February 23, 2019 518SHARESShareTweet

አክሊሉ ወንድአፈረው  (የግል አስተያየት) ethioandenet@bell.net

የካቲት 16፣2011( ፌበርዋሪ 23፣ 2019)

በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ  የተጀመረው ለውጥ ቁልፍ በሆኑ ጥያቄወች  ላይ  ምላሽ እየሰጠ የሚጓዝባቸው ሂደቶች በሰፊው ይስተዋላሉ። የፖለቲከ ምህዳሩን  ከማስፋት (ሊበራላይዜሽን ) ወደ ዴሞክራሲያዊ መሰረት መጣል (ዴሞክራታይዜሽን)  ለመሸጋጋር የተለያዩ ድንጋጌወችን ማውጣት አፋኝ ህግጋትን መሻርና  ዴሞክራሲአዊ ስርአትን እውን ሊያደርጉ የሚችሉ ተቋማትንም መገንባት አሰፈላለጊ ነው።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለብሔራዊ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን አባልነት ከተሰየሙት 41 ግለሰቦች መካከል ቃለ መሃላ ከፈጸሙት ውስጥ ከፊት ረድፍ ከግራ ወደ ቀኝ አቶ አያልነህ ሙላቱ፣ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) እና አቶ ደበበ እሸቱ ይገኙበታል

ተቋም ሲባል ዴሞክራሲአዊ ስርአትን አውን ለማድረግ በቅርጽም በይዘትም የሚያግዙ ተቋማትን እንጂ ማንኛውንም ተቋም ማለት አይደለም። ህወሀት ኢህአዴግ ለ27 አመታት እጅግ ዘግናኝ የሆነ ግፍ የፈጸመው፣ እንድነተችንን ያዳከመውና መራራቅ ስር እንዲሰድ ያደረገው በተቋማት ተደግፎ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም።

በዚህ አንጻር በዚህ ጽሁፍ ውስጥ በቅርቡ የታወጀውን የብሄራዊ እርቅና ሰላም  ኮሚሽን ምስረታ በተመለከተ የሚታዩትን አበረታች እና አሳሳቢ ገጽታወች በተወሰነ ደረጃ እዳስሳለሁ ። ይህን ጽሁፍ በማድረግም ጠንካራ ጎኖቹን ይበልጥ ለማጠናከርና ድክመቶችንም በጊዜው ለማረም ግብአት ይሆናል የሚል እምነት አለኝ። ከዚህ በተጨማሪም ለወደፊቱ በሀገራችን ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ለሚወሰዱ እርምጃወች አንዳንድ ትምህርትንም ይሰጣል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ።

መነሻ                                                                                    

ሕዝባችን ያሳለፈው  ሰቅጣጭና በመብት መጣስ የተሞላ ታሪክ ሁሉንም የህብረተሰባችንን ክፍል እጅግ ጎድቷል። ይህ ተደጋጋሚ የመብት ረገጣ አለመተማመንን ፣ በሀገር አለመመካትን፣ የበላይና የበታች ስሜትን ወዘተ አስፍኗል።በሀገራችን ታሪክም ሆነ በወደፊት አቅጣጫዋ ላይ  ከመግባባት ይልቅ ጥልቅ ልዩነት እንዲሰፍን ሆኗል። በነዚህና ተዛማጅ በሆኑ ምክንያቶችም ሀገራችን በፖለቲካ ምስቅልቅልና በጦርነት አዙሪት   ከተተበተበች እጅግ ብዙ ጊዜ ሆኗል።

በሀገራችን ውስጥ በመንግስታትና፣ በህዝብ፣ በመንግስታትና በፖለቲካ ድርጅቶች፣ በተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች መሀላ፣ በያንዳንዱ ፖለቲካ ድርጅት ውስጥ፤  በተለያዩ ማህበረሰቦች መሀል ወዘተ ግጭቶች፣ አለመተማመኖች ወዘተ እንደተከሰቱ፣ እነዚህም ግጭቶች ባግባቡ ሳይፈቱ እስካሁን እደቀጠሉ ይታወቃል።

ይህን የተወሳሰበ ችግርና እጅግ የተጎዳ የወገኖቻችንን ስብራት ለማከምም ሆነ የተወሳሰበውን ብሶትና አለመግባባት ለመቅረፍ ታላቅ ትግስትን የሚጠይቅ በፍትህና እውነት ላይ የተመሰረተ የብሄራዊ እርቅ ሂደትን ተግባራዊ ማድረግ ተገቢ ነው።

