January 16, 2018

 

~በፌደራል ደረጃ 115 ያህል እስረኞች ይፈታሉ ተብሎ ነበር!
~ሆኖው አንድ የእስረኛ ቤተሰብ ከእስረኞች ባገኘው መረጃ መሰረት እንደገለፀልኝ፣ ወደሰንዳፋ የተወሰዱት 111 እስረኞች ነበሩ!
~ ወደ ሰንዳፋ ከተወሰዱት መካከል ደግሞ በቂሊንጦ ቃጠሎ የተከሰሱት ዲንሳ ፉፋ እና ቶሎሳ በዳዳ ወደ ቂሊንጦ ተመልሰዋል! 109 እስረኞች ነው የሚፈቱት ማለት ነው! ከእነሱም መካከል ካልተቀነሰ ነው!
~ በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ 115 እስረኛን እንፈታለን ሲሉ ሌላ የሌለ ማስረጃ እንደጨመሩ እየተገለፀ ነው። አብዲሳ ቦካ በቂሊንጦ ቃጠሎ ወቅት በጥይት እንደተገደለ እስር ቤቱም አምኗል። 115 ተብሎ በተጠቀሰው ዝርዝር ውስጥ የቂሊንጦ እስር ቤት ያስገደለው አብዲሳ ቦካም ተጠርቷል ተብሏል። ወደ ማሰልጠኛ ተወሰዱ የተባሉት 111 ናቸው። በመግለጫው ደግኔሞ 115 ይፈታሉ ተብሏል። እንግዲህ አራቱ እንደ አብዲሳ ቦካ የተገደሉት ናቸው ማለት ነው። ትህነግ/ህወሓት የኢትዮጵያ ህዝብን ለማሞኘት የተገደሉትንም እፈታለሁ እያለ ነው! ቁማሩ በተገደሉትም እስከመቀለድ ነው!
——–
የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አቶ ጌታቸው አምባዬ 528 እስረኞች ክሳቸው ተቋርጦ ይለቀቃሉ ብለዋል። ጠቅላይ አቃቢ ህጉ የሚፈቱት እሰረኞች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ናቸው ብለዋል።
– ህገ-ምንግሥቱን ወይም ህገ-መንግሥታዊ ስርዓቱን የመናድ እንቅስቃሴ ላይ ያልተሳተፉ ወይም ያልመሩ
– በከፍተኛ የኢኮኖሚ አውታሮች ላይ ጉዳት ለማድረስ በተደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ ያልተሳተፉ ወይም ያልመሩ
– የሰው ህይወት ያላጠፉ ወይም በአካል ላይ ከባድ ጉዳት ያላደረሱ
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያሟሉ እስረኞች ከሁለት ቀናት የተሃድሶ ስልጠና በኋላ ይፈታሉ ተብሏል።
አቶ ጌታቸው አምባዬ በአሁኑ ሰዓት ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ሲሆን ሙሉ ዘገባው እንደደረሰን እናቀርባለን።