መከላከያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈርጌሳ
አጭር የምስል መግለጫ የሃገሪቱ የጸጥታ ሃይሎች በኣንድ ኮማንድ ስር ይታዘዛሉ ተብለዋል

አርብ ምሽት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለስድስት ወራት የሚቆይ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ አስታወቁ::

የሚኒስትሮች ምክር ቤትም ውሳኔውን በሙሉ ድምፅ እንደተቀበለውና: በሃገሪቱ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት የሽግግር መንግሥት ማቋቋም አስፈላጊ እንዳልሆነ ሚኒስትሩ ተናግረዋል::

በሃገሪቱ ያለው የፀጥታ ችግር እየተባባሰ መሆኑን ዛሬ ቅዳሜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተናገሩት ሚኒስትሩ ችግሩ በዋና ከተማዋ በአዲስ አበባም መንፀባረቁን ገልፀዋል::

ሚኒስትሩ እንዳሉት ኢህአዴግ ለ17 ቀናት ባደረገው ግምገማ ላይ ያለው ችግር በ15 ቀናት ውስጥ ካልተፈታ የአስቸኳይ ጊዜ ሊታወጅ እንደሚችል ቀደም ሲል ከስምምነት ላይ ተደርሶ እንደነበር ጠቁመዋል::

ለስድስት ወራት የሚቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በየጊዜው የሚገመገም ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ከተገፕ ለአራት ወራት ሊራዘም እንደሚችልም ተገልጿል::

አዋጁ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብ የተናገሩት ሚኒስትር ሲራጅ: የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚከታተል ኮማንድ ፖስት ተቋቁሟል::

ንጭ     –    ቢቢሲ/ርኛ