በንድነት ካምፕ ውስጥ እየታየ ስላለው “ኦሮማራ” ስለሚባለው አዲስ “ክስተት” እና የኦሮሞ ፖለቲከኞች ከእስር መለቀቅና ለወደፊቱ የሚከተሉት ፖለቲካ ምን ሊሆን እንደሚችል እስክንመለከት ድረስ ይህንን ከዚህ በታች የሉትን የተለያዩ አገራዊ ጉዳዮችን አንስተን እንመለከታለን።

ከጥቂት ቀናት በፊት አንድ ታዋቂ “አክቲቪሰት” በቀለ ገርባ <<ከጎንደር ስለመጡ ታሳሪዎች>> ያልተፈቱ እንዳሉ በቃለ መጠይቁ በመግለጹ ስለገለጸ ብቻ “አንድነት መጣች” የሚል የተለጠጠ ስሜታዊ አጀብ ያለው ጽሑፍ ኢመይል አድርጎልኝ ነበር። ይህ ስሜት የነ በቀለ ገርባ፤የነ ጃዋር፤የነ ዳውድ፤የነ ሌንጮ፤የነ ዲማ ነገዎ…..” “የጭራቅ ኦሮሚያ አገር ምስረታ” ሕልም ያቆማሉ ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ባደርግላቸሁ እንደ ዘወትር የምትንጫቹ እንዳላችሁ አውቃለሁ። ሆኖም መንጫጫትና እውነታ የተለያዩ ስለሆኑ ምንም ቢመርር አውነታውን ዋጥ አድርጉትና እንወያይ።

“የጭራቅ ኦሮሚያ አገር ምስረታ” የሚለው ቃል ግራ እንዳይገባችሁ፤ ግልጽ ለማድረግ፤ በሚቀጥለው ሰሞን ጽሑፌ የሚያትተውም በዚህ ርዕስ ነው። ኦሮሚያ ተብሎ በተቀየሰላቸው ጂኦግራፊ መሬት ውስጥ አገር ቢመሰርቱ የደቡብ ሱዳን ወይንም የሶማሌ ያህል የእርስ በርስ እልቂት ቢያንስ በሦሰት ክፍሎች ተከፍለው (የፖለቲከኞች ሹኩቻ፤ የሃይማኖተኞች ሽኩቻ፤ የማንነት ሽኩቻ፤ እና “ከተለያዩ ጎሳዎች የተወለዱ ግማሽ ኦሮሞና ግማሽ ሌላ ጎሳ የተዋለዱት እና በጥራት የሚፎክረው “ወርቅ” ኦሮሞ ደም መካካል ግጨት ሽኩቻ) መካከል እልቂት እንደሚያመጡ በዝርዝር ስለማቀርብ ነው፤ “የጭራቅ ኦሮሚያ አገር ምስረታ” የሚል አገላለጽ የተጠቀምኩት። ኦሮሞዎች የመገንጠል ሕልማቸው ቢሳካ አሁን ያሉት ልሂቃን የዚህ ክስተት ጥቃት ስለሚሆኑ እዛው ኦሮሚያ በሚባለው አገር እየተጋፈጡ ለመኖር ፍላጎት ስለሌላቸው (ዛሬም እንደምታዩት የሚኖሩት እዚህ ነው) ግጭቱን አባባብሰው እንደ ሶማሌዎቹ እውጭ ጋር ሆነው የአልሸባብ ዓይነት በባሌ ውስጥ የሚኖሩ ሶማሌዎች በኩል ተባባሪነት “ለእስላማዊ አክራሪዎች” አስረክበው ወደ ውጭ ይፈረጥጣሉ። ለዚህ ሰፋ ያለ ትንታኔ በሚቀጥለው እንመለከታለን። ከዚያም ወደ ትግራይ በተመሳሳይ እንመለከታለን። ከዚያም አክራሪ እስልምና ለኢትዮጵያ አስጊ ኤኢደለም ለሚሉትም የሚያብራራ እንመለከታለን። ትንተነው የሚያተኩረው የመገንጠል ዕድል ቢያገኙ የሚደርሰው ክሰተት የሚያትት ነው።

ይህ ለወደፊቱ የምትመለከቱት ሲሆን ዛሬ ግን በእነ በቀለ ገርባም ሆነ በእነ እስክንድር ነጋ እና እና መሰል ዜጎች ሰለ እርስ በርሳቸው መተዛዘንም ሆነ፤ ስለ ሌሎች ነገዶች እስር ስላሉ
አንስተው ‘ማሰብና መተዛዘን’ የአንድነት ምልክት ነው ብለው በስሜት ሰማዩን ለመንካት የሚቃጣቸው ሕዝብን በስሜት ስለ የሚነዱ ልሂቃን አንድ ነገር ለማለት እፈልጋለሁ።

