የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋ ከደህንነት ተቋሙ ሊሰናበት ወደ ሲቪል አስተዳደርነት ስልጣን ሊሸጋሸግ ነው።

image_pdf

የደህንነት ሹሙ አቶ ጌታቸው አሰፋ ከደህንነት ተቋሙ ሊሰናበት ወደ ሲቪል አስተዳደርነት ስልጣን ሊሸጋሸግ ነው። እጅግ ጨፍጫፊና አፋኝ ገዳይና አሳሪ የሆነውን የደህንነት ተቋም ሲመራ የቆየውና በርካታ አለም አቀፋዊና ሃገራዊ ወንጀሎች ላይ የተሳተፈው መልኩን ደብቆ እጅግ አደገኛ መንግስታዊ ሽብሮችን ሲፈፅምና ሲያስፈፅም የነበረው የደህንነት ሹሙ ጌታቸው አሰፋ ወደ ሲቪል አስተዳደርነት ስልጣን ሊሸጋሸግ መሆኑ ታውቋል።

የሕወሓትና የኢሕ አዴግ ጉባዬ ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ ፌዴራል ወይንም እንደ ደብረፂሆን ወደ ትግራይ ክልል ይመደባል የሚባለው ሰው በላው ጌታቸው አሰፋን የሚተካው የደቡብ ተወላጅ የሆነውና የደህንነት ተቋሙ ሶስተኛ ሰው እንደሆነ የሚነገርለት ያሬድ( ዘቢስት\አውሬው) በሚል የሚጠራ ግለሰብ እንደሆነ እየተነገረ ሲሆን ይህን ግለሰብ አብሮት የሚሰራው የጌታቸው አማካሪ የሆነ ግለሰብና ራሱ ጌታቸው አሰፋ ከጀርባ እንደሚያንቀሳቅሰው መረጃዎች ይጠቁማሉ። በሌላ ጥቆማ ጌታቸው ከደህንነት ስልጣኑ ከተነሳ ባለው የስልጣን ሽኩቻ መሰረት በከፍተኛ ሙስና የተዘፈቀው የሳሞራ ቡድን የራሱን የበላይነት ለማረጋገጥ ይጣደፋል ሲል መረጃው ይጠቁማል

በመቀሌው የሕወሓት ማራቶን\ስብሰባ ላይ በተወሰነው ውሳኔ መሰረት አብዛኛዎቹ አመራሮች ትኩረታቸውን ወደ ትግራይ በማድረግ ቀጣይ ስራቸውን ለመስራት ማቀዳቸው ይታወቃል። በክልል እንደለመዱት በፌዴራልም የብዓዴንና የኦሕዴድ አመራሮችን ወደ ከፍተኛ ስልጣን በማምጣት ከጀርባ ለመዘወር ይረዳናል ያሉትን የመዋቅር ንድፍ መስራታቸው ተሰምቷል። ወደ ሲቪል ስልጣን የሚመጡ ከፍተኛ የደህንነት ተሻሚዎች በርካታ መሆናቸውን የገለጸው መረጃው አቶ ጌታቸውን ወደ ሕወሓት አመራርነት ማምጣት የፖለቲካ ተሿሚ ለማድረግ ያቀደ መሆኑ ቀደም ብለው የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ።

#ምንሊክሳልሳዊ

No widget added yet.

← Ethiopia postpones elections for third time Geneva Press Club: Fear of State Collapse and Prospect of Democratic Transition in Ethiopia →

Leave A Reply

Comments are closed