ኢት-ኢኮኖሚ     ET-ECONOMY

የኢትዩጵያ መድኃኒት ቅመማ ፋብሪካዎች የሙስና ሽያጭ!!!   –    ፀ/ት ፂዩን ዘማርያም

‹‹ለተገፋ ሁሉ ፍርድ እንዳይታጣ፣

  ድመት ሌሊት አይሂድ፣ አይጥም  ቀን አይምጣ፡፡››

ከቻይናና ከህንድ  የሚገቡት አብዛኛዎቹ መድኃኒቶች በውጭ ምንዛሪ ድርቅ የተነሳ አገር ውስጥ ባለመግባታቸው ህብረተሰቡ በመድኃኒ እጦት እየተሰቃየ ነው፡፡ በአንፃሩ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ከ100 በላይ የሚሆኑ የመኪና አስመጪ ድርጅቶች የወያኔ መንግሥት ሽርካዎች አዳዲስ መኪናዎች  ከባህር ማዶ በማስገባት ሲሸጡ ይስተዋላሉ፡፡ ለነሱ የዘነበ የውጪ ምንዛሪ ለመድኃኒት መግዣ መንጠፉ ምን ይባላል፡፡ በሃገሪቱ ከውጪ የሚገባ የዲያስፖራ የሃዋላ ገቢ ቀንሶል፣ የቱሪስት ጎብኝዎች ቁጥር አቆልቁሎል፣ በገቢ ንግድ ወደ ሀገር ውስጥ ዕቃና ሸቀጣ ሸቀጦች የሚያስገቡ   ነጋዴዎች በውጪ ምንዛሪ እጦት መሥራት አልቻሉም፡፡ የፕራይቬታይዜሽንና መንግስታዊ ኢንተርፕራይዝ  ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ከዴሬክተር ጀነራል አሰፋ አብርሃ፣ በየነ ገብረመስቀል እስከ ብርሃኔ ገብረመድህን የአንድ ዘር የስልጣን ሰንሰለት የህወኃት/ኢፈርት መንግሥት  በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ዘርፎች አትራፊ የሆኑ የኢትዩጵያ መድኃኒት ቅመማ ፋብሪካዎችን የህዝብ ንብረቶችን ወደ ግል ዘርፍ በማዘዋወር ሥም ከፍተኛ ምዝበራ በወያኔ ተካሂዶል፡፡ በኢትዮጵያ የወያኔ መንግሥት የኢትዩጵያ መድኃኒት ቅመማ ፋብሪካ፣ ለሜድሮክ አዲስ ፋርማኪዩር፣ ለኢፈርት/ አዲስ ፋርማሲዩቲካል ፋብሪካና ፣ ለቻይና መንግሥታዊ የንግድ ኩባንያዎች አትራፊ የነበሩ መድኃኒት ፋብሪካዎች ተሸጠዋል፡፡

