January 5, 2018

Egyptian security forces [file photo]

ኤሊያስ ተስፋዬ እንደዘገበው

አል ፕረስ እንደዘገበዉ ከተባበሩት አረብ ኤምሬት ጋር ቅንጅት የፈጠረና በዘመናዊ የጦር ኃይል የተደራጀ የግብፅ ሰራዊት ዛሬ ኤርትራ ሰፍሯል::

አልፕሬስ አንዳንድ ምንጮችን ጠቅሳ እንደዘገበዉ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በግብፅና በሱዳን መንግስታት በተቃዋሚዎች መካከል ሰሞኑን ጉባኤ ተካሂዶ ነበር።

የቱርክ ወታደሮችም ሱአኪን በተሰኛዉ ደሴቷ ላይ እንዲሰሩ ሱዳን ፈቃድ መስጠቷን ተከትሎ ነዉ። ሶስቱ ጥምረቶች የኤርትራና የግብፅ ወታደሮች እንዲሰሩ የተስማሙት ነው የሚሉ ዘገባዎች እየተናፈሱ ነዉ።

አዲሱ የሱዳን ግድብ ከ20ኛዉ ክፍል ዘመን ጀመሮ ከመመስረቱ አስቀድሞ ሉአኪን የተሰኘዉ ደሴትና ወደብ በጥናታዊ ሱዳን በኦቶማን ኢምፓየር ሲተዳደር የኖረ ታላቅ የባህር በር እንደነበር ያታወቃል።

ቱርክ በሱአቢን ደሴት የጦር ቀጠና መመስረት እንደምትፈልግ ከዲፕሎሲ ምንጮች ያገኘዋቸዉ መረጃዎች አሉ ሲል አል ፕሬስ ዘግቧል::

በሱአቢን ወደብ ቱርኮች ከሰፈሩ በኋላ በአቡዳቢ፣ በካይሮባ በካርቱም መካከል ያለዉን ግንኙነት እያሻከረ መምጣቱ ተግጧል።

ባለፈዉ አመት ግንቦት ወር ላይ ግብጾች ኤርትራ ዉስጥ የጦር ቀጠና ለመመስረት እየተሯሯጡ ነዉ በሚል የወጡ ዘገባዎች የአገሪቱን የጦር ሰራዊት ማስተባበሉ ይታወቃል።

ግብፅ ሶማሊያና ጅቡቲ ዉስጥ ከ20ሺ ባላይ የሚሆኑ ወታደሮች መያዝ የሚችል ቀጠና ለመመስረት እየተጣደፈች ነዉ በሚል አንዳንድ የሱዳን ብዙሃን መገናኛዎች መጠቆማቸዉ ይታወሳል።

ግብፅ ከአባይ ዉሃ የምታገኝዉን ጥቅም በሕዳሴው ግድብ ሳቢያ እንዳይተጓጎል ድጋፍ ያደርግላት ዘንድ በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን ስትለማመጥ መክረሟ መዘገቡ አይዘነጋም:: ኢትዮጵያ በበኩሏ የግድቡ መገንባት ግብፅና ሱዳንን የኤሌትሪክ ሀይሎች ፍጆታ በማቅረብ ይጠቅማል እንጅ ጉዳት የለዉም ስትል መከራከሪያ ማቅረቧ ይታወሳል::