ጥቅምት 02/2007
የኢሕአፓ የእርማ ት እን ቅስቃሴ
ቃል ኪዳን ይታደስ

ፓርቲያችን ኢሕአፓ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት፣ ለሕዝብ ያልተገደበ ዲሞክራሲና መብት መከበር፣ ለአምባገነናዊነት መወገድና ለሕግ የበላይነት መሥፈን ከምስረታው ጀምሮ ታግሏል። ኢሕአፓ ባሳለፈው
እጅግ መራራ ትግል እንዲያ የሚያኮራ ፓርቲ ሊሆን የበቃው ከላይ እስከታች ሁሉም በፓርቲው ዙርያ የተስባሰበው ኃይል ለፓርቲው ዓላማና መተዳደሪያ ደንብ በመገዛቱ ነበር:: ያ ቆራጥ ትውልድ የፋሽስቶችን
የስቃይ ዓይነቶች ተቋቁሞ፣ ሊረሸን መሳሪያ ተደግኖበት እንኳን በፍርሃት የመወርዛትና የመርበትበት ምልክት አልታየበትም። ይልቁንም ድል የሕዝብ ነው በማለት ሞትን እንደ አመጣጡ እያስተናገደ ነበር ለኢትዮጵያ
ሕዝብና ለድርጅቱ የነበረውን ፍቅርና ታማኝነት ቃላት ሊገልጹት በማይችሉት ጀግንነቱ አስመስክሮ ያለፈው::
ይህ በብዙ አባላቱ ደምና አጥንት የተመሠረተ ድርጅት በአሁኑ ወቅት ያለበትን ሁኔታ ብዙዎችን የሚያሳዝን ሆኖ እናገኘዋልን። ድርጅቱ በተወሰኑ አመራሮቹ የአመራር ጉድለት በራሱ የውስጥ ቅራኔ ተጠላልፎ እንዴት
እንደደከመ በገሃድ የሚታይ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ድርጀቱ በጸረ ዘረኝነት ትግሉ ውስጥ ግንባር ቀደም እንዳልሆነ ዛሬ የጎላ አስተዋጽዖ ማድረግ አልቻለም። ከውጭ ያሉት የፓርቲው ጠላቶች ጋር በውስጥ
የራሳቸውን ጣዖት የሚጠርቡ መሪዎቹ ድርጅቱንና አባላቱን ከመቼውም በላይ ከፋፍለው የራሳቸውን አንቱነት ብቻ በመስበክ ፓርቲውን ከፋፍለውታል። በድርጅቱ ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍል መፍትሔ ከመፈለግ ወያኔ
ጠቀም የሆነን ልዩነት ሲደልቁ ይሰማሉ ፣ ይነበባሉ፣ ይታያሉ።