የኢትዩጵያ መድኃኒት ቅመማ ፋብሪካዎች በፕራይቬታይዤሽን ሥም ቅርምት

1-ሜድሮክ አዲስ ፋርማኪዩርPharmacure

በቀ.ኃ.ሥ. ዘመን በ1956 ዓም የተቆቆመው የኢትዩጵያ መድኃኒት ቅመማ ፋብሪካ (ኢመፍ) ፋብሪካ በመንግስት ይዞታ ከቆየ በኃላ ከመስረከም 15 ቀን 2007 ዓም ጀምሮ ፋብሪካው ሜዲቴክ ኢትዩጵያ ንብረትነት ተሸጠ፡፡ ኢመፍ በ436,600,000 ብር (436 ሚሊዩን 600 ሽህ ብር) ሽያጭ ወደ ግል ይዞታ መዛወሩ ይታወቃል፡፡‹‹የኢትዩጵያ መድኃኒት ፋብሪካ››(ኢመፍ)የሃምሳኛውን ዓመት ባከበረበት ግዜ በአንድ ቢሊዩን ብር የማስፋፋት ሥራ ለመስራት በሰበታ ከተማ በሊዝ በተገዛ 40,000 ሜትር ካሬ ቦታ በመረከብ የፍብሪካ ግንባታ ጀምሮል፡፡ የኢትዩጵያ መድኃኒት ቅመማ አክሲዩን ማህበር በሚል መጠርያ የህወኃት/ኢህአዴግ መንግሥት፣ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ሚድሮክ የኢትዩጵያ መድኃኒት ፋብሪካ››(ኢመፍ)ኢፋርም ፋርማሲዮቲካል ገዝቶል፡፡ The largest of these are MIDROC’s Pharmacure, the SOE EPHARM established in 1972 (currently 50 products and 570 employees), ፋርማ ኪዩር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት በ1998 እኤአ በሜድሮክ ኢትዩጵያ ባለሃብት በሸክ መሃመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲ የተመሠረተ ድርጅት ነው፡፡ ፋርማ ኪዩር፣የመድሃኒት መቀመሚያ ፋብሪካ ሲሆን የተለያዩ መድሃኒቶችና የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች ለማምረት የተቆቆመ ፋብሪካ ነው፡፡ ፋብሪካው በአመዛኙ በደም ስር የሚሰጡ ፈሳሽ መድሃኒቶችና ግሉኮስ በማምረት ለሃገር ውስጥ ፍጆታ በማዋል ይታወቃል፡፡ ለ109 ስዎች የስራ እድል አስገኝቶል፡፡

ኢፋርም/ EPHARM በ1972 እኤአ የተቋቋመ የመድሃኒት ፋብሪካ ሲሆን ከ50 በላይ መድሃኒቶችን በማምረት ሲታወቅ ለ570 ሠራተኞች የስራ እድል ፈጥሮል፡፡ በኢትዩጵያ የሚገኙ የመድሃኒት ፋብሪካዎች 98 በመቶ የመድሃኒት ጥሬ እቃዎች ግብአት ከቻይና ኢንፖርት እንደሚያደርጉ ጥናቶች አረጋግጠዎል፡፡ የመድሃኒት ምርቱም አቅርቦት  70 በመቶ ለመንግስታዊ ፋርማሲዩቲካል ዘርፍ  በግልፅ ጨረታ ይቀርባል፡፡

2- ኢፈርት አዲስ ፋርማሲዩቲካል ፋብሪካ (Addis pharmaceutical factory) የህወኃት/ኢህአዴግ መንግሥት፣ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ለስታር ፋርማሲዮቲካል ኤንድ ሜዲካል ስፕላይ ሼር ካንፓኒ (Star Pharmaceuticals & Medic. Supp S.C) ከተሸጡት 91 አነስተኛ የችርቻሮ ሱቆችና ቢዝነሶች ውስጥ 2ቱን 2,948,541 ሚሊዮን ብር ገዝተዋል፡፡ ሁለቱ ፋርማሲዎቹ  ሴንትራል ፋርማሲ እና ሂልሰን ፋርማሲ ናቸው፡፡ በ1995ዓ/ም ስታር ፋርማሲዮቲካል  25 ሚሊዮን ብር ካፒታል ያለውና በመቐለ ቢሮ እንዳለው ይታወቃል፡፡ The relatively very few purchases by either endowment funds or endowment-owned companies of SOEs under the privatisation process are also remarkable: Kuraz publishing (bought by Mega for ETB13million) two pharmacies and one or two hotels seem to be almost the only exceptions.2 (Sarah Vaughan and Mesefin Gebremichael, Aug. 2011)

