ይህ ጽሁፍ በቪዲዮ ቀርቦ ነበር:: ብዙ ሰዎች በጽሁፍ ይቅረብልን በሚል በጠየቁን መሠረት በጽሁፍ አቅርበነዋል:: ቪዲዮውን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በዛሬ ሹክሹክታ የምንዳስሰው በወያኔ ቅጥር ብሎገሮች ላይ ይሆናል። ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ ሆነው እሳት ከሚለኩሱት ውስጥ ዳዊት ከበደ፣ ዳንኤል ብርሃነ፣ ዘራይ ሃይለማርያም እና ቢንያም ከበደ (ቤን) በዋናነት ይጠቀሳሉ። ያለ አቅሙ የኮሚኒኬሽን ዲያሬክተር እንዲሆን የተሰየመው ሃዱሽ ካሱ ይመራቸዋል። ሰሞኑን በፌስቡኩ በሚለቅቀው መረጃ ሃዱሽ ሃከሩ ተብሏል። አሁን እንደተባረረ የተነገረን የትግራዩ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ – ገብረሚካኤል መለስ ቦላጊዎቹን ይመግባቸው ነበር። ሴሰኛው ደብረጽዮን ደግሞ እንደ እንዝርት ያዞራቸዋል።

በህወሃት የውስጥ ሽኩቻው ተባብሷል። የህወሃት መናቆር ታማኝ ውሾቻቸውንም እርስበርስ እያባላቸው ነው። ለትንሽ ግዜም ቢሆን ተቃዋሚውን ለቀቅ አድርው አንዱ በሌላው ላይ ምስጢራዊ መረጃ ማሾለኩን ተያይዘውታል።


ሕዝብ ቢምቢ ብሎ ነው የሚጠራቸው። ይህ ስም ያለምክንያት አልወጣላቸውም። እንደ ባዶ በርሜል ይጮሃሉ፣ ያገኙትን ሁሉ እንደ መርዘኛ ትንኝ ይናደፋሉ። ለስድብ ይከፈላቸዋል። ወጋቸውም የሚተመነው በስድባቸው መጠን ነው።

የጥቅማ – ጥቅማቸው ሚስጥር ከወጣ በኃላ እንደወትሮ መንቀልቀላቸውን እና አፋቸውን መክፈት አቁመዋል። ሰሞኑን ስራቸው የርርስበርስ መተማማት ሆኗል። የብሎግ ቋንቋቸውንም ቀይረዋል። ስድብ ይሁን ሙገሳ ብቻ መረጃውን በትግርኛ እየለቀቁብን ነው።

ዳናኤል ብርሃኔ በትግርኛ ሁለት ስንኝ ወግ ለጥፎ ነበር። የክፍያቸው ሚስጥር አደባባይ ከተበተነ በኃላ ለመጀመርያ ግዜ የለጠፋት ነገር ናት። አንዱ ይጠይቀዋል።

“ለዚህ ደግሞ ስንት ተከፈለህ፤ 30 ሺህ?”

ዳንኤል በዚህ ጥያቄ ይበሳጫል ብሎ ያልጠበቀ የለም። እሱ ግን እቴ – ፍንክች የለም።

“ምን ብትንቀኝ ነው በዚህች በ30 ሺህ የምትገምተኝ?” ሲል በድፍረት መለሰ።

30 ሺህ ብር ለሱ ኢምንት ናት። 30 ሺህ ለእነ ቤን እና ለእነ ዳዊት ከበደ ይወረወር ይሆን እንጂ ዳንኤል በዚህች በትንሽ ዲናር አይታማም። እሱ ከነ ደብረጽዮን ጋር በከፍታው ዘመን ላይ ነው።

