ሳውዲ አረቢያና ኢትዮጵያ የወታደራዊ ኃይል ስምምነት ተፈራረሙ !

 

ሳውዲ አረቢያና ኢትዮጵያ በወታደራዊ ኃይል ተባብረው ለመስራት መስማማታቸዉን በሳምንቱ መጀመሪያ ለሚኒስትሮች ካቢኔ በቀረበው ሪፖርት መካተቱን መረጃዎች ያስረዳሉ። ሳውዲ ወታደራዊ ኃይል ስምምነቱን የፈረሙት የመከላከያ ሚኒስትሩ እንደሆኑ ቢጠቆምም የሚለው በኢትዮጵያ በኩል ስምምነቱ በማን እንደተፈረም የተሰጠ ይፋ መግለጫ የለም ።

ምንም እንኳን መረጃው ከሳውዲ በኩል ይፋ ቢሆንም በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ስምምነት ስለመፈረሙም ሆነ ስለተዛማጅ ሁኔታዎች የተሰጠ ዝርዝር መረጃ የለም ። በተመሳሳይ ሁኔያ በሳውዲ የኢንባሲ ሪያድ ኢንባሲም ሆነ በ ጅዳ ቆንስል በኩል የተባለው ወታደራዊ ኃይል ስምምነት ስለመደረጉ ይህን መረጃ እስካስተለፍኩበት ሰዓት ድረስ ምንም አይነት መረጃ ተላለፎ አልተመለከትኩም ።

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ ፤ የደህንነት መስሪያ ቤቱ ኃላፊዎችና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ከወራት በፊት በሳውዲ ዋና ከተማ በሪያድን ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል !

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለወራት ሲጠበቅ የነበረው ግን ሲጓተት የከረመው የሰራተኛ ስምሪት ስምምነት በሚመለከት እስካሁን ስምምነት አለመደረሱን ማረጋገጥ ችያለሁ ። የሳውዲ ከፍተኛ ህግ አውጭ የአልሹራ ምክር ቤት ጉዳዩን ለሰራተኛ ሚኒስትር ስር ለተቋቋመ አንድ ኮሚቴ ካስተላለፈው ወዲህ ካሳለፍነው ሳምንት ጀምሮ በሁለቱ ሃገራት መካከል በተወሰነ ደረጃ መግባባት ላይ መደረሱን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድ ከፍተኛ ባለስልጣን ጠቁመው ነበር ። ያም ሆኖ ስምምነቱ በይፋ የሚፈራረሙበት ጊዜ አለመቆረጡን መረጃዎች ያስረዳሉ!

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ

Leave a Reply