አብዛኛዎቹ በአዲስ አበባ የሚገኙ ውጤታማ ነጋዴዎች ከህወሃት የጦር አበጋዞች መንግስት ጋር የጠበቀ የንግድ ግንኙነት አላቸው፡፡ የህወሃት/ ኢፈርት ድርጅት 51 በመቶ የኃብት ድርሻ ከአዲስ ፋርማሲዩቲካል ፋብሪካ፣ ስታር ፋርማሲዩቲካልና ሜዲካል ሰፕላይ የጋራ ሼር ነበረው፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው ሼር ደግሞ ሙሉጌታ ጎዴ መንግስቴ በሁለት አስርት አመታት በኃብት ምጥቀት መሠላል በሮኬት የተተኮሰ በሎንደን ከተማም የሰናይ ታወር ባለቤት በመሆን ከወያኔ ጋር በጋራ የዘረፉ መሠረተ ደሃዎች ናቸው፡፡ ሙሉጌታ ጎዴ መንግስቴ አዲስ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ባለቤትና ከፍተኛ ሼር ድርሻ በአቢሲኒያ ባንክና ናይል ኢንሹራንስ እንዳላቸው ይታወቃል፡፡  Actually, many of the successful businessmen in Addis Ababa have financial connections with the TPLF. If we take EFFORT, we see that it owns 51% share in Addis Pharmaceutical Factory, and Star Pharmaceutical and Medical Supply. Most of the remaining shares are those of Mulugeta Guade Mengiste [an Amhara] who has risen like a rocket in the business circle in Addis Ababa within a span of a decade. Mulugeta is in control of Addis International Trading while at the same time being a major shareholder in the BANK of Abyssinia and NILE Insurance.

አዲስ መድኃኒት ፋብሪካ በ1992 እኤአ በሁለት ሰዋች በጋራ ንብረትነት የተመሠረተ የንግድ ድርጅት ነበር፡፡ ፋብሪካው ደቡብ ምዕራብ ትግራይ በአዲግራት ከተማ የተቋቋመ ፋብሪካ ነው፡፡ በ1995 እኤአ ሙሉጌታ ጎዴ መንግስቴ የንግድ ድርሻውን ለኢፈርት አስተለላለፈ፡፡ በ1997 እኤአ ፋብሪካው ምርት ማምረት በመጀመር 30 በመቶ ብቻ የማምረት አቅሙን እንደተጠቀመ ከዛም በህወሓት መንግስት ድጋፍ ከውጭ የሚገቡ መድኃኒቶች ወደ ሃገር ውስጥ እንዳይገቡ በማገድና ከአዲስ መድኃኒት ፋብሪካ እንዲገዙ ትእዛዝ በማስተላለፍ የመድኃኒት ገበያ ድርሻውን ከፍ ማድረግ ችለዋል፡፡ በአሁኑ ግዜ የፋብሪካው የምርት አቅርቦት 77 በመቶ መድረሱ ይገለፃል፡፡ ፋብሪካው የመድሃነት ምርቱን 130 ዓይነቶች አድርጎ በመጨመርና በ10 የምርት ማምረቻ የመስመር ስርጭት በማድረግ በኢትዩጵያ ትልቁ የመድኃኒት ፋብሪካ ለመሆን በቅቶል፡፡ (The company has more than nine production lines and fully equipped laboratories as well as the capacity to produce tabulates, capsules, syrups/suspensions, dry powders for reconstitution, injectable vials, liquid injectable ampules, creams and ointments.) Addis Pharmaceutical Factory manufactures more than 91 high quality products of different therapeutic categories including antibiotics, gastro-intestinal drugs, central nervous system drugs, cardiovascular drugs, anti-diabetic agents, antihistamines, antehelmitics, analgesics, antiprotozoals, respiratory drugs, dermatological preparations, minerals and vitamins as well as large volumes of Parentals.

በ2009 እኤአ ሁለተኛውን ፋብሪካውን በአቃቂ ከተማ manufacturing of large volumes Parenterlas. The Ethiopian pharmaceuticals sector remains relatively small, with 10 firms producing pharmaceutical products, and three others making medical supplies. The largest of these are MIDROC’s Pharmacure, the SOE EPHARM established in 1972 (currently 50 products and 570 employees), and EFFORT’s Addis Pharmaceuticals. Ethiopian production satisfies only 20% of the domestic market: pharmaceuticals imports were valued at US$190million in 2008, and more than a hundred importers and wholesalers are registered in the country.

Although the sector is regarded as a priority for development and import substitution, tight regulation constitutes a barrier to entry, as does the Ethiopian industrys import of more than 90% of raw materials, accounting for 40% of costs (Sutton and Kellow, 2010 165ff). A number of medium- sized enterprises were reported to be in trouble in the middle years of the decade. Controversy attaches to the eventual purchase by EFFORT in 2005 of the shares of the remaining partner, after relations apparently soured (see below, on Tower Trading Company). …Addis Pharmaceuticals also hopes to move into regional export markets, and its horizontal integration was improved by the acquisition of the newly established but insolvent Lifeline IV fluid manufacturer. Ninety-eight per cent of the companys raw materials are imported, mainly from China, and 70% of its products are sold to the state-owned Pharmaceutical Fund Supply Agency on open-tenders (Sutton and Kellow, 2010).

