January 16, 2018

ከዳንኤል ጎበዜ፤ ከሰሜን አሜሪካ ፤ሚኒሶታ

የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ በወያኔ የዘር ፖለቲካ በዉስብስብ ችግሮች ተለጥጦ በየአቅጣጫዉ ተወጣጥሮ ባለበት ወቅት መቸና እንዴት እንደሚፈነዳ ቁሞ ከመተከዝ  ይልቅ አምባ ገነኖችን ለመጣል በአንድነት ተባብሮ ዉድቀታቸዉን ከማፋጠን ዉጭ ብዙ መዘገብ ጊዜን ማባከን ነዉ።

ዛሬ ይህችን ለመጻፍ ያነሳሳኝ ዋና ምክንያት ግን ሰሞኑን በከርቸሌ እጅና እግራቸዉን ታስረዉ ፍትህ በመሻት ፍርድ ቤት ለምስክርነት የጠሯቸዉ ባለ ሥልጣናት በመሆናቸዉ አይቀርቡም በሚል ፍርደ ገምድል ዳኛ ጥያቄአቸዉን ሲያጣጥል የብሶት መዝሙር እዬዘመሩ የጀግንነት ድምጻቸዉን ሥሰማ፤ እንዴት በጠቅላይ ሚኒስተር አንደበት ለሃገራዊ መግባባት ሲባል ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ይፈታሉ በተባለ ማግስት ለምን የቅጣት ዉሳኔወች ሰጡ? በወንድምና እህቶቻችን ላይ የሰቆቃ ተግባር ለምን ተፈጸመባቸዉ? አወ የጮኹት ጀግኖች ናቸዉ። ሞትን  ያሽቀነጠሩ፤ በትንሹ እስር ቤት ሁነዉ በትልቁ እስር ቤት የግፍ ቀንበር ለተሸከመዉ ህዝባቸዉ ህልዉና በአገራቸዉ ላይ ለተደቀነዉ የጥፋት አደጋ ሲሉ አዎ ጩኽታቸዉን አሰሙ። በእርግጥ ሰምተናል ብቻ ሳይሁን በደም በአጥንታችን ሰርጾ ገብቷል። ከትልቁ የፍርሃት እስርቤት ሊያስፈቱን በአመጽ ዘመሩልን ብዬ ብሶታቸዉም ጅግንነታቸዉን ሳስብ የነጻነቱ ቀን መቃረቡን አመንኩ። የካንጋሮዉ ፍርድ ቤት የባንዳዉች ጥርቅም መሆኑ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መንገር ለቀባሪ አረዱት እንደማለት ነው።
የአምባገነኖች የጭቆና መሳሪያ የሆነ ፍትህ አልባ ፍርድ ቤት በወያኔ  እዬታዘዘ ታሳሪወችን ብቻ ሳይሆን ቤተሰብን፤ ህዝብን በስነልቦና ለመጉዳት እዬተወሰደ ያለ እርምጃ መሆኑን እንረዳለን። በዚህ ባሳለፍነዉ ሳምንት ብቻ ሥንቶቹ ናቸዉ ቤተሰቦቻችን  በገና በዓል ይፈታሉ በሚል ተስፋ ደግሰዉ፤ ልብስ አዘጋጅተዉ እዬተጠባበቁ ባሉበት ሰዓት የግፍ ግፍ ከእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ ሆነና ወያኔ ራሱ ቀማኛ ራሱ ዳኛ ሆኖ  ቀጥፋት ላይ ጥፋት ከበደል ላይ በደል ሲፈጽ ም ሁላችንም አሞናል። በትልቁ እስር ቤት ያለነዉ ያለፍርሃት እንደ ህዝብም እንደ ሃገርም በትብብር ታግለን የወያኔን የግፍ በሽታ አስወግደን መዳን አለብን።
