10 የካቲት 2010 ዓ.ም (19 February 2018)

‘የሚጠይቅ ፈላስፋነው’ ይባላል። እኔም ፈላስፋ ባልሆንም መጠየቅ እውዳለሁ። ያ ሲባል ለሚጠየቁ ጥያቄዎች ሁሉ መልስ ይገኝላቸዋል ማለት አይደለም። ስለሆነም ለዚህ ጥያቄ የተሟላ መልስ የሚሰጥ እውቀት ባይኖረኝም የሚታየኝን ለማስጨበጥ እሞክራለሁ ።

ህወሃት ቀደምቶቹ የኢትዮጵያ ገዢዮች ማዕከል የአዲስ አበባን ቤተገዢዮች (ቤተ መንግሥት) መቀመጫው ካደረገበት 1983 ዓ.ም ጅምሮ በመጠንና በዓይነት የተለያዩ በርካታ ጠመንጃ አልባ ፀረ-ህወሃት አምጾች ተደርገዋል እየተደረጉም ነው ።እንደማንኛውም የተፈጥሮ ዕድገት ወይም ወደፊት የመሄድ ሕግ(natural progression) ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ፀረ-ወያኔ ትግሉ በዓይነትም በመጠንም ከፍ እያለ መምጣት የለውጥ ተስፋ የሚስጥ ቢሆንም  የሚያስፈነድቅ አይደለም ።

ይህንን በተመለከተ የኢትዮ-ዲያስፖራ ጋዜጠኞች ለአንዳንድ ለኢትዮ-ዲያስፖራ ፖለቲከኛ ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች አስተያየት ሲጠይቁ፣ከሁለት ዓመት በፊትም፣ከዓመት በፊትም፣አሁንም ፣የሚሰጡት መልስ ወያኔ (አበቃለት፣ስድስት ወር፣ዓመት ወዘተርፈ አይቆይም) ሲሉ ይደመጡ ነበር፤ይደመጣሉ ። ነገር ግን እነሱ በሚሉት አጭር ግዜ የወያኔ መውደቅ ዝርዝር ምክንያቶች አይሰጡም ፤ መልሳቸው ሾላበደፍን ነው ።

ግምትና እውነታ ፣እይታና እውነታ ፣መላምንትና እውነታ ወዘተ… እየብቻ ናቸው ።በርግጥ ወያኔና ሥርዓቱ በሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ክፉኛ ተጠልቷ።አልተጠሉም ፣ከሕዝብ ጋር ናቸው የሚሉ ካሉ የሥርዓቱ ተጠቃሚዮች ብቻ ናቸው። የአንድን ፀረ-ሕዝብ መንግሥት የመውደቅ ዋንኛ መሳርያ በሚገዛውን ሕዝብ መጠላትና የሚገዛውን ሕዝብ አልታዘዝ ሲለው ነው ።

አገራችን በጣሊያን በተወረረችበት ወቅት አያቶቻችንና አባቶቻችን ከሰማይ የመርዝ ጋዝ እየረገፈባቸው፣በጎራዴና በጦር ከጣሊያን ታንክዎችና መድፈፎች ጋር እንደተፋለሙ፤የ60ዎቹ  ወጣቶች በድንጋይና በጠጠር የአጼ ሃይለሥላሴን ጨቋኝ ሥርዓት ከሚያስጠብቁ ፖሊሶችና ፈጥኖደራሾች ጋር ተፋልሟል ፤ የ70ዎቹ ወጣቶች በጡጫቸው፣በእጆቻቸውና በራስ ምት ከፋሽስቱ ደርግ ታንከኞችና መድፈኞች ጋር ግብግብ ገጥሞዋል፤ ጉረሮ ለጉረሮ ተናንቀዋል።

የአሁኖቹ የ21ኛው ክ/ዘመን ባለጽወኞቹ የኢትዮጵያ ወጣቶች ከሰማይ በሄሊኮፕተር በተጫኑ አነጣጥሮ ተኳሾች ጥይት እየተርከፈከባቸው፣ በምድር የናዚ- ጅርመኒ ኤሰኤስ  <s s> አቻ በሆኑት አጋዚዎች ጥይት እየተደበደቡ ከወያኔና ከሥርዓቱ ጋር በሰላማዊ አመጽ እየተፋለሙ ይገኛሉ ። ይህ በወያኔና በሥርዓቱ ላይ የመረረ ጥላቻ ለመኖሩ በቂ ማስረጃ ነው ።