3- ቻይና Sino ሂውማን  ሄልዝ ኬር፣  ቻይና አዲስ  መድኃኒት ፋብሪካዎች በኢትዮጵያ በመገንባት ላይ ትገኛለች፡፡ሂውማን  ሄልዝ ኬር 91 ሚሊዮን  ዶላር ወይም በ2 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር በአማራ ክልል ሃገረማርያም ቀሰም በመገንባት ልይ ይገኛሉ፡፡

China’s biggest pharmaceutical company in to build plant in Ethiopia/Thursday, June 16, 2016{addisfortune.net}

Humanwell Healthcare, China’s biggest pharmaceutical company, will invest $91million (2 billion Birr)for the construction of a plant in Ethiopia- its second investment destination on the continent, after Mali, in West Africa. The plan will produce tablets, capsules, injections and syrups when operational within the next two years. The factory is to be constructed in the Hageremariam Kesem district of Amhara, located approximately 65 Km north of Addis Ababa. “When the plant is completed, the prices of medicine for locals will be low” said Mebratu Melese, Ethiopia’s state minister for industry. The local pharmaceutical industry comprises 22 pharmaceutical and medical suppliers and manufacturers, with nine directly involved in the manufacture of pharmaceutical products.

በተመሳሳይ ቻይና ቲሲጁ የሲቪል ኢንጂነሪንግ ካንፓኒ የቅሊንጦ ኢንዱስትሪል ፓርክ በመገንባት፣ ፓርኩ በ270 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በ204 ሚሊዮን ዶላር በዓለም ባንክ ብድር በተሰራው ፓርክ ሌላ አዲስ  መድኃኒት ፋብሪካዎች በመገንባት ላይ ትገኛለች፡፡

CHINA DAILY.COM.CN/ /Xinhua/ 2017

Ethiopia to commission Chinese-built pharmaceutical Industrial Park in March 2018A.A-Ethiopia will commission Chinese-built Kilinto industrial park which will host pharmaceutical companies in March 2018, an Ethiopian official said on Sunday. Speaking to journalists, Getahun Agenew, project manager at Kilinto industrial park, Said 75 percent of the project had been completed. The industrial park lying on 270 hectares of land is being constructed by china Tiesiju civil engineering Group Co Ltd (CTCEGCL) at a cost of $204 million. The World Bank is wholly financing the construction of the industrial park through a loan scheme. Kilinto industrial park, when completed, will encompass 18 km of asphalt roads, provision of basic social services, green spaces, warehouses, business centers and car parking space. Ethiopia is currently constructing or has commissioned 15 industrial parks as part of plan to turn the country into a light manufacturing hub in Africa by 2020.

Average availability of key essential drugs in PHCFs in the six regions (Figure 2) varied between 65

% (Amhara region) and 90% (Tigray region) showing relatively highest availability of essential drugs in Tigray region and lowest availability in Amhara region. However, the mean variations for both adult and children products were found to be insignificant (P>0.05).