ብሄራዊ እውቅ ወይም እርቀሰላም  ሲባል  ቢያንስ ላለፉት አርባና ሀምሳ አመታት የደረሰውን የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ረዘጣ  ያስከተለውን በደልና ሰቆቃ በመመመርመር  በቂም በቀል መንፈስ ሳይሆን እውነትን መሰረት ያደረገ ፍትህ ተጎጂወች እንዲያገኙና አስከፊው የታሪካችንም ምእራፍ ተዘግቶ በይቅር ባይነትና  በታደሰ መንፈስ የግጭት አዙሪትን የምንሰብርበት አንድንትን መተሳሰብን፣ እኩልነት የምንገነባበት ሂደት እውን ማድረግ ማለት ነው።

በሀገራችን ውስጥ የ እርቅና ሰላም  ኮሚሽን የተመሰረተው በ ታህሳስ 16፣  2011 (ዲሰምበር 25፣ 2018 https://www.satenaw.com/amharic/archives/64129  ) በጸደቀ አዋጅ  ሲሆን የኮሚሽኑ አባላት ስም ዝርዝር ለፓርላማው ቀርቦ የጸደቀው ደግሞ በጥር 28፣ 2011 (በ ፊበርዋሪ 5፣ 2019) ነበር   https://www.satenaw.com/amharic/archives/64132

በጠቅላጠይ ሚኒስቴር አብይ የሚመሩት መንግስት ይህን ታላቅ ተግባር እውን ለማድረግ የሚያሰችል የመጀመሪያውን እርምጃ መውሰዱ የሚያበረታታና የሚያሰመሰግነውም ነው። ይህን ስልም የአዋጁ አላማና የሚሽፍናቸው ጉዳዮች ቢያንስ ከላይ የተጠቀሰውን የብሄራዊ እርቅ ያካትታል በሚል እምነት ነው።

ብሄራዊ እርቅ በሀገራችን ተግባራዊ እንዲሆን ለረዥም አመታት ብዙወች  ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ሲታገሉለት የነበረ ሆኖም በገዝው ህወሀት መራሹ ኢህአዴግ እምቢተኛነትና  በተወሰኑ በተቃዋሚው ካምፕ የነበሩ ድርጅቶች ተቃውሞ ሳይሳካ  የኖረ ጥሪ ነው።

አሁን የሚታየው አዲስ ጅምር አበረታችነቱ  እንዳለ ሆኖ፤  ውጤታማ እንዲሆን ደግሞ ገና ከመጀመሪያው በጥንቃቄ ሊታዩ የሚገባቸው ጉዳዮች ውስጥ ጥቂቶቹን ከዚህ በታች አቀርባለሁ። ለግንዛቤ እንዲረዳም በተመሳሳይ የብሄራዊ እርቅ ጎዳና የተጓዙ ሀገሮችን  ልምድ ምን እንደሚመስል በመጠኑ አሳያለሁ።

የእርቀሰላሙ ኮሚሽን  ተመራጮች መመዘኛና ማንነት ገና ከመጀመሪያው  ግልጽ የመሆን አስፈላጊነት

የብሄራዊ እርቅን  (እርቀ ሰላም) አላማ ታላቅነት ስንመለከት ይህን እውነታ ተግባራዊ ለማድረግ ሀላፊነቱን የሚሸከሙ ሰወች እነማን ናቸው ምን  አይነት መመዘኛ ማሟላት አለባቸው. ምን አይነት ልምድ ፣ ማህበራዊ ከበሬታ ፣ እውቀት፣ ወዘተ ሊኖራቸው ይገባል  የሚለው እጅግ መሰረታዊ ጥያቄወች ሆነው እናገኛለን።

ሂደቱ ገና ከመጀመሪያው በተለያዩ ክፍሎች በተለይም በተጎጂ አካሎች ታማኒነትን እንዲያገኝ ለማድረግ ለዚህ ከፍተኛ ሀላፊነት የሚመረጡ ግለሰቦችን  መመዘኛወች በተመለከተ የተለያዩ  ባለድርሻወች ሀሳብ ሊሰጡበትና ሊስማሙበትም ይገባል። ይህ ሂደት የተጎጂ ወገኖችን ፍትህ ማሰገኘትና ስብራታቸውንም ማከም ዋና አላማው ስለሆነም ፣ የነርሱን ግብአት ማካተትን ታላቅ ቦታ የሚሰጠው ተግባር  ነው።