ክርስቶስን በሰላሳ ዲናር እንደሸጠው አይሁድ በልቅምቃሚ የሚታሙት ትናንሾቹ ናቸው። ግን ትግርኛው ለምን አስፈለገ? እነ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና እነ ለማ መገርሳ በማይገባቸው ቋንቋ መቦለግ ለምን አስፈለገ? ይህ ግራ ቢያጋባም አያሌ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላሉ። የታማኝነት እና የእኔ እበልጥ ፉክክር ሊሆን ይችላል። ገመናቸውን ትግርኛ ተናጋሪ ያልሆነው ወገን እንዳያውቅ ለማድረግ ከአለቆቻቸው ታዝዘውም ሊሆን ይችላል።

“መተማመን ጠፋ” ብለው ነበር ዞሚዎቹ ባወጡት ጋዜጣዊ መግለጫ። እነ ቤን ትግሬ አይደሉም። እንዲያው ለመኖር ሲሉ እንደ ፓራሳይት ህወሃትን ተጠግተው የሚጮሁ አድርባዮች ናቸው። ዳናኤል ብርሃኔም ቢሆን የድሬዳዋ ትግሬ ነው። በነሱ መስፈርት ሲመነዘር ኦሪጅናል ከሚባለው የትግሬ ዘር አይመደብም። ዳዊት ከበደ ደግሞ የአድዋ ትግሬ ይሁን እንጂ በአንድ ወቅት ህወሃትን ክዶ እንደገና የተመለሰ በመሆኑ የጥርጣሬ ራዳር ውስጥ ነው።

ያም ሆኖ፤ የወያኔ ብሎገሮች የሰሞኑ የርስበርስ ንክሻ ከተለመደው የጥቅም ጉዳይ አላለፈም። በመርህ ወይም በፖሊሲ ነገር ላይ የሃሳብ ልዩነት ሊያከረክር፤ ጠንከር ሲል ደግሞ ሊያጣላም ይችላል። የነሱ ግን ይለያል። የህወሃት የመግደል እና የማግለል ፖሊሲ ላይ ሁሉም ይስማማሉ። ዜጋን ያላግባብ መግደል፣ ማሰር እና ማሰቃየት ለነሱ ምንም አይደለም። ገንዘብን ብቻ ስለሚያመልኩ ይህ ሁሉ ግፍ አይናቸውን አሳውሮታል። ብእሮቻቸው የሚነጥበው በወገን ስቃይ ላይ አይደለም። ከዚያ ይልቅ የአለቆቻቸውን መልካም ገጽታ በመገንባት፣ እንደ ሩዋንዳው በዘር ላይ ተንተርሰው የርስበርስ ጥላቻን በማባባስ ነው። ይህን ለማድረግ እኔ እበልጥ – አኔ እበልጥ ፉክክር ውስጥ በመሆናቸው ጸባቸው ካዚያ ያለፈ አይደለም። እንደፈጣሪያቸው እንደ ህወሃት ያሳተሳሰራቸው የጥቅም ሰንሰለት መፈታታት ሲጀምር፣ ገመናቸውም አደባባይ ተዘረጋ። እነሆ ጉዳቸው እርቃኑን ሆኖ ሃፍረታቸውን ገላለጠው።

እንደ ሴት ወይዘሮ፣ ወገባቸውን ይዘው ሲሳደቡ የነበሩ የወያኔ ብሎገሮች ሁሉ ጥቀርሻቸውን ይተፉብን የነበረው ወደው አልነበረም። ገንዘብ ይናገራል እንዲሉ፣ ለአንዲት ስድብ በመቶ ሺዎች ይከፈላቸው ኖሯል። “ውቼ ጉድ!” አለ ያገሬ ሰው። ይህችን ሃገር በስንቱ ነገር ነው የሚግጧት!