ዛሬ የፓርቲው አባላት ቁጥር ከፓርቲው እድሜ ባነሰበት ወቀት ፓርቲው ከክፍፍሉ በኋላ ጠንካራ ሆኗል ፣ ወያኔ እኛን ፈርቶ ተርበትብቷል፣ ብለው የሚመጻደቁ አይጠፉም። እንኳን በሃገር ውስጥ በውጭ እንኳን
የፓርቲው ምንነት ከመግለጫ ሊያልፍ አልቻለም። በሕብረተሰቡ ማሃል ከዚህ በፊት ፓርቲው የነበረውን ክብር በፓርቲው ክፍፍል አጥቶ፣ በወቅታዊ ትግል ላይ መሪነት ተስኖት፣ ከአሉባልታና ከተረብ ያለፈ
አስተዋጽዖ ማድረግ ተስኖት ወይም በአንድ በኩል ብቻውን መቆም አቅቶት የሕብረትን ከለላ ሲሻ ነው የሚታየው። በሌላ በኩል ደግሞ በድንፋታና በስድብ ተወጥሮ ከተጨባጭ ሁኔታ ርቆ በፕሮፖጋንዳ ራሱን ለጥጦ፣ ለራሱ ግዙፍ እንደሆነ አስቦ ቅዠት በሆነ ሕልም ውስጥ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት ኢሕአፓ ደጋፊ አጥቶ
ሳይሆን በየወቅቱ በድርጅቱ መመሪያና ሕግ መተዳደር ያቃታቸው መሪዎች በድርጅቱ ውስጥ መከፋፈልን ፈጥረው፣ አባላትን በተሳሳተ መረጃ አጅለው የራሳቸውን የበላይነት ለመመስረት በሚያደርጉት ጥረት ድርጅቱ
የተደጋገመ መከፋፈል ገጥመውታል። በዚህም ምክንያት አባላት ድርጅታቸውን እየወደዱ ነገር ግን በክፍፍል ውስጥ አስተዋጽዖ እንዳያደርጉ ብቻ በገፍ ፓርቲውን ጥለውት ከዳር ቁመው ተመልካች ሁነዋል።
ይህንኑ ችግር ጎልቶ ፓርቲውን አሁን የደረሰበት ሁኔታ ከመድረሱ በፊት በቃልም ሆነ በጽሁፍ መፍትሄ ያቀረቡ አባላት ቁጥር በቀላሉ የሚገመት አይደለም:: ሆኖም ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ትዕግሥትም ሆነ
ፍላጎት የሌላቸው ጥቂት የአመራር ክፍሎች፣ ባጠቃላይ ከእውነት የራቀ ምክንያት በመስጠት አንጋፋ አባላትንና የወክንድን አመራር ከፓርቲውና ከወጣቱ ክንፍ (ወክንድ) ለማባረር ያደረጉት አሳፋሪ ድርጊት
ፓርቲው ምን ያህል የከፋ ችግር ውስጥ እንዳለ አመላካች ሆኗል። ሌላውን ትተን ይህ ከላይ የጠቀስነው
ድርጊት ብቻ እንኳን ጥቂት የአመራር አባላት ምን ያህል በተሳሳተ አቅጣጫ እንደነጎዱ ፍንትው አድርጎ ያሳየናል።
ይህንን የፓርቲውን ሁኔታ የተረዳን አባላት ድርጅቱ ከገባበት ዙሪያ ጥምጥም ከሆነ የመከፋፈል አባዜ እንዲወጣና ድርጅቱን አጠናክሮና አንድነቱን ጠብቆ ለፀረ ወያኔ ትግል ከመግለጫ ያለፈ ተጨባጭ ትግል
እንዲያደርግ ከተፈለገ ችግሩን አጥንቶ ለመፍታት የሚያስችል ጉባዔ ይጠራ በማለት መዋቅርን ጠብቀን ያደረግነው ጥረት ከድርጅቱ አመራሮች አወንታዊ መልስ ሳይሆን በሚያሳፍር መንገድ የድርጅቱ ሕግና ደንብ
በሚጻረር መንገድ ከድርጅቱ መባረር ደርሶብናል። ብዙ በአሜሪካ የሚገኙ ቻፕተሮች ታጥፈዋል፣ የወክንድ አመራሮች ከድርጅቱ ተባረው ለይስሙላ ወክንድ በሚል መግለጫ ይሰጣል፣ አባላት በገፍ ድርጅቱን ለቀው
ሄደዋል።