በቀጣይነት የህዝብን  አመኔታን ለማግኘትም  ለዚህ ሀላፊነት የሚመረጡ ሰወች የሚመረጡበትን መሰረታዊ መመዘኛወች ለህዝብ ግልጽ ማድረግና እያንዳንዱ ተመራጭም  የተባሉትን መመዘኛወች እንደሚያሟላ ማረጋገጥ  እምነትን ለማዳበር እጅግ አሰፈላጊ ጉዳይ ነው።

ከዚህም አልፎ የተመራጮች (የኮሚሸን አባላት ) አመራራጥን በተመለከተም ህዝብ  በተለያየ መልክ የእጩወች ጥቆማ እንዲያደርግና ተከታታይ ግብአት እንዲሰጥ  የሚያሰችል አሰራርን እውን ማድረግ ብሄራዊ እርቅ የኮሚሽኑን ታአማኒነት ይበልጥ የሚያጠናክር ህዝብ ኮሚሽኑን የኔ ነው ብሎ አመኔታን እነዲሰጠው የሚያግዝ እርምጃ ነው።

በደቡብ አፍሪካ ፣ በሴራሊዮብን በላይበሪያም ሆነ በቲሞር የተካሄዱት የ አርቅ የኮሚሽነሮች ምርጫወች መመዘኛወች ከሞላ ጎደል የሚከተሉትን ያካተቱ ሲሆኑ፣ እነዚህ መመዘኛወች በህዝብ ግብአት የዳበሩና  ለህዝብም በጊዜ ግልጽ ተደርገው እንደነበር መግለጥ ተገቢ ነው።

የዚህ አይነት ግልጽ አካሄድ ተግባራዊ ባልተደረገበት ተመራጮችም (የኮሚሽኑ አባላት)፡ በምን ሁኔታ እንደተመረጡ ባግባቡ በማይታቀውበት ሁኔታ ኮሚሽኑ ሰፊ ተቀባይነትና ታአማኒነትን  እንዲያገኝ ማድረግ  እጅግ ከባድ ይሆናል።

የእርቅና ሰላም ኮሚሽኑ አባላት  አመራረጥ ሂደት ተአማኒነት እንዲኖረው የማድረግ አስፈላጊነት

የተለያዩ ሀገሮች ተመክሮ እንደሚያሳየው ይህን ባለብዙ ፈርጅ የተጠራቀመ ችግር እንፈታለን ብሎ የሚነሳ ክፍል የመጀመሪያው ስራ የእርቀ ሰላሙ ሂደት በሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም ሰለባ በሆኑ አካሎች ታአማኒነትን እንዲያገኝ  ማድረግ ነው። ይህን ለማድረግም ፣ ሽፍጥን አግላይነትን፣ የሌሎችን ጉዳት ዝቅ አድርጎ መመልከትን ፣ የተወሰኑ ክፍሎች የፖለቲካ መሳሪያ  ሆኖ መታየትን ማስወገድ የሚቻልበትን አካሄድ በጥንቃቄ መምረጥና  መከተል አስፈላጊ ው።

በዚህም መሰረት ገና ከመጀመሪያው ከሰላምና እርቅ ኮሚሽኑ አባላት አመራረጥ ጀምሮ አካሄዱ ግልጽነት ያለው፤ አግባብ ካላቸው ክፍሎች በተለይም የመብት መጣስ ሰላባ ከሆኑ ክፍሎች ግብአትን ያካተተ፤ ግልጽና የህዝብ እምነትን የሚያዳብር ሆኖ መገኘት ይኖርበታል።

