብይ አህመድም ራሳቸውን ከፈጣሪ በታች መጠበቅ ይገባቸዋል። ለሚሊዮኖች ድምጽ ሲሉ። በአቶ ለማ መንፈስ በዙም ስጋት የለብኝም፤ በተወሰነ ደረጃ የባለቤታቸው ነፍስ ጥግ ይሆናቸዋል ብዬ አስባለሁ። ይህንንም እንደመልካም አጋጣሚ ማዬቱ ይበጀናል።
የዶር አብይ አህመድ ጉዳይ እንኳንስ የወያኔ ሃርነት ትግራይ እና አቶ በረከት ስምዖን ጋዜጠኛ ማስረሻ አለሙ እኮ ያንገበገበው፤ የለበለበው ጨጓራውን የጠበሰው „የለማውያን“ አጀንዳ መሆን ነው። በዚህ ስሌት ማዕቀፉ ቡቃያ የማዬት ሳይሆን ተቀብሮ ወይንም ተሰናክሎ የማዬት ህልም ተለምዷል። እዚህ ውጪ ሀገር መፈናፈኛ የሌለውም ለዚህ ነው። ሃሳብ እንዳሻው የማይንሸራሸርው ማደግም ያልቻልነው። የሃሳብ እድገት እኮ የለም ከዚህ። ዝም ብሎ በዕምቅ ገድጓድ መማቀቅ። … የማይድን ምርቅዘት።
እርገት።
የኢትዮጵያ ሙሁራኑ ድምጽ 40 ዓመት ያልተደፈረውን ዕውነት አንድ ለአራት ሰሞኑን ሞግተው። ዕውነቱንም አፍልቀውታል። አዬዋ ወያኔ ዛሬስ ጆሮ አለህን? ግዴለህም አድምጠው። የምታውቀውን ብቻ ነው የምታውቀው። ጭካኔ። መክፈል። አጋ መለዬት። መግደልና ማሰር። ግን አሁንም ኢትዮጵያ በትግሬ የበላይነት ቅዝፈት ውስጥ ሰምጣ ሌሎቹ 79ኙ አቤት እያሉ ነው? ኤሉሄ እያሉ ነው። ትናንት ኢትዮጵያ የብሄረሰቦች እስር ቤት በማንፌስቶ ነበር። ዛሬ ግን 27 ዓመት ተኖረበት። ካድሬ ዕውነት አይደለም። መኖር ነው እውነት። የመኖርን እውነት ተቀበሉት ይሏችኋል። አራቱ ቅኖች ፈራ ተባ እያሉ በተመጠነችው የነፃነት ልክ። አንዱ ደግሞ አቶ አሰማህኝ አስረስ ለዛውም „የጋዜጠኝነት ተጋብቦት መምህር“ የጠጡትን መርዝ ያገሳሉ። አዝናለሁ የጋዜጠኛ መምህር ካድሬ¡ ያሳፍራል ጋዜጠኛ ተሁኖ ካድሬነትን መምረጥ፤ ሞት በስንት ጣዕሙ። መፍትሄውን ሳይሆን ገደሉን ነው እዬማሱት ያለው አቶ አሰማህኝ አስረስ። ማፈሪያ¡ አይኔን ግንባር ያድርገው፤ አልሰማሁም፤ አላዬሁም ይላሉ ሎሌነቱ ሆነ ግርድናው ተመችቷቸው። ይህ ለወያኔ ሃርነት ትግራይም አያድነውም። የሆነ ሆኖ የዶር አብይ አህመድ መሰረታዊ የተልዕኮ አቅም „ሰውን“ ማዕከል ማድረግ ነው። ይህ ደግሞ የመፍትሄ አደራዳሪ ብቻ ሳይሆን መፍትሄ ነው በራሱ። ሰውነት የድል መባቻ ነው። ሰዋዊነት የብሥራት ዓዋጅ ነው። በራስ ላይ ዘምቶ መለወጥ ትውልድነት ነው። ከነስንክሳሩ ሳይሆን ከራስ በሚጀምር የውስጥነት የማጽዳት ዘመቻ ብቻ ነገ ይገኛል። አይዋ ወያኔ አንተም እምልህን ስማ፤ ይሄ የቃላት ካብ የድቡሽት ቤት ነው – እሺ የሰሞኑ መግለጫህ ድርቆሽ።
http://www.satenaw.com/amharic/archives/43961
ወቅታዊ ውይይት -በአማራ ቴሌቪዥን።
„ማናችንም አድገን አልጨረስንም!“
(ከወ/ሮ ጽዮን ተክሉ ዓለም ዐቀፍ ድንቅ የምናብ ሰብል የተወሰደ።)
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ ቀድሞ ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
በማጠቃልያው እስክመለስ ድርስ እግዚአብሄር ይስጥልኝ፤ መሸቢያ ጊዜ።