December 21 2018

የኦሮሞ ብሄርተኞች ኢትዮጵያን ማስተዳደር ከፈለጉ አፋን ኦሮሞን የየትኛውም ብሄረሰብ ብቸኛ ሃብት ባልሆነው በግእዝ ፊደል ወይም ኢትዮጲስ እንዲፃፍ ቢፈቅዱ የተገንጣይ ስሌት እርግፍ አድርገው መተዋቸውንና፣ ኢትዮጵያን ከነሙሉ ታሪኳ ለማቀፍ መወሰናቸውን ስለሚያሳይ ሃገር የሚያረጋጋ ይመስለኛል።
በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ መሪነት ብቸኛ የአፍሪካ ፊደል የሆነውን ግእዝ የአፍሪካ ቋንቋዎች ፊደል እንዲሆን ኢትዮጵያ ሃሳብ ታቀርባለች ብዬ አስባለሁ።
ያ ከመሆኑ በፊት ግን የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ሁሉ በግእዝ ፊደል እንዲጠቀሙ ማግባባት ያስፈልጋል፣ ይህም ሃላፊነት በጠቅላይ ሚኒስትሩና በኦቦ ለማ መገርሳ ትከሻ ላይ ወድቋል። እነርሱ ኦሮሞን ማሸነፍ ከቻሉ፣ የተቀረው ገብስ ነው።
የተለየ የኦሮሚያ ሪፐብሊክ ለመመሥረት የወረረን የላቲን ቁቤ እንዲያከትም መከራከር፣ መምከር መጀመር አለብን። በጉዳዩ ላይ ብዙ ጥናት ያደረጉትም የኮምፒዩተር ሳይንስ ምሁር ዶክተር አበራ ሞላ ከሰሞኑ ወደ አዲስ አበባ ስለሚያቀኑ፣ መንግስት፣ ምሁራንና፣ ሚዲያው ተገቢውን ትኩረትና መድረክ ይሰጣቸዋል ብዬ አስባለሁ። ከ42 ዓመታት በፊት በግእዝ ፊደል የተፃፈውን በሪሳ ጋዜጣ እስኪ ተመልከቱት።