እኛ የፓርቲውና የወጣት ድርጅት (ወክንድ) አባላት ድርጅቱን በተለያዩ ምክንያት የተለዩትን አባላት በመፈለግ፣ የድርጅቱን ችግር በጋራ ለመፍታት ያደረግነው ጥረት ትንሽ አይደለም። ይህ ጥረት ከመነጋገር
ታልፎ በድርጅቱ ውስጥ የነበሩ ወይም ለለድርጅቱ የሚቀርቡ የሃገር ሽማግሌዎችን በማሰባሰብ ችግሩን በውይይት ለመፍታት ጥረት ማድርግ ተጀምሮ ነበር። ይህ ጅምር ቅራኔዎችን ከማባባስ በሰላም በውስጥ
የሚያልቁበትን መንገድ መሻት በሚል የተነሳውን የብዙሃኑን አባላትና ደጋፊዎች ሃሳብ በአካተተ መልኩ የተደረገ ጥረት ነበር። ምንም እንኳን የእርማት እንቅስቃሴው ይህ ሁኔታ በአመራር ከሚገኙ ግለሰቦች
የተፈጥሮ ጠባይ፣ የዲሲፐሊን ሁኔታ አንጻር የማያስኬድ መሆኑን ቢገነዘበውም ለብዙሃኑ ፍላጎት በመገዛት ሁኔታውን እስከ መጨረሻው ሲከታተለው ነበር። የእርማት እንቅስቃሴው አስቀድሞ እንደተነበየው ይህ በብዙ
ጥንቃቄ የተያዘው ሂደት ሃላፊነት በጎደላቸው፣ የፓርቲው ሕልውና በማይሰማቸው፣ ለግል ጥቅማቸውና ለግል ታሪካቸው ብቻ በሚያስቡ በሚያሳፍርና ሽማግሌዎችን ባስደመመ እንቢተኝነት ተደምድሟል።
የሽምግልናውን ሂደት ሆነ በፓርቲው ውስጥ የተፈጠረውን ችግር በሚመለከትም እንቢተኝነቱን የገለጸው ወገን ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ ጸያፍ በሆነ ቃላት ሲያብጠለጥሉ በድረ ገጾች፣ በፓልቶክና በሬዲዮ ተሰምተዋል፣
ተነበዋል። በፓልቶክ በቀረበው ቃለ ምልልስ ላይ መረጃም እንዲቀርቡ ተጠይቀው መረጃ ለማቅረብ ተስኗቸዋል። ስለ ድርጅቱ የወደፊት ዕድል “የወቅቱ አመራር” ተወካይ ራዕይ ያለው መፍትሔ መስጠት
አቅቶቶት መረጃ የሌለውን አሉባልታ ሲያሰማ ታዳሚውን እስከ ማሳዘን ደርሷል።
ዛሬ ሃገራችን ከገባችበት አረንቋ ለመውጣት ትብብር በሚያስፈልግበት ወቅት ችግሮችን ለመፍታት ውይይትን የሚጠይቁ አባላትንና የወጣት ክንፍ መሪዎችን ማባረር ችግሮችን አስወግዶ ድርጅቱን ለማሳደግ ሳይሆን
ድርጅቱን ለመግደል የሚደረግ የጥቂቶች ስውር ጥረት መሆኑን የእርማት እንቅስቃሴው አባላት እናምናለን። በተለይ በአደባባይ በጽሁፍና በፓልቶክ የሚደረጉ የስም ማጥፋቶች መረጃ እስከሌላቸው ድረስ ተቀባይነት
የማይኖራቸው የተለመዱ አሉባልታዎች እንደሆኑም እናምናለን። ራስ ወዳድ መሪዎች ስልጣናቸውን ላለመልቀቅ “ከስልጣን እንዳለቅ አባላት አስገደዱኝ” የሚለው የውሸት ሰበብ ለብዙ ዓመታት ሊቀጥል
እንደማይችልም እናምናለን።
የእርማት እንቅስቃሴው ይህንን በጥቂት ግለሰቦች ድርጅቱን ለመግደል የሚደረገውን ጥረት አለመቃወ ምም ይሁን በአድርባይነት እውነቱን እያወቁ አሉባልታን በመፍራት ዝምታን መምረጥ አሳፋሪና የታሪክ ተ ወ ቃሽ
የሚ ያ ደርግ ተግባር መሆኑን ያምናል። በተለይ በወቅቱ በአመራር ላይ የሚ ገኙት ን ይህ ለተ ፈጠረው ች ግር መፍ ት ሄ አለመፈለግ ድርጅቱን የሚጎዳና የራስን ስብዕና የሚነ ካ በመሆኑ ከ ዚህ አሳፋሪ ተ ግባር ወ ጥተ ው
ኢሕአፓዊ የሆነ ቆ ራጥነትን ይላበሱ ዘንድ አሁንም ደግመን ደጋግመን እን ጠይቃለን ። ድፍ ረት አግኝ ተ ው ለፓርቲው ጥቅምና የሰማዕታትን ቃል ኪዳን ለመጠበቅ ሲ ሉ በድብቅ የሚ ናገሩት ን አደባባይ አውጥተ ው
እን ዲታገሉ እንጠይቃለን። ዛሬ አሉባልታ ማለፍ ቢቻልም ከታሪክ ተወቃሽነት መዳን አይቻልምና ለእውነ ት ማ ደርን መምረጥ ከ እያ ን ዳን ዱ አመራር የሚ ጠየቅ መሆኑን አጥብቀን እናሳስባለን ።

ከበርካታ ዓመታት በኋላ የክፍፍሉን ምክንያት ለማጥናት ድርጅቱን አንድ ለማድረግ ብዙሃን አባላትና ደጋፊዎች በተለያየ መንገድ እንቅስቃሴና ግንኙነት ጀምረዋል። የድሮውም ይሁን የአሁኑ አባላቱና ደጋፊዎቹ
ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ለዚህ አኩሪ ተግባር ተዘጋጅተዋል። አባለትና ደጋፊዎች አደባባይ እየወጡ ይህ የክፍፍል አባዜ መቀጠል የለበትም በማለት መናገርና መሰባሰብ ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል። ይህንን
የፓርቲውን የመከፋፈል ችግር መርምሮ፣ ችግሩን አስወግዶ ፓርቲውን አንድ ለማድረግ የሚደረገውን ለሃገር ጠቃሚ እንቅስቃሴ ለማኮላሸት የሚደረገው ጥረት ደግሞ ትንሽ አይደለም። ኢሕአፓ በመከፋፈሉ ተጠናክሯል
ከሚሉ ወገኖች የምሰማው የሰለቸና በመረጃ ያልተደገፈ ጩኽት ደግሞ ይሰማል። በዚህ ጩኸት ውስጥ ምን አልባት በክፍፍሉ የጠነከረው የግል ጥቅማቸው እንጂ ኢሕአፓ እንዳልሆነ የአደባባይ ምስጢር ነው።