አክታቸውን የሚያስመልሱበት ድረ-ገጽ አላቸው። ቆሻሻቸውን የሚጸዳዱበት ማህበራዊ ገጽ ተከፍቶላቸዋል። ጉንጫቸው እስኪቀደድ በጫት ተወጥረው እንደ አሽኮለሌ ሲሳደቡ እዚያ ይውላሉ። በማህበራዊ ገጽ ሲሳደቡ ያመሻሉ። የዘር ጭፍጨፋን እየሰበኩ ወገንን ከወገን እርስበርስ እያባሉ ይከፈላቸዋል። ወፍራም ክፍያ። አንድ የሳይንስ ተመራማሪ ከሚያገኘው በመቶ እጅ የሚበልጥ ክፍያ።

አጀማመራቸው ስለ ልማቱ እያጋነኑ እና እያዛቡ ህዝብን እና አለም አቀፉን ህብረተሰብ እንዲያወናብዱ ነበር። ልማታዊ ጋዜጠኛ ለልማታዊ መንግስት በሚል መርህ ሕዝብ ለማሳመን ረጅም ጉዞ ተጓዙ። የገፅታ ግንባታ፣ ተሃድሶ፣ ጥልቅ ተሃድሶ፣ መተካካት ወዘተ… የሚሉ አዳዲስ ቃላትን ቢፈጥሩም ተለመዱ። እንደ ሞቃዲሾ ጣብያ ሰሚ አላገኙም። እንደ ናዚው ጎብልስ ሚሊዮን ግዜ ቢደግሙትም ወፍ የለም። ስድቡም፣ የልማቱ ወሬም፣ ፕሮፓጋንዳውም … ሁሉም በአፋቸው ላይ ቀረ።

ይልቁንም ከጥልቅ መታደስ ወደ ጥልቅ መበስበስ ገቡ። እቅዱ ሲተገበር ከመተካካት ይልቅ መከካካት ሆነ። የተጻፈው እና የተነገረው እድገት፣ ትራንስፎርሜሽን እና የገጽታ ግንባታ የግል ግንባታ ብቻ ሆኖ ቀረ። አገር ሳይሆን ፤ እነሱ ተገነቡ። አይናችን እያየ ከድህነት ወደ ብልጽግና ተቀየሩ። አካላቸውም ተድቦለቦለ። ስለ ዳንኤል ብርሃኔ ትራንስፎርሜሽን ሆዱ ብቻ ይመሰክራል። ሃገሪቱ የሱን ሆድ ግማሽ ያህል ብታብጥ ኖሮ የትራንስፎርሜሽኑን አሲዮ ቤሌማ እውን ይሆን ነበር።

ብሎገሮቹ ትወናውን በብቃት ስላልተወጡ ፣ በዚህ መንገድ የሚያምናቸው ጠፋና የትኩረት አቅጣጫ ቀየሩ። ተቃዋሚዎችን ፣ ዲያስፖራ አክቲቭስቶችን መስደብ እና ማዋረድ። በዚህ መስመር ጉዟቸውን ሲጀምሩ የኢዮትጵያ ፈርስቱ ቤን የመጀመርያው ሰልፍ ላይ ነበር። የኋላ ኋላ የዘር ግንዱ ተጣራና ገሸሽ ተደረገ። ይህ ሰው ልማታዊ ብሎገር ሆኖ ምስጢር ግን አይደርሰውም።

ይህ መገለል ለቤን ምንም አይደለም። ቻፓው አይቋረጥ እንጂ የዞሚ ምስጢር ለሱ ምን ሊበጀው?

ቢምቢዎቹ እነ ቤን በማያውቁት ትግርኛ መቦለግ ጀምረዋል። ዳንኤል ብርሃነ በትግርኛ ሁለት ስንኝ በለቀቀ ማግስት ዳዊት ከበደም አንድ ምስጢር በትግርኛ ለጥፏል። በትግርኛ መቦለጉ የቋንቋ ችሎታ ፉክክር ይሁን ወይንም ደግሞ ምስጢር ድበቃ ግልጽ አይደለም። የትግራይ ክልሉ የማስታወቂያ ሃላፊ አቶ ገብረሚካኤል መለስ ከስራው ተባረረ ሲል ጽፏል። የትግራይን ሜድያ ገድሏል ተብሎ ሲከሰስ እንደነበር ተጠልፎ የወጣው መልእክት ጠቁሟል።