ከዚህ አኳያ/እይታ ብቻ የህወሃት የአገዛዝ ሥርዓት መውደቂያ ተቃርቧል የምንል ከሆነ ተሳስተናል ። ህወሃት በርካታ ሥልጣን ማራዘሜያ ምንጮች አሉት፤ስለሆነም ትግሉ ውስብስብ ነው የሚሆነው ። ህወሃት የሚያበቃለት ወይም የህወሃት የአፓርታይድ ሥርዓት የሚበረከከው የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲሟሉ ነው እላለሁ ።

1.ትግሉ የተበታተነና ግብታዊ ነው። አማአክሎ የሚመራ ድርጅትና መሪ የለውም፣ስላማዊ አማጽያን በቀላሉና በተናጥል ለመመታት የተጋለጡ ናቸው። መሪ ድርጅትና የተደራጀ አመራር ባለመኖሩ በፀረ-ሕዝብ ደርግ የተነጠቀው የ66ቱን አብዮት ጋር ማዛመድ ያስፈልጋል። ከዚህ የከፋ መዓት እንደሚያመጡ፣ ሥልጣናቸው በምን ዓይነት ዳብሎስ ለመተካት እንዳሰቡ የምናውቀው ነገር የለም። ስለሆነም የፖለቲካ ድርጅቶች የጋራ ማዕከል፣ አስተማማኝ የጋራ እቅድ <realistic plan> ፣የጋራ እስትራተጂ፣የጋራ ስልት፣የጋራ ንዑስ ማታጌያ ማዕከሎች (peripheries)፣የጋራ የእዝ ሰንሰለቶች፣የጋራ ማታጌያ ቁሳቁሶች ወዘተ.. ሲኖር

2.የሁሉንም ከተሞችና ገጠሮች ኢትዮጵያውያን አንድላይ ተነስተው እየሞቱም ፣እየተደበደ          ቡም ፣እየታሠሩም ወዘተርፈ ሲታገሉ፤ የህወሃት ሥርዓት የሚዘውና የሚጨብጠው ሲያሳጡ ፤ግራሲያጋቡ

  1. የወያኔዎች ሥልጣንና ሃብት ክምችት፣የመንግሥታት ተወካዮች፣የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ወዘተርፈ መናኽርያ የሆነው አ/አበባ በአመጽ ሲናውጽ ፤ቀውጢ ሲሆን

4.ለመከላኬያ ሃይል፣ለአየር ሃይል፣ለፖሊስ ሠራዊት፣ለጸጥታና ለስለላ ግብረ ሃይል፣ለካድሬዎች ፣ለቢሮክራሲውና ለተራ ሠራተኛው ደሞዝ መክፈል ሲያቅተው ፤የሚበሉትና የሚጠጡትን አጥተው ከሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ሲሰለፉ

5.ገንዘብ አበዳሪና ገንዘብ ለጋሽ አገሮች ማበደርና መለገስ ሲያቆሙ ፤በወያኔና በሥርዓቱ እምነት ሲያጡ ፤ ሕዝባዊ አመጹን ከሚመሩት የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ሲሰለፉ

6.የትግሉና የሕዝባዊው አመጽ ቅኝት ማለት በስትራተጂ፣በስልታዊነት፣በፖለቲካዊ እውቀት፣በፖሊቲካዊ ስሌት፣እንቅስቃሴ ወዘተ..ወያኔዎች ከሚያደርጉት ፀረ-ሕዝብ ትግል እስትራተጂ፣ስልት፣ፖልቲካዊ እውቀት ወዘተ..በልጦ ሲገኝ

7.እያወራንም፣እየበላንም እንደምናስብ ሁሉ- ትግሉ ወደ አልጠበቅነው አቅጣጫ ዘንበል፣ፈትለክ ፣ሙልጭ ወዘተ..እንዳይል እያጠርን፣እየከበብን፣እየተቆጣጠርን ወዘተ..መታገል ስንችል

8.ባጠቃላይ የወያኔ ሥርዓት በስትሮክ/stroke ሲመታ ማለት የወያኔዎች ዓለም ሲያበቃ (when it become in a state of Big Crunch or Zero-G) ሲሆን