የ እርቅና ሰላም ኮሚሽን አባላት ምርጫ  ነጻ መሆንን ፣ ብቃትና ታአማኒነታቸውንም  ለማረጋገጥ የኮሚሽኑን አባላት ምርጫ  በመንግስት መሪ በብቸኝነት ወይም በግብታዊነት በሚሰጥ ሀላፊነት በተወሰኑ  ምርጥ ግለሰቦች አማካሪነት የሚካሄድ  ሳይሆን የሀገሪቱን ታሪካዊና ተጨባጭ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና የተወሳሰቡ ችግሮች (ቅራኔወች) በጥንቃቄ ባገናዘበ ሁኔታ የተለያዩ ባለድርሻወችን ያሳተፈ አስመራጭ ኮሚቴ በኮሚሽን አባላቱ ምርጫ ላይ ሀላፊነት ወስዶ በቀጥታ  ሊመራው  እንደሚገባ የተለያዩ ሀገሮች ልምድ አሳይቷል።

የዚህ አይነት መሰረት ሳይመቻች ከፍ ያለ ታማኒነትን ማግኘት፣ ሰላባ የሆኑ ሁሉ ሂደቱንና ተቋሙን “ለእኔም  ፍትህን ያሰገኛል” ብለው ኮሚሽኑን እንዲተባበሩ ማድረግ እጅግ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ይህ ካልሆነ ደግሞ የእርቀሳላሙ ሂደት ገና ከመጀመሩ ይከሸፋል፣ የግጭትና የጦርነት አዙሪትም ይቀጥላል።

የተለያዩ ሀገሮች ልምድ እንደ ማሳያ

ብሄራዊ እርቅን በተሳካ ሁኔታ በመተግበር  ከሚታወቁት ሂደቶች ውስጥ የደቡብ አፍሪካው የእውነትና የኢርቅ ኮሚሽን   (Truth and Reconciliation Commission TRC) አንዱና አንጋፋውም ነው። ይህን ተግባር በሀላፊነት ለውጤት ያደረሰው ኮሚሽን ምስረት የተካሄደው የተለያዩ ፖለቲካ ድርጅቶችና ሲቪክ ማህበረሰብ ወኪሎች እንዲሁም የገዥው ያአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ( ኤ ኤን ሲ ANC)  አባላትን አካትቶ  በተዋቀረ ኮሚቴ  በጋራ ባካሄዱት የእጩወች ምርጫ አማካኝነት ነበር። ደቡብ አፍሪካውያን የኮሚሽን አባላትን በመጠቆም ሳይቀር ቀጥተኛ ተሳታፊ ሆነው ነበር። https://www.britannica.com/topic/Truth-and-Reconciliation-Commission-South-Africa

እጅግ አሳዛኝና ዘግናኝ በሆነ የዜጎች ሰቆቃና የሰብአዊ መብት ረገጣ ውስጥ ያለፈችው ላይበሪያም ብትሆን በህዝቧ ውስጥ የደረሰውን ስብራት ለመጠገን የተጓዘችበት የብሄራዊ እርቅና እውነት ጎዳና ሲሆን ይህን ሀላፊበት እንዲመሩ የተመረጡ የኮሚሽን አባላትም የተመረጡት ሶስት ከሲቪክ ማህበረሰቡ የፖለቲካ ድረጅቶች ሁለት ወኪሎች አንድ ከተባበሩት መንግስታት ወኪል እና አንድ ወኪል ደግሞ ከምእራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማብህበረሰብ  (ECOWAS)  ተብሎ ከሚታወቀው የምእራብ አፍሪካ ሀገሮች  ድርጅት ወኪል የተውጣጣ ሰባት አባላትን ባካተተው ኮሚቴ ነበር https://www.refworld.org/pdfid/473c6b3d2.pdf

የረዥም አመታት የ እርስ በርስ ጦርነትና የብሄር ክፍፍል ስትተራመስ የኖረችው የምእራብ አፍሪካዋ ሴራሊዮን  የብሄራዊ እርቅ ኮሚቴ አባላትን ምርጫ ያካሄደው ስድስት ሰወችን ያካተተ የአስመራጭ ኮሚቴ ሲሆን ይህ አስመራጭ ኮሚቴ የተውጣጣውም ከሚከተሉት ክፍሎች  አንድ አንድ ወኪሎችን በማካተት ነበር ፡፡

ከ Revolutionary United Front of Sierra Leone  ከተሰኘው የፖለቲካ ስብስብ፤  ከጦር ሀይሎች፣  ከሰብአዊ መብት ድርጅቶች ፎረም፣ የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ድርጅት ወኪል እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሀፊ ልዩ መልእክተኛ በኮሚቴው አስተባባሪነት ።