የሰቆቃ ድምጽ በፍርድ ቤት መንበር እዬተዘመረ ነዉ። ይህ ጩኸት በፍርድ ሚዛን ሲለካ የኢትዮጵያ  ህዝብ በአንድነት እምቢኝ ብሎ ለመነሳት የፖለቲካዉ ነዉጥ ሰዓት ደርሶ ከግፈኛ ዘረኛ አምባ ገነን መሪወች ሰፈር እያንኳኳ ጢሱ እያፈናቸዉ እንድሆን እርግጠኛ ነን። አምባገነኖች የሚታወቁበት ዋና ምልክት ሊወድቁ ሲንገዳገዱ  ህዝብ ይወደናል በሚል ቅሌት ካለፈዉ በበለጠ ይዋሻሉ፤ ሹምሽር ያበዛሉ፤ የሻሩትን ሌላ ስልጣን ይሰጣሉ፤ ዳንኪራቸዉ ጀሮ ያደነቁራል፤ ያላቸዉ ሃይል አለምን እንደሚያንቀጠቅጥ ወሬ ያናፍሳሉ፤ ከህዝብ ፊት ቀርበዉ ህዝብ የወሰነዉን አይቀበሉም፤ እራሳቸዉ የወሰኑትም መሸት ሲል ያፈርሱታል፤ ላገሪቱ ሰላም አምባሳደር እያሉ ጊዜ ለመግዛት ሸምጋይ አባቶችና የሃይማኖት መሪወችን እዬወጡ እንዲናገሩ ይማጠናሉ። ህዝቡ ችግሮችን ከቁጥጥር ስር አዉሏል እያሉ ይለፋሉ በጓሮ በር ገብተዉ ጨለማን ተገን አድርገዉ አፈናዉን ያጧጡፋሉ፤አሁንም  ሰላም አለ ይላሉ። ሃቁ ግን ከአዋጁ በኃላ በዚህ ሰዓት በሺዎች የሚቆጠሩትን መብራት አጥፍተዉ መገናኛዎችን ዘግተዉ በአንድ ሌሊት አፍነዉ እዬገደሉነዉ፤ በየቀኑ በሽወችም  እየታሰሩ ነዉ።
ሕዝብ ጠልቶ አልፈልግም ያለዉ ገዥ ቡድን  ይህን ሁሉ ኢሰባዊ ድርጊት የሚፈጽመዉ መዉደቁን አዉቆ በተዘጋጀበት 11ኛዉ ሰዓት ላይ ነዉ። ቀንደኛ ካድሬና ዘራፊ መሪወች ገንዘባቸዉን ዉጭ አስቀምጠዋል፤ ቤተሰቦቻቸዉ ዉጭ አገር ናቸዉ፤ የጦር ጀነራሎች ወታደሩን ከህዝብ ጋር በማጋጨት ለችግር ዳርገዉ  እነሱ አመጹ ሲበረታ ኬኒያ፤ ሱዳን ወይም SOMALILAND ሆቴል ተቀምጠዉ ያዋጋሉ፤ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን ቤት እያከራዩ በሄሊኮፕተር ጎረቤት አገር ማደር እንዳዘወተሩ ይሰማል። በሱዳን በኩል ግን ህዝቡ 30 ዓመታት በአልበሽር መንግስት ተሰቃይቷል፤ እንደወያኔወች በቅርቡ መዉደቁ አይቀሬ ነዉ። ለዚህም ብዙ መረጃወች አሉ መዘርዘሩ ግን ጠቃሚ አይደለም። ያም ሆነ ያ ግን ከሱዳን ጋር ተባብሮ ታላቋን ትግራይ ለመገንጠል፤ በአባይ ግድብ ስም ማጭበርበር ኢትዮጵያን የመበተን ጋብቻ በአጭር ቀን ያከትማል።
ሌላዉ የሚገርመዉ ህዝብን ያበሳጨዉ ጉዳይ ወያኔወች ወራትን ካስቆጠረዉ የነብስ አዉጭኝ ስብሰባቸዉ በኃላ  የድርጅት መበላለጥ እንደለሌ ተማምነናል ይላሉ። ለመሆኑ ያለፈዉ ይቅርና  የአሁኑን እስረኞችን የመፍታት ዉሳኔ የሚገለባበጠዉ እዉነት በአራቱ ኢህአዴግ ድርጅቲች ነዉ? በመላ አገሪቲ የሚካሄደዉ እስራትና ግድያ በደቡብ ፤ በኢትዮጵያ ሱማሌና ኦሮሞ ማህበረሰብ መካከል ትዉልድ የማጣፋት ድርጊት በማንኛዉ ድርጅት ሴራ እንደሚከናወን ህዝቡ እያስረዳ ያለዉ፤ እጣቱን የቀሰረዉ ወደወያኔ የመከፋፈል ሴራ አይደለምን?