ምኞት ጥሩ ነው። ግን ምኞት ከነባራዊው ጋር ሲገናኝ ብቻ ውጤት ይኖሮዋል። ነባራዊው ሁኔታ ያሳየን የ26 አመት “ሰብቨርዢን/ብከላ/ ባንድ ቀን የሚለወጥ አይሆንም። በእስረኞች መካካል እንዲህ ያለ መተዛዘንና መቀራረብ ሲከሰት “አንዳንድ ሊህቃን” አንድነት መጣች ዓይነት በስሜት የመዋጥ ክስተት ማሳየት የሚጠበቅና ባህሪያዊ ነው። ሆኖም እነዚህ በነዚህ እስረኞች እርስ በርስ መተዛዘን ወይንም አንድነታዊ ስሜት ማንጸባረቅ “ተፈጥሮአዊ የሆነ ጊዜያዊ የሰው ልጆች ስሜት/ኢንስቲንክት/ እንጂ ወደ “ፖለቲካው ወለል” ሲወርዱ ያ የጋለ ስሜት እቦታው ላይ አይገኝም። ባጭሩ እንኳ ቢያንስ ለ26 ዐመታት የተነጠፈው “እኛ” እና “እነሱ” የሚለው የነ በቀለ ገርባ ከሥር ያለው ድብቅ ንጣፍ ስንመለከት፤ ከላይ ካለው አሁን የሚንጸባረቀው ጊዜአዊ ንጣፍ በውርድም በቁመትም ስለማይጣጣም ከጊዜ ቆይታ አውነተኛውን ገጽታ እየደመቀ ይወጣል።

እንዲህ ያለ ክስተት ለማየት ሊታይ የሚችለው ምክንያት፤ሁለት ተጻራሪ የጎሳ አባሎች (ሁለት የተጻራ ፖለቲከኞችም ሊሆን ይችላል) በጋራ ጠላታቸው ምክንያት እስር ቤት የነበሩ ሰዎች እና በምድረ በዳ በረሃ አብረው ወደ ስደት ሲጓዙ በጠላፊዎች ተይዘው በደረሰባቸው የጋራ ጥቃት ምክንያት በጣም የተቀራረበ ወንድማዊና እህትማዊ ቤተሰባዊነት የትስስር ስሜት ባጭር ጊዜ ውስጥ ማዳበር የሚከሰት ባህርያዊ ነው።

እልም ባለ ምድረ በዳ ውስጥ ባንድ አጋች ተጠልፈው ስቃይ ደርሶባቸው ከዚያ ጭለማና ስቃይ ተለቅቀው ወደ አቀዱበት የስደት አገርም ገብተውም ቢሆን ያ አብሮነትና የመተዛዘን ስሜት ለተወሰኑ ጊዜያቶች መተሳሰብ መነጋጋር፤ በስልክ መደዋወል፤ መነጋጋር፤ መመካካር፤መረዳዳት ይቀጥሉና፦ ከጊዜ ቆይታ በኋላ የነበራቸው የጋራ መተዛዘን እና መመካከር ቀስ በቀስ ቀዝቅዞ፤ ሁለቱም ወደ እየ መንገዳቸውና ስሜታቸው በማቅናት የራሳቸው መንገድ ይቀይሳሉ ። ይህም ክስተት በግብጽ ምድረበዳ ውስጥ በጠላፊዎች ተይዘው በነበሩ፤ በአንድ ኤርትራዊ እና ኢትዮጵያዊ ወገኖች ያደመጥኩት የፓልቶክ ፖለቲካዊ ውይይት ነው። ይህ ስሜት አስቀድሜ ሳስብበት በመኖሩ በሁለቱም በኩል የተነገረው የፓልቶከ ወግ ሳደምጥ የነበረኝ አስተሳሰብ ሲገጣጠም በማየቴ ይህንን ርዕስ ላስተላልፍ ፈለግኩ።

በዚህ መልክ ኢትዮጵያውያን ከሚገባው በላይ በቀለ ገርባ ስለ ጎንደር ታሳሪዎች አሁንም እሰር ቤት ስላሉ ይፈቱ ብሎ ተናገረ ተብሎ በየፌስ ቡካችሁ በማሸብረቅ የምትጥሩ የሰማዩን ጣራ ለመንካት የሚዳዳቸው ሊሂቃን ‘አክቲቪስቶች” እባካችሁ እየተስተዋለ። ለዚህም በተመለከተ በሚቀጥለው ሰሞን የምሰጠው ትችት ጠብቁኝ። ሌላው ምክር፤ ለአንዳንድ ሚዲያዎች ነው።

መጀመሪያ ነገር ሚዲያው ትንሽ መሻሻል ቢያሳይም፤ አሁንም ከወገንተኛነት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ አልጸዳም። የተለየ ሃሳብ ያለንን የኔና መሰል ጸሐፊዎች አንድ ቀን ትለጥፉና (ይህ ለዘሃበሻ እና ሳተናው ድረገጽ አዘጋጆችን ነው) በማግስቱ አይታይም። የሃይለማርያም ደሳለኝ ጉዳይ 10 ተመሳሳይ ጽሑፎች ለሳምንት ይነበባሉ። እባካችሁ ተቃራኒ ሃሳቦችን አስተናግዱ። ሃይለማርያምን እርሱት!