በሴራሊዮን ሁኔታ የኮሚሽኑ አባላት ገሚሱ ከሀገር ውስጥ ሎሌሎች ደግሞ በውጭው ሀገር ከሚገኙ ሴራሊዮናውያን የተዋቀረ ሲሆን በውጭው የነበረውን የኮሚሽን አባላት ምርጫ ያቀነባበረው ደግሞ  በጀኔቭ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር (The Office of High Commissioner for Human Rights (OHCHR )   ጽህፈት ቤት ነበር  http://www.sierraleonetrc.org/index.php/national-vision-for-sl

ለማጠቃለል ሁሉም የእኔ ብሎ የሚቀበለው ውጤትን ለማግኘት፣ ተጎጂወች ያለምንም ፍራቻና ቸልተናነት በግልጽ የደረሰባቸውን በደል ለማካፈል እንዲችሉ ለማበረታታት ሁሉም ባለድርሻ የተሳተፈበትና አመኔታን የሰጠው  ሂደት ተግባራዊ መሆኑ  መሰረታዊ ጉዳይ ነው።

በእኛ ሀገርስ?

በሀገራችን ውስጥ በጠቅላይ ሚኒስቴር    አብይ አማካኝነት  የእርቀ ሰላም ኮሚሽኑን  ለማቋቋም  የቀረበው ረቂው አዋጅ በፓርላማው ቀርቦ የቀደቀው  በታህሳስ 16፣ 2011  (ዲሰምበር 25፣ 2018) ነበር። የኮሚሽኑ አባላት ስም ዝርዝር ለፓርላማው ቀርቦ የጸደቀው ደግሞ በጥር 28፣ 2011  ( በ ፊበርዋሪ 5፣ 2019  )፡ማለትም ባንድ ወር ከሁለት ሳምንት ውስጥ ነበር ማለት ነው።

ከአዋጁ  የሚመነጭ ድክመት

የእርቀሰላም ኮሚሽኑን አመራረጥ በተመለከተ በአዋጁ ውስጥ የሚከተለው ሰፍሮ ይገኛል፡፡

የኮሚሽኑ አባላትና አሰያየም

1/     የኮሚሽኑ አባላት ቁጥር በመንግስት የሚወሰን ይሆናል፡፡

2/     የኮሚሸኑ ሰብሳቢ ፣ምክትል ሰብሳቢ እና ሌሎች አባላት በጠቅላይ ሚኒስቴሩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ይሰየማሉ::

3/     የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ የኮሚሽኑ ፀሐፊ ሆኖ ያገለግላል::

በአዋጁ እንደተመለከተው፣ በዚህ ሂደት ውስጥ የኮሚሽኑን አባላት ለመምርጥ የተቋቋመ (በይፋ የሚታወቅ) አካል አልነበረም። ተመራጮቹን  “ በጠቅላይ ሚኒስቴሩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ይሰየማሉ “  ከማለት ሌላ  ለጠቅላይ ሚኒስቴሩ በእጩነት ማን እንደሚመርጣቸው  በምን መመዘኛ አጣርቶ ለሀላፊነት እንደሚያጫቸው የሰፈረ ነገር የለም።

የባለድርሻወች ግብአት አለመኖር

አዋጁ የኮሚሸኑን አባላት አመራረጥ በተመለከተ በሂደቱ ላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ግብአት እንዲኖራቸው የደነገገም  አይደለም። የሰብአዊ መብት ጥሰት ሰለባ የሆኑ ዜጎችም ሆኑ አጠቃላይ ዜጎች  ድምጻቸውን ለማሰማት የሚያስችል አሰራር (ሜካኒዝም) ባዋጁ ውስጥ አልተካተተም።

አዋጁ ከሚለው ውጭ የተካሄደ ምክክር  ቢኖር እንኳ በሚስጥር የተካሄደ እንጂ ግልጽነት ያለው ነው ለማለት አይቻልም። ስለዚህም የኮሚሸኑ አመሰራረት ድክመት የሚጀምረው ከማቋቋሚያ አዋጁ ነበር ችግሩ ሲስተሚክ ነው ማለት ይቻላል።