፤  በወልቃይት ጠገዴ፤ በጠለምት እየተካሄደ ያለዉ የሺሬዉ  አዲስ የሰሞኑ የአፈና ዘመቻ እዉነት ወያኔ እንደሚለዉ የሁሉም አጋር ድርጅቶች ዉሳኔ ነዉ፤  የነ ሃጫሉ ሁንዴሳ ፤የነቴወድሮስ ካሳሁን የከያኒወችን የሙዚቃ ዝግጅት አዲስ አበባ ዉስጥ የከለከለ አካል የብአደን ወይም የኦዴድ ጀኔራል ነዉን? ፍርዱን ለኢትዮጵያ ህዝብ ልተወዉ። በአለፉት 3 ቀናት አቶ አዲሱ ለገሰ የጎንደርን ህዝብ አማራና ቅማንት በሚል ለዘመናት አብሮ የኖረ ህዝብን ለመከፋፈል እያወኩ የሰነበቱት የድንበር ችግር የሌለበት ፌደራሊዝም ነዉ የሚለን ወያኔ ይህን ጉዱን በማታለል ለማለፍ አይደለንም? የጎንደር ህዝ በአንድነት ለ27 ዓመታት አንከፋፈልም እያለ ጀሮ ዳባ ልበስ ብለዉ የታላቋን ትግራይ  የቅዠት እራይ ለማሳካት አይደለምን የቅማት ክልል አስፈላጊ ነዉ የሚባለዉ፤ በኦሮሞና በሱማሌ ህዝ ግጭት እንዳስነሱት በጎንደርም ለመድገም አንዴ በረከትሲሞን አሁን አዲሱ ለገሰ የሚመላለሱት። የጎንደር ህዝብ ግን ይህን ሸራቸውን ጠንቅቆ ያውቃል።
ሌላዉ አዲስ ፈሊጥ የስርዓቱ እንደራሴዎች የዘዉግ ፌደራሊዝም በራሱ ችግር የለበትም የሚለዉ የኢህደጎች እንድምታ ያለዉ አገላለፅ የቂሉ ማሞ ጨዋታ ስለሆነብን ትንሽ ማለት እፈልጋለሁ። በቅድሚያ ግን ከድርጅት መሪወች መካከል ህዝብን የማዳመጥ ቀልብ ያለቸዉ ለወደፊትም በመሪነት ከለዉጥ በኃላ  በህዝብ ተመራጭነት የተስፋ ብርሃን የሆኑ እንዳሉ እዬገለጽኩ በኢሕአደግ በተለይም በትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር ፊታ,ዉራሪነት ዘርን መሰረት ያደረገ ፖለቲካ የማስቀጠል ሙከራ ግን ቀኑ ያለፈበት እንደሆነ ማሳሰብ እንወዳለን። ኢትዮጵያን እና ህዝባችን ያወከ ከመዝገብ መፋቅ ያለበት ዘላቂ ሰላማችን የነሳ  የብሄር ፌደራሊዝም እንደሆን ማስረገጥ እንፈልጋለን። ይህንን የተልፈሰፈሰ ስርዓት ከምንወዳቸዉ መሪወች ጋር ማቆይት አንፈልግም። በዚህ በኩል ያለዉን አወንታዊ የህዝብ ጥያቄ ለተከበሩ አቶ ለማ መገርሳና ለተከበሩ አቶ ገዱ አንድአርጋቸዉ መልክቱ ይድረሳቸዉ።
