Mengistu Musie

09/