የኮሚሽኑን አባላት ምናልባት ጠቅላይ ሚኒስቴሩና አማካሪወቻቸው ዝርዝር አዘጋጅተው ራሳቸው መርጠዋቸው ይሆናል። ይህ ታዲያ ለጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ ያለን አክብሮት እንዳለ ሆኖ፣ የኮሚሽኑን  ታአማኒነት ከፍ አያደርገውም። ጥንካሬም  አይሰጠውም።

ምናልባትም ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ የሚቀርቧቸውን  የተወሰኑ ሰወች ወይም የድርጅት ተወካዮች አማክረው ባገኙት ጥቆማ መሰረት የመጨረሻ ውሳኔ ሰጥተውም ሊሆን ይችላል። ይህም ቢሆን የኮሚሽኑን ገለልተኛነትና ታአማኒነት ከፍ የሚያደርገው በተለይም በተጎጅወች እይታ የመተማመንን መሰረትን  የሚገነባ አይደለም።

በሀገራችን ውስጥ ብሄራዊ እርቅ እውን መደረግ እንዳለበት አበክረው የሚያምኑ ክፍሎች ለረጅም ጊዜ ሰፊ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ በስብስብ ደረጃ፣ በክቡር ፊታውራሪ መኮንን ዶሪ የሚመራ ድርጅት  እንዲሁም የ 25 ድርጅቶች ስብስብ የሆነው በሲያትል የተመሰረተው የፖለቲካ ድረጅቶች የብሄራዊ መግባባትና እርቅ ኮሚቴ፣  እንዲሁም  “ትብብር” የተሰኘው የሲቪክ ማህበራት ስብስብ  የሚጠቀሱ ናቸው።

እኔ ባለኝ መረጃ በዚህ ኮሚሽን አባላት ምርጫ ላይም ሆነ በኮሚሽኑ አወቃቀር ላይ ከላይ የጠቀስኳቸው ማናቸውም ቢሆኑ ስለተመሰረተው የብሄራዊ እርቅ ኮሚሽን ምንም አይነት ግብአት እንዲሰጡ  አልተደረገም።  ሀያ አምስቱ ድርጅቶች የመሰረቱት የብሄራዊ እርቅ ኮሚቴ፣ ቀደም ሲል ከፕሬዚደንት ሙላቱ ጋር ተገናኝቶ አላማውን እና ህልውናውን እንዳስታወቀ፣ በቀጣይም ለጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ ጽህፈት ቤትም ጊዜ ተሰጥቶት ሀሳቡን ለማቅረብ እድል እንዲሰጠው ቢያንስ ሁለት ደብዳቤ ጽፎ እንደነበረ፣ ባለፉት 10 ወራት ውስጥ በአዲስ አባባ ውስጥ በዚሁ የብሄራዊ እርቅ ጉዳይ ላይ  ያተኮረ ቢያንስ ሶስት ትልልቅ የምክክር ስብሰባወችን አንዳካሄደና  ቢያንስ ባንዱ ስብሰባ ላይ የመንግስት ባለስልጣኖች (የለውጥ ሀይሉ) ተገኝተው እንደነበረ እኔ ራሴ የማውቀው ጉዳይ ነው።

እነዚህ በቅን መንፈስ ተነሳስተው  በዚሁ አጀንዳ ላይ ሰፊ ስራ የሰሩ ክፍሎች በሂደቱ ላይ ግብአት እንዲሰጡ አለመደረጉ እምነትን ይቦረቡራል አላስፈላጊ ጥርጣሬንም ይፈጥራል።

ባጭሩ  በኔ እይታ ምንም እንኳ በኮሚሽን አባልነት የተሰየሙትን አንዳንዶቹን በግል የማውቃቸውና በችሎታቸውም ሆነ ለፍትህ ባላቸው አቋም አይበገሬነት እጅግ የማከብረቸው  ቢሆንም የኮሚሽኑ ምስረታ ነጻና ሁሉን አሳታፊ በሆነ አካል አለመካሄዱ፣ የተለያዩ ባለድርሻወችን ግብአት ያካተተ አለመሆኑና  አካሄዱ ግልጽነት የጎደለው መሆኑ ትልቅ ድክመት ነው እላለሁ።

ይህ ሂደት እጅግ ታላቅ ጥያቄ ውስጥ የሚገባው ደግሞ በኮሚሽኑ ውስጥ የተካተቱትን የተወሰኑትን በቅርበት ስንመለከት ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ ጥቂት ምሳሌወችን  ላንሳ፡