በአደባባይ የወጣው ሌላው ምስጢር ይሁዳ ያሉት ራሱ ዳዊት ከበደ ቅርብ ክትትል እንዲደረግበት ተወስኖበታል። ሃዱሽ ካሱ ከዘራይ ሃይለማርያም ጋር ባደረገው የአጭር ጽሁፍ ልውውጥ ዳዊት ከበደ ከደብረጽዮን ጎራ እንደተሰለፈ ይጠቁማል። ሁለቱም ተወቃሾች ከአድዋ መሆናቸው ደግሞ ነገሩን ግልጽ ያደርገዋል። እነ ዳዊት ከበደ የዳናኤል ብርሃኔን የክፍያ ምስጢር አደባባይ በማውጣት ይታማሉ። በብሄራዊ ደህንነት መዋቅር የስለላ ብሎገሩ፣ ዘራይ ሃይለማርያም ዳዊት ከበደን ከተቃዋሚዎች ጋር በምስጢር ይገናኛል ሲል ይከስሰዋል።

በመቀሌው ስብሰባ መተማመን አልነበረም። ታማኝ የተባሉት ብሎገሮች ሳይቀሩ በስብሰባው አዳራሽ ስልክ ይዘው እንዳይገቡ ተከልክለው ነበር። እንግዲህ የከፍታቸው ጥግ እዚህ ድረስ ነው።

የጥቅሙ ነገር ሚስጥራቸውን መደባበቅ እስኪሳናቸው ድረስ እያባላቸው ነው። በዚያ ላይ ደግሞ የዘር ግንድ ጉዳይ አለ። አድዋዎቹ በተለይ አዲግራትንና አክሱምን ገሸሽ እያደረጉ ነው። የዘሩ ጉዳይ ሙቀቱን የበለጠ አግሎታል። የነ ደብረጽዮን ምስጢር ይለቀቃል። ሕዝቡም እያረረ ይስቃል….

ጨዋታውን ያሳመረው ግን በመሃል የመጣችው የሃከር ጫወታ ናት። የፌስ ቡክ አካውንት አንዴ ሃክ ሊደረግ ይችላል። በየሰከንዱ ሃክ ተደረገ የሚባል ጨዋታ ማንንም አያሳምንም። የፌስ ቡክ አካውንቱ ሳይሆን ሃዱሽ ራሱ ሃክ ተደርጎ ይሆን?

የኮሚኒኬሽን ዲያሬክተሩ ሃዱሽ ካሱ ፌስ ቡክ ሃክ ተደረገም አልተደረገ – በገጹ ላይ የሚለጠፈው መረጃ መሬት ላይ ጠብ አይልም። ለምሳሌ ከእስር ስለሚፈቱት የፖለቲካ እስረኞች የኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣሉ ብሎ ነበር። እንዳለውም ሆነ። ስለ ህወሃት የስራ ስምሪት መጠቆሚያ ሰጠ። ይህም ተፈጸመ። ሚስጥራዊውን የህወሃት ማእከላዊ ኮሚቴ ግምገማ ቃለ-ጉባኤ ለጠፈ። ሴሰኛው ደብረጽዮን የሞተ መ/ቤትን እንደሚመራ በማስረጃ አስደግፎ ነገረን። ይህንን አይተን አጃኢብ ብለን ሳናበቃ ሟቹ ክንፈ ገ/መድህን ስልጣን ዘመኑ በእንግሊዝ ያስቀመጠውን በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለመቀራመት ደብረጺዮን ማሊዥያ ከሚኖር ወዳጁ ጋር የተለዋወጣቸውን ጽሁፎች ዘርግፎልናል። ስለቻይናው የህወሃቶች የትምህርት በጀትም አቋድሶናል።

ይህንን ሁሉ የታዘብ እንዲህ ይላቸዋል “የሃከሮች እና የፋከሮች” ፍጥጫ ይቀጥላል…