አንባቢዎች ሆይ!

ሚዲያዎቹ ስትመለከቱዋቸው፤ ስለ ሃይለማርያም ደሳለኝ <<ከእልፍ አስከልካይነት ሥራው>> መባረሩ ትልቅ ዜና አድርገው ድረገጾች የሚያጣብቡትን ጸሐፊዎች ስትመለከቱ የተለየ አስተያየት ያላቸውን ጸሐፊዎች የሚያቀርቡት አስተያየት ለሕዝቡ ለናንተ እንዳይደርስ ማድረግ በሃሳብ ላይ እገዳ ማድረግ ነው። ሚዲያዎችም ሆኑ ጸሐፊዎች ስለ ሃይለማርያም ጉዳይ እንዲህ ተጨናንቀው ሲነግጋጉ ማየቴ እጅግ ገርሞኛል። ሌላ ቀርቶ ወንጀለኛውና የፈረንጅ ቅጥረኛው “ታምራት ላይኔ” ሕዝብ ከሚያጃጅልበት ዓለም ደውለው ስለ ሃይለማርያም ደሳለኝ መባረር እንዲያስተምረን በሚዲያ አቅርበውታል። ተቃዋሚው ለሃይለማርያም ደሳለኝ ምን ያህል ቦታ ሰጥቶት እንደነበረ የሚያሳየኝ ይህ ጋጋታ “እጅግ ስሜታዊ ” የሆነ ተቃዋሚ የበዛበት መሆኑን ያሳየን አጋጣሚ ነው። አንድ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር “ጅነዲን ሰዶ፤ጃዋር መሐመድ፤ሌንጮ ለታ እና ታምራት ላይኔን” ጠርተው እባካችሁን እስኪ አስተምሩን ብለው <<በኢሳትም ፤ በሕብር ራዲዮም ፤ ሲቢኤስም …….ወዘተ ወዘተ…>> ተጋብዘው ተኩራርተው እንዲያሾፉብን ሲደርግ ይህ ተቃዋሚ ምን ይሻለዋል? ያሰኛል።

በመጨረሻ ይህ መልእክት አስፈላጊ ስለሆነ ልብ ብላችሁ አንብቡት።

ኢንጂኔር ይልቃል ጌትነት የተባለው የሰማያዊ ፓርቲ መሪ <<ኦሮሚያ ክልል አማራዎች ላይ እየተካሄደ ያለው ጥቃት በአስቸኳይ ይቁም! – በኦሮምያ ክልል በጎሮ ቀበሌ ጥቃት የተፈፀመባቸው አማራዎች አሁንም ሜዳ ላይ እንደታገቱ ናቸው!!! (ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት)>> የሚል መልዕክት ያስተላለፈው በwelkait.com ድረገጽ ተለጥፎ አንብቤአለሁ። ይህ አማራን የማጥቃት ዘመቻ ዛሬም በቀጣይነት እየተካሄደ መሆኑን እየነገረን ያለው ይህ ዜና በድረገጾች ሽፋን አላገኘም።

የዜና ድረገጾች፤ በሃይለማርያም ደሰለኝ እና በእነ በቀለ ገርባ ተጣብቦ አማራ ህጻናት፤ እመጫቶች፤ አዛወንቶች፤ አባት እና እናቶች፤ ከመኖርያ ቤቶቻቸው ውጡ እየተባሉ መባረራቸው ድረገጸች እንደተለመደው “ጀሮ አልሰጡትም”። ይህ ደጎሞ አዲስ ነገር ሳይሆን ተቃዋሚው ሚዲያም ሆነ ጸሐፍትና የፖለቲካ ድርጅቶች በአማራ ላይ ያለው ደንታ ቢስነት ዛሬም እንደቀጠለበት ነው። ስለዚህ አማራ ተወካዮችና ድርጅቶች ይህንን ዜና በየድረገጾቻችሁም ሆነ በስብሰባም ሆነ በተቻላችሁ መንገድ “የአማራ ሕዝብና ወጣት” ዜናው አንዲደርሰው እንድታደርጉ ጥሪ አቀርባለሁ።
ዜናው ለአማራ ወጣቶችና አማራ ሕዝብ ካልተዳረሰ፤ አሁን በኦሮሞም ሆነ በምስራቅ አካባቢ ያለው ጸጥታ ተጠያቂነት ስሌላው በነዚህ ዜጎች ላይ የከፋ ጥቃት ሊደረስ ስለሚችል፤ እና ተቃዋሚውም ሆነ ሚዲያው በነ በቀለ ገርባ መፈታት በነ ሃይለማርያም ደሳለኝ ውስጥ እየዳከረ ስለሚገኝ እነዚህ ዜጎቻችን አድመጭ አጥተው ለከፋ ጥቃት እንዳይጋለጡ በምታምኑዋቸው መንገዶች ጭምር የዜናውን ግልባጭ እያደረጋችሁ ብትልከላቸው ጥቃቱ’ በሕዝብ ከታወቀ አንድ አርምጃ ያስኬዳል።

አመሰግናለሁ! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ) getachre@aol.com