የኮሚሽኑ አባላት ቅንብር ጋር የተያያዙ ድክመቶች

የኮሚሽኑ አንዱ ተግባር በህወሀት መራሹ አገዛዝ ላላፉት 27 አመታት የተፈጸመውን የመብት ጥሰት መመርመር ነው እስከተባለ ድረስ እስካ ዶክተር አብይ ጠቅላይ ሚኒስቴር  መሆን ድረስ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስቴር ሀይለማርያም ደሳለኝ በዚህ ኮሚሽን ውስጥ መካተታቸው ፤ የኮሚሽኑን ታማኒነት በተለይም የሰባአዊ መብት ሰለባ በሆኑ ወገኖች በኩል እጅግ ዝቅ ያደርገዋል።

በጠቅላይ ሚኒስቴር ሀይለማርያም ዘመን   ሀገራችን ኢትዮጵያ እጅግ መጠነ ሰፊና አሰከፊ  የመብት ረገጣ የተካሄደባት ሀገር ነበረች። እርሳቸው ጠቅላይ ሚኒስቴር ከሆኑ በኻላ የተገደሉ፣ መዳረሻቸው የጠፋ፣ አካለ ስንኩላን የሆኑ የተገረፉ (ቶርች የተደረጉ) የተኮላሹ  ፣ ግብረ ሰዶም የተፈጸመባቸው. ፣ በግዳጅ የወሲብ ጥቃት የደረሰባቸው ከህግ ውጭ ንብረታቸው የተነጠቀ፣ የተፈናቀሉ ወዘተ ኢትዮጵያውያን መጠነ ሰፊ ናቸው። ታዲያ  የስርአቱ ግፍ ሰለባወች  እንዴት ነው ከእርሳቸው  ፍትህን የሚያገኙት? በተካሄደው የመብት ረገጣስ እርሳቸው ተጠያቂ ሊሆኑ የማይችሉበት  ሁኔታ ምንድን ነው?

አልፎ አልፎ እርሳቸው ለስም ብቻ ጠቅላይ ሚኒስቴር ተብለው የተቀመጡና ሁኔታውን ሁሉ ያሽከረክር የነበረው ህወሀት ነበር የሚለው አባባል በሰፊው ይስማል። ይህ እውነት ሊሆን ይችላል። ሆኖም ግን ይህ ጉዳይ በእርሳቸው በአቶ ሀይለማርያም አንደበት በእርቀሰላሙ ኮሚሽን ፊት መነገር የሚገባውና  ለህዝብ  በግልጥ መቅረብ የሚገባው አይደለምን? ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት ባንድ ድርጅት ውስጥ አንዱን ወንጀለኛ  ሌላውን ነጻ ማድረግስ ፍትህን ተግባራዊ ከማድረግ ጋር እንዴት ይጣጣማል?

ሁለቱ የቀድሞው ፕሬዚደንቶችም ጉዳይ በዚሁ ማእቀፍ ውስጥ የሚታይ ጉዳይ ነው። እዚህ ላይ ማናቸውንም ወንጀለኛ ናቸው ለማለት አይደለም። ሆኖም ግን በነሱ የስልጣን ዘመን የተካሄዱ የመብት ጥሰቶች በሚመረመሩበት በዚህ ሂደት ውስጥ እነርሱ መልሰው የእርቀሰላሙ ኮሚሽነሮች ሆነው መቅረባቸው ግራ የሚያጋባ ነው።

እርቀ ሰላሙ ከሰብአዊ መብት ጥሰት በተጨማሪ ሊመለከታቸው የሚገባው የተሌኤዩ ጉዳዮች ሊኖሩ እንደሚችሉና ለዚህም እነዚህ የቀድሞ ባለስልጣኖች ሊጫወቱት የሚችሉት ሚና እንደሚኖር አምናለሁ። ያ ግን በእርቀሰላሙ ኮሚሽን ውስጥ መግባትን  የግድ አይልም።

ሌላው ደግሞ የእርቀሰላሙ ስራ በሽወች የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን የቀጠፈው የደርግን አገዛዝን ዘመን ያደረሰውን ግፍ መመርመርን ያካትታል እስከተባለ ድረስ በዚያ ጊዜ በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ያገለግሉ  ግለሰቦችን በኮሚሽኑ አበልነት መሰየም  ከላይ የጠቀስኩትን አይነት ትልልቅ ጥያቄን እንደሚያሰነሳ  ግልጽ ነው።