ዘርን መሰረት ያደረገ መፈናቀልን አድበስብሰን ይህን ሥርዓት አሞካሽተን የፖለቲካ አክሮባት በመዘወር ለመገላበጥ ሲባል መሪወች ነዉ የተሳሳቱ እነሱ ከስልጣን ወርደዋል በሚል ተሸፍኖ በቅቤ ተለዉሶ መርዝ ለማጉረስ እንደ ማሰብ ይቆጠራል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከጅምሩም በሽታ እንድሆነ አዉቋል የ27 ዓመታት ታሪክ የሚያሳዬዉም ይህን ሃቅ ነዉ፤ የአርባጉጉ፤ የጉራ ፈረዳ፤ የወልቃይት ጠገዴ፤ የእራያ፤ የቢሻንጉል ፤ በኦሮሞና በኢትዮጵያ ሱማሌ ማህበረሰብ የደረሰዉ ጭፍጨፋ ቋንቋና ዘርን መሰረት ባደረገ አከላለል ነዉ። ሁሉም በአንድ አገር ዜጋ ሁኖ የመኖር ስሜቱንና ፍላጎቱን ስለተነፈገ ነዉ። ይንን ሁሉ አንረሳዉም። የዘዉግ ሥርዓት አንድ ቀንም አብሮን እንዲያድር አንፈልግም፤ የድርጅቶች መነገጃ እና የስልጣን መንጠላጠያ; የህዝብ ሃብት መዝረፊያ ከመሆኑም በላይ የአገርና የህዝብ ክብር የሚያዋርድ ሉዓላዊነትን የሚሸረሸር ሁኖ አግኘተነዋል። አንፈልገዉም ከወያኔ ጋር ይሰናበትልን፤ አልጠቀመንም፤ በጣም እጅግ ጎዳን።
ከኢህአዴግ መሪወች በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከተባሉት ግለሰብ ግን  ህዝብን ያሳዘነ ጉዳይ አለ።  የህዝብ አስተያኀት ዘወትር እንደሚቀርበዉ ጠ/ሚኒስተሩ የራሳቸዉን የግለሰብ ስብእና ነጻነት ያጡ በወያኔ ለሚሸረቡት ሴራወች መልክት አስተላላፊ ማይክሮፎን  ሁነዉ ከህዝብ ጭራሹን የተለዩ፤ በጸያፍ አነጋገራቸዉ ጭምር በጣም ተንቀዋል። ከትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር ዘረኛ ድርጅት ትዛዝ እየተቀበሉ የደንበር ችግር ተፈትቷል፤ በእስር ቤት የመሰቃዬት ዘመን የደርግ ሥራዓት ብቻ ነበር እያሉ የሚያስተላልፉት መልዕክት እጅግ አሳፋሪ ነው ። መልዕክቱ  እንዲደርስ የምንፈልገዉም ለባለቤታቸዉ፤ ለቤተሰባቸዉ፤ ጓደኛ ካላቸዉ ፤ፕሮፌሰር ወንድም አላቸዉም ስለተባለ፤ እባካችሁ የሚሰሙ ከሆነ ቁጭ ብላችሁ ምከሯቸዉ፤ ህዝብ እንደ ጠ/ር ጭራሽ አይቆጥራቸዉም፤ምክንያቱም ሚና የላቸዉም። ለኢትዮጵያ ህዝብ እንደመሪ በራሳቸዉ እራይ ስላልቆሙ ተበዳይ ሕዝብ አቤቱታ ለሳቸዉ ማቅረብም አይፈልግም፤ በእርግጥም አቶ ሃይለማሪያም በራቻቸዉ አንደበት እንደተናገሩት የምወስነዉ ሁሉ መረጃ ሳይኖረኝ ነዉ ብለዋል እና ይህን ያህል የቁም እስረኛ ጠቅላይ ሚኒስተር ከሆኑ ለምን RESIGN አያደርጉም። ለምንስ ነዉ በድክመታቸዉ ህዝብ የሚሰቃይ። የድንበር ችግር ተፈትቷል እያሉ የወልቃይት ጠገዴን፣ ጠለምት ቃብታ ሁመራን፤ የእራያን በወሎ የወያኔን ፍላጎት ለማሟላት የጎንደር ብሎም የአማራ ኦሮሞ ጥያቄን የሚያድበሰብሱት ለምን ነዉ፤ የአጋዚ ጦር ከኢትዮጵያ ሱማሊ ልዩ ሃይል ጋር ተቀናጅቶ እያካሄደ ባለዉ ዘመቻ የኦሮሞ ፤የኢትዮፕያ ሱማሌ ወንድምና እህቶቻችን ተጨፍጭፈዋል፤ አንድ ሚሊዮን ህዝብ ተፈናቅሎ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሁነዉ እያለ ግን በመወገን የኦሮሞ ፖሊስ  ሱማሌወችን እንደጨፈጨፈ አድርገዉ ያይጥ ምስክሯ ድንቢጥ የተገላበጠ አሽቃባጭነትን የሚያራምዱት ሥራ የታሪክ ተወቃሽ ያደርግወታል። ሌላ ብዙ ነገር ሳያበላሹ እባካችሁ ንገሯቸዉ።
ዛሬ ሣናነሳ የማናልፈዉ ጉዳይ ደግሞ እዉነትም ጀሮ ከተማ ሆነና ብዙ ነገር እዬሰማን ነዉ፤ ሰሞኑን እንታረቅ በሚል ጨዋታ የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር አማራ ጠላታችን አይደለም የሚል ዲስኩር  አምጥተዋል ፤ ይቅርታ መጠዬቅ ተገቢ ሁኖ እያለ ወያኔ በማንፌስቶዉ አማራ ጠላታችን ነዉ ብሎ አርባ አመት ታግሎ አዲሰበባ ከተማ ከገባም በኋላ በቅርቡ የማንፊስቶ ጻሃፊ የመጀመሪያዉ የወያኔ ሊቀመንበር የአማራና ኦርቶዶክስን አከርካሪ ሰብረናል እያሉ  በአማራ ጥላቻ ያረጁት  ስብሃት ነጋ ሲዝቱ እዬተሰማ ሎሌነን ባዮች ሳይቀር እነ አለምነዉ መኮነን ሰድበዉ ለሰዳቢ ለመስጠት ላሃጫም አማራ ብለዉናል። በእርግጥም 5ሚሊዮን አማራን ከጨረሱ በኃላ እንደነ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም አማራ የለም ሳይሉ አይቀሩም። ነገርግን ብአዴንን አፍርሰዉ ሎሌ ማጣት የሚፈልጉ አይመስለንም። በተለይ እነ በረከት ስሞን እነ ካሳ ተክለ ብርሃን፤ እነ አለምነዉ መኮነንን፤ እን አዲሱ ለገስን አማራ ሳይሆኑ የአማራዉ ህዝብ መሪ ተብለዉ የሚቀልዱበት ድርጅት የት ያገኛሉ?። ወያኔወች ሊነገራቸዉ የሚገባ አንድ ሃቅ ግን አለ፤ አማራዉ በነገድም፤ በቋንቋዉ ከሁሉም ኢትዮጵያ ህዝብ የተጋመደ ነዉ፤ ዘሩን ቆጣሪ ሳይሆን የሁሉም ትዉልድ ደስታና መከራ ተካፋይ ማህበረሰብ ነዉ፤  ይህን የአንድነት ሃረግ ለመበጠስ በእናንተና በተከታዮቻችሁ ጥቃት ደርሶበታል። አማራዉ ከመላዉ ኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ዉሃና ወተት ነዉ። አትለዩትም። የማይቀርላችሁ ጉዳይ አለ አማራዉ ከመላዉ ኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ተዋህዶ የወያኔን የግፍ ሥራት አሸቀንጥሮ ጥሎ ኢትዮጵያን ለመረከብ ቃል ኪዳን የገባ ህዝብ ነዉ። ዘላቂ ሰላም ለማምጣትም በዘር ሳይሆን በክፍለ ሃገራት ፌደራሊዝም  የደስታ የጸጋ የፍትህ የእኩልነት ዘመን ለመፍጠር እስከ አሁን 12 ክፍለ ሃገራት ተወካዮች የጋራ ህብረት መስርተዋል፤ ይህ ትልቅ እራይ ነዉ፤ ሊደገፍም ይገባል።