እነዚህ ክፍፍልን የሚያቀነቅኑ ክፍሎች እውን ፓርቲውን የሚወዱ ከሆነ፣ ለዓላማው የቆሙ ከሆነ የክፍፍል ከበሮውን ከመደለቅ ተቆጥበው ፣ ለአንድነት ለመስራት ዛሬም አልረፈደም። ዛሬም ቢሆን ለሁሉም የሚበቃ
የትግል መድረክ ሊፈጠር ይቻላል። በዚህ መድረክ ፓርቲውንም ሆነ ሃገርን የሚጠቅሙ ተግባሮች መፈጸም ይቻላል። ይህ አይሆንም ብሎ በክፍፍል መንገድ ለመሄድ የሚደረገው ጥረት የሚያስከትለው የታሪክ አተላ
ሆኖ መቅረትን ብቻ ነው። ስለዚህም መስመራቸውን ከብዙሃኑ ጋር ሊያስተካክሉት የግድ ይላል። በዚህ ዘመን
አባላትንና ደጋፊዎች በተሳሳተ መረጃ አጅሎ ለክፍፍል ማዘጋጀት ድርጅቱን ለአደጋ ማጋለጥ ነው። ኋላም በታሪክ ያስጠይቃል::

ፓርቲውን ወደ ተነሳበት ዓላማና አስራር ለመመለስ ከተፈለገ ወቅቱ ዛሬ ነው ። የጋራ አመራር መሠረት ያደረገ፣ ተጠያቂነትና ግልጽነት ያለበት አሠራርን መልስን በፓርቲው ለማስፈር የሁላችንም ጥረት አስፈላጊ
ነው። ድርጅቱ ከክፍፍል ወጥቶ ለሃገር የሚጠቅም ተግባር እንዲፈጽም ከተፈለገ ኢሕአፓ አንድና አንድ ብቻ ነው በሚለው መርህ ሥር መሰባሰብ ያሻል።
የእርማት እንቅስቃሴው ዛሬም ኢሕአፓ አንድና አንድ ብቻ ነው በሚለው መሪ መፈክሩ በመነሳት ኢሕአፓ አንድ የሚሆንበትንና የሚጠናከርበትን መንገድ የመሻት ትግሉን ይቀጥላል። ሌሎች አሳቡን የሚካፈሉትን
ወገኖች በማሰባሰብ ኢሕአፓን ለማፍረስ የተጀመረውን ስውር ደባ ያጋልጣል። አሉባልታዎች ቦታ አግኝተው አባላት እንዳይከፋፈሉ ከተጨባጭ መረጃ ጋር በማቅረብ አሉባልታውንና የስም ማጥፋቱን ከምንጩ
ከማድረቅ የበለጠ አማራጭ መንገድ የለም።
ኢሕአፓን አንድ አድርግን ትግላችንን ለማጠናከር በምንነሳበት ወቅት ትግሉ ቀላል እንዳልሆነ እንገነዘባለን ። ከውጭ በወያኔ ደጋፊዎችና በውስጥ ደግሞ ጦኦት ጠረባ፣ የግል ጥቅም፣ አድርባይነት፣ የስልጣን ጥም
እንደሚታገሉን እንረዳለን ። ቢሆንም ዛሬ ከአባላትና ከደጋፊዎች የሚገኘው ድጋፍ ከፍተኛ ነው። ይህ ድርጅት በውይይት ችግሩን ከመፍታት ውጭ ሌላ መፍትሄ እንደሌለው በብዙሃኑ የታመነ ነው። ለዚህም ነው
የእርማት እንቅስቃሴው በቆራጥነት ለፓርቲው አንድነት የሚታገለው። አሁንም በድጋሚ ይህንን ፓርቲውን አንድ ለማድረግ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ያልተቀላቀሉ አባላት፣ የአመራር አባላትና አካላት ትግሉን
እንዲቀላቀሉ ጥሪ እያቀረብን ይህንን የአንድነት ጥሪ የሚያሰናክሉትን ለሕዝብ ማጋለጥ እንደምንቀጥልም ቃል እንገባለን። በአመራር ስም በኢህአፓ ላይ የተፈጸመውን በደልና ክህደት በማስረጃ እየደገፍን ለህዝብ ና
ለአባላት ማቅረቡ የሚቀጥል ሲሆን ለሚደርሰው ሁሉ ጉዳይ ከዚህ በኋላ ተጠያቂ አመራር ነን ባዮች እንጅ የእርማት እንቅስቃሴው አባላት እንደማይሆኑ ከወዲሁ ማሳሰብ እንወዳለን::
ኢሕአፓ አንድና አንድ ነው !
የኢትዮጵያ ሕዝብ ያቸንፋል!

Phone: (202) 670-2387 P.O. Box 56521 Was hington, DC 20040

Leave a Reply