ምንም እንኳ ጉዟችን ወደእርቅና ይቅር መባባል እንደሆነ ግልጽ ቢሆንም፣ በዚያ ወቅት በከፍተኛ የመንግስት ሀላፊነት ተመድበው ያገለግሉ የነበሩ ግለሰቦች  በኮሚሽኑ ውስጥ መካተታቸው የመብት ጥሰት ሰላባ ለሆኑ ሁሉ የሚያሰተላልፈው መልእክት አወንታዊ  አይሆንም ። እነዚያ ሰለባወች ከዚህ ኮሚቴ ይህ ነው የሚባል ፍትህን እናገኛለን ብለው በድፍረት በኮሚሽኑ ፊት ቀርበው ያለ አንዳች ፍራቻ የደረሰባቸውን በደል ሊገልጹ መቻላቸውም እጅግ አጠራጣሪ ነው።

እንዚህ የቀድሞ ባለስልጣኖች  ሀገራችንን ሊየገለግሉ የሚችሉባቸው እጅግ ብዙ ዘርፎች መኖራቸው ምንም አያጠራጥርም። የእርቀሰላም ኮሚቴ ግን ከነዚህ ውስጥ የሚመደብ አይሆንም።

ሶስተኛው ደግሞ የኮሚሽኑ አባል የተደረጉትን የፖለቲዩካ ድርጅቶች ከፍተኛ መሪወችን ይመለከታል።

ለኮሚሽን አባልነት የተመረጡት የፖለቲካ መሪወች እጅግ የማከብራቸውና አንዳንዶቹም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አብሬያቸው ሰፊ ስራን የሰራው ቢሆንም ባሁኑ ሳአት የፖለቲካ ድረጅት ከፍተኛ መሪወች በዚህ ኮሚሽን  ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ ግን በእርቀሰላሙ ሂደት ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን ነው።

እነዚህ ግለሰቦች የመብት ረገጣው ቀጥተኛ ሰለባወች እንደሆኑ እየታወቅ እንዴት ነው መልሰው አስታራቂ የሚሆኑት።

በሀገራችን ለማምጥት የምንሻው ፍትህንና ይቅርታን በዚህም ላይ ተመርኩዞ በጋራ መጓዝን ከሆነ እነዚህ ከፍተኛ የፖለቲካ መሪወች እንዴት ነው ለሁሉም እኩል ፍትህን ያጎናጽፋሉ ተብሎ በተቃዋሚወቻቸው ሊታመኑ የሚችሉት?

ይህ ሂደት ሂሳብ ማወራረድ ሳይሆን  ተበደልኩ የሚሉትን  ሁሉ የሚያደምጥ ይቅር መባባልን መሰረት ያደረገ ከሆነ እነዚህ የፖለቲካ መሪወችስ ሊጠየቁባቸው የሚችሉ ጉዳዮች ሊኖሩ እንደሚችል እንዴት ይዘነጋል? ይሀስ ከሆነ እነርሱ በሚመሯቸው ድርጅቶች  ጉዳት ደርሶብናል የሚሉ የህብረተሰብ ክፍሎች  በዚህ ኮሚሽን ላይ እንዴት ነው እምነት ሊኖራቸው የሚችለው?

እነዚህ የተለያዩ ድክመቶች የኮሚሽኑን ታአማኒነት በተለያየ አቅጣጫ  ጥያቄ ውስጥ ያስገቡታል።  ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል ነው እና  ባስቸኳይ ሊታረሙም ይገባል።

ጉድለቶቹን ለማረም ምን ይደረግ

በኔ እይታ የእርቀሰላሙ ሂደት መጀመር ለሀገራችን ያለው ጠቀሜታ እጅግ ከፍተኛ እንደመሆኑ መጠን ጅምሩ የሚታዩበትን ድክመቶች አስወግዶ ወደሚፈለገው ብሄራዊ እርቅና ሰላም ለመምጣት መደረግ አለባቸው የምላቸውን እንደሚከተለው አቀርባለሁ።

It is in our hand to create a better world for all who live in it.Mandela