በተጨማሪም በትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር የተጋረጠብን ቁስል ለማዳንም  በሃገረ አሜሪካ ሚኒሶታ ክፍለ ሃገር ዉስጥ ሁሉም ነገድ በህብረትተዋህደን ለመሥራት ETHIOPPIAN FORUM FOR RECONCILATION AND DEMOCRACY በሚል ሥያሜ ባለፉት 9 ወራት ተመስርቶ የታሪካዊ የአንድነት ምሰሶ መሰረት እዬጣለ መሆኑን ከመግለጫወቹ አንዱ የሆነዉን ይህን LINK ከፍተዉ ቢያነቡ መልካም ነዉ   http://www.zehabesha.com/amharic/?p=84287 ወደዋናዉ ነጥብ ለመመለስ አማራዉ የሁሉ ኢትዮጵያ ሕዝቦች አካል ነዉ። ወልቃይት ጠገዴን እራያን ጨምሮ አሁን የአማራ ክል ተብሎ በሚጠራዉ አራት ክፍለ ሃገራት ዉስጥ 30 ሚሊዮን ህዝብ አለ። እናንተ ከገደላችሁት 5 ሚሊዮን ዉጭ ማለት ነዉ። ከኦሮሞ ወገኑ ጋር የሚኖረዉ ቁጥር በተከበሩ አቶ ሌንጮ ባቲ አንደበት አሥራ አንድ ሚሊዮን አማራ ይኖራል።  በሌሎች በቀሩት ክልሎች ዳታ ባይኖረም በአጭሩ ወደ 7 ሚሊዮን ይኖራል የሚል እምነት አለን ። በዉጭ ከሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ከግማሽ በላይ  አማራ ሊሆን እንደሚችል ጥርጥር የለዉም። ወያኔወች ይህን ህዝብ ጠልተዉ ለምን ኢትዮጵያን እንምራ ብለዉ ሞከሩ ነዉ ዋናዉ ጥያቄ።
እናማ መሆን የነበረበት ህዝብን አይንን በጨዉ ታጥቦ ከማታለል ይልቅ በልጅነታችን የነበረንን ጥላቻ አዉልቀን ጥለናል፤ ማንፌስቶዉንም ከህዝብ ፊት እንቀዳለን፤ እንዲያዉም ይህ ህዉሃት የተባለ ድርጅት ከኢትዮጵያ ህዝብ አጠልቶናል ስሙንም ተቀይሮ ኢትዮጵያዊ ድርጅት ሁኗል የሚል ትልቅ ዜና አዲሱ ትዉልድ የትግራይ መሪ ያመጣል ብለን ስንጠብቅ ሽማግሌዉቹ የትልቅ ጭጫዎች እነ አቦይ ስብሃት ያሰባሰቡት ቡድን ተሿሹሞ የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር ብሎ እንደገና ታድሻለሁ ብሎ በነጻ አዉጭነት ብቅ አለ። ለምን ያህል ጊዜ ነዉ የትግራይን ህዝብ ነጻ እኒዲወጣ የሚታገሉለት? ኢትዮጵያንስ ማን ነዉ ነጻ የሚያወጣት?፤ አዲስ አበባስ ቤተመንግስት ነጻ አዉጭ ድርጅት ለምን ተቀመጠ?፤ መልሱን በአስቸኳይ የኢትዮጵያ ህዝብ ይሻል።
በአጭሩ የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር በአማራ ህዝብ ላይ ጥላቻ የለኝም የሚለዉን የሽርደዳ ጨዋታ ተወት አድርገዉ፤ ከስተታቸዉ አዲሱ ትዉልድ ተምሮ ወደፊት የጥላቻን ስይጣን ሰባብሮ ለመጣል የአማራን ህዝብ ይቅርታ መጠዬቅ ዉርደት ሳይሆን አብሮ የመኖር የሰላም አጀንዳ  መሆን ነበረበት።-
የህዝብ መልክት ከአገር ቤት
መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በዉጭ አገር የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ ለህዝቡና ላገሩ በሚያደግረዉ ታጋድሎ ከፍተኛ አድናቆት አለዉ። በተለያዬ መንገድ መልክቱን አሥተላልፏል። ወገንን ለመርዳት የሚደረገዉን ጥረት እጅግ ያደንቃል። በህዝብ መገናኛ የሚተላለፉ መልክቶች ብዙ አወንታዊ ጠቀሜታ እንዳላቸዉ አምኖ ጊዜ ሰቶ በቁም ነገር ያዳምጣል። አምባ ገነኑ መንግስት ማህበራዊ ድህረ ገጾችን ቢዘጋጋም በዬትም መስመር ተዘዋዉሮ አገላብጦ ESTAT፦ HIBER RADIO፦ VOA፦GERMAN RADIO፦ ADDIS DIMTS፦ FENOTE RADIOን  ይከታተላል። ከድህረ ገጽም ZEHABESHA፥ ETHIOMEDIA፦ECADF፥ QUATERO፦ETHIOFORUM ፦ABAY MEDIA መግለጫወችን ፤የምስል መልክቶችን ያነባል ያዳምጣል። ይህ አገልግሎታቸዉ ወደር የሌለዉ መሆኑ ሁሌም ይነገራል። በነጻነት ትግሉም የታሪክ እንቁ ናቸዉ፤ ከድርሳናት ምዕራፉ ዉስጥም ተገቢ ሥፍራ ይኖራቸዋል።
የመጨረሻ ያገርቤቱ መልክት
1ኛ በአገር ዉስጥ በትጥቅ የሚታገሉ ደጋፊወች በዉጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን አንድ የትብብር ግበረ ሃይል ፍጠሩ፤ የተናጠል አካሄድ እርስ በእርስ መጠላለፍን ስለፈጠረብን መሬት ላይ በዉጭ ፉክክር ከመከፋፈል አድኑን የሚል ነዉ
2ኛ በዉጭ የምትኖሮ የሲቢክ ተቋማት አንድ የጋራ ኮሚቴ/ ምክር ቤት መስርቱ
3ኛ አገር ቤት ህጋዊ ሁናችሁ የምትታገሉ ድርጅቶች ሁሉ ልዩነቶችን አጥባችሁ አንድ የጋራ ሸንጎ/ምክር ቤት አቋቁሙ የሚል ነዉ
ድል ለኢት ዮጵያ ሕዝብ

በአሁኑ ሰዓት ሥርዓቱ የፈጠረዉ ቀዉስ የ27 ዓመታት የዘዉግ ፖለቲካ ዉጤት መሆኑን በማዬት እና የራሱን ህግ ሌትና ቀን የሚሽር ዉሸቱ ማቆሚያ የሌለዉ የግፍ አገዛዝ በመሆኑ ጭራሽ ማንም ሃይል የማይበግረዉ  ለድል የሚያበቃ የትግል እሳት በየአቅጣጫዉ እየጨሰ ለመሆኑ ግን እርግጠኛ ነን። ይህን  ህዝባዊ የለዉጥ ሃይል በመሳሪያ አፈሙዝ አስቆማለሁ በሚል ትቢት የሚዳክረዉ አፋኝ ቡድን ከጭፍጨፋዉ ስራ ካላቆመ በትግሉ ወላፈን ተቃጥሎ እርቃኑን ሲቀር መዉደቂያዉ እንደ አዉሎ ንፋስ የፈጠነ ሁኖ ያከትማል፤ በህዝባዊ መንግስትም እንደሚተካ የማይቀር ሃቅ መሆኑን መናገር ይቻላል።