Figure 2 Availablity of key essential drugs in PHCFs in six regions

የኢትዮጵያ መድኃኒትና ሕክምና መገልገያ አምራቾች ማህበር ፕሬዜዳንት አቶ ዮናስ ገብረፃዲቅ ለሪፖርተር እንዳሉት ‹‹በኢትዮጵያ 15 መድሃኒትና የህክምና መገልገያ አምራቾች አሉ፡፡ ከነዚህ መካከል 8ቱ መድሃኒት አምራቾች ናቸው፡፡ አጠቃላይ የገበያ ድርሻቸውም 10 በመቶ ብቻ የሚሆነውም በኢንዱስትሪው ላይ ማነቆ የሆኑ ትልልቅ ችግሮች መኖራቸው ነው፡፡ ከእነዚህ ማነቆዎች 50 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ የሚይዘው የውጪ ምንዛሪ እጥረት ሲሆን፣ ከባለፈው 2009ዓ/ም የካቲት ወር ጀምሮም ኩባንያዎቹ ምንም ዓይነት የውጪ ምንዛሪ ማግኘት አልቻሉም፡፡ 90 በመቶ የሚሆነው ጥሬ ዕቃ የሚገባው ከውጭ አገሮች መሆኑ ደግሞ የምንዛሪው እጥረት የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ከባድ እንዲሆን አድርጎታል፡፡በዚህም አብዛኞቹ ኩባንያዎች የሚያመርቱት የምርት መጠን እንዲቀንስ ሆኖል፡፡ ሠራተኞች የቀነሱም አሉ፡፡›› በአጠቃላይ አገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶች የአገሪቱን የመድኃኒት አቅርቦት 10 በመቶ ያህል ቢሸፍኑ ነው፡፡ እስከ 90 በመቶ የሚሆነው ከውጭ የሚገባ ነው፡፡ የሃገር ውስጥ መድሃነት አምራቾች 90 በመቶ የሚሆነውን የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ከውጭ አገር መግባቱ ከሌሎች ዓለም አቀፍ አምራቾች ጋር እኩል ተወዳዳሪ መሆን እንዳይችሉ ያደርጋቸዋል፡፡ አብዛኛዎቹ አገር ውስጥ የሚገቡ መድኃኒቶች ከህንድና ከቻይና ነው የሚገቡት፡፡ ውድድሩ ጥሬ ዕቃና ዋናውን ምርት ከሚያመርቱ ድርጅቶች ጋር ነው የሚሆነው፡፡‹የአገር ውስጥ አምራቾች የሚያመርቱት አሞክሳሲሊን፣ አምፒሲሊን የመሳሰሉት ምትክ የሌላቸው መሰረታዊ መድኃኒቶችን ነው፡፡ ሲዲቲ (Center for Innovative Drug Development and Therapeutic Trials for Africa) አንዱ ነው፡፡ ሲዲቲ በአፍሪካ ውስጥ የመድኃኒት፣ የክትባት፣ የላብራቶሪ ዲያግኖስቲክ፣ የመድኃኒት ምርምርና ሌሎችም በህክምናው ዘርፍ የሚታዮ ክፍተቶችን በትምህርትና በሌሎች የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ለመሙላት የተቆቆመ ድርጅት ነው፡፡ በሲዲቲ ፕሮግራም የሚገዙ መድኃኒቶች የወባ፣ የቲቪ፣ የቤተሰብ ምጣኔ፣ የክትባት መድኃኒቶችና የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ሲዲቲ ፕሮግራም የቀረበው መድኃኒት ካለው ፍላጎት አንጻር የሚያጥርበት አጋጣሚ እንደሚፈጥር፣ ስለዚህም የእርዳታ መድኃኒቶችን በተገላባጭ ፈንድ የሚገዙበት አጋጣሚዎች እንዳሉ ዳሬክተሮ ወ/ሮ አድና በሬ ገልፀዋል፡፡ በ2007 ዓ/ም 12.5 ቢሊዮን ብር፣ በ2008ዓ/ም 12.8 ቢሊዮን ብር፣ በ2009ዓ/ም 13.5 ቢሊዮን ብር፣በ2010ዓ/ም 15.3 ቢሊዮን ብር የሚገመት መድኃኒት በየጤና ተቆማቱ ኤጀንሲው ገዝቶ አሰራጭቶል፡፡ በ2009ዓ/ም በኤጀንሲው የተፈፀመው የመድኃኒት ግዥ 13.3 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ ከአገር ውስጥ አምራቾች 1.2 ቢሊዮን ብር የሚገመት መድኃኒት ለመግዛት ዕቅድ ተይዞ ማግኘት የተቻለው ከ900 ሚሊዩን ብር የሚገመት መድኃኒት ብቻ ነው፡፡

የህሊና እስረኞች የፈቱ!!!

የሙስና መርማሪ ኮሚሲዮን ይቆቆም!!!

ከሙስና ኢኮኖሚ ግንባታ በፊት፣ የህዝብ ውይይት ይቅደም!!!

ጊዜዊ የሽግግር መንግሥት ይመሥረት!!!