https://www.youtube.com/watch?time_continue=10&v=uQOC8qwZMIU

 

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከጠቅላይ ሚንስትርነታቸው እና ከኢህአዴግ ሊቀመንበርነታቸው ለመነሳት ጥያቄ አቅርበዋል። ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ እንደዘገቡት ከሆነ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከጠቅላይ ሚንስትርነታቸው እና ከኢህአዴግ ሊቀመንበርነታቸው ለመነሳት ጥያቄ አቅርበዋል።

በቀጣይ ጠቅላይ ሚንስትሩን ማን ሊተካ ይችላል የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ነው። ዛሬ ለተለያዩ ሚዲያዎችም በሰጡትም መግለጫ ሰሞኑን በኃገሪቱ ላይ በተከሰቱት አለመረጋጋቶች ምክንያት የብዙዎች ህይወት መጥፋት፣ከአካባቢያቸው መፈናቀል እንዲሁም ኢንቨስትመንቶች የተጓጎሉ መሆናቸውን ጠቅሰው ገዢው ፓርቲም ሆነ መንግሥት የተለያዩ ማሻሻያዎችንም እየሰራ ነው ብለዋል። “ለነዚህ ማሻሻያዎች መሳካትም ሆነ እንዲሁም ላስቀመጥናቸው የመፍትሔ አቅጣጫዎች የመፍትሔ አካል ለመሆን በማሰብ በገዛ ፍላጎቴና ፍቃዴ የኢህአዴግ ኃላፊነቴንም ሆነ የመንግሥት ኃላፊነቴን ለመልቀቅ ጥያቄ አቅርቤያለሁ” ብለዋል።

ጥያቄያቸውንም የደኢህዴን እንዲሁም የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መቀበላቸውን አመስግነዋል። “ሥልጣን መልቀቅ መፈለጌን በሰለጠነ መንገድ በአዎንታዊ ተቀብለውታል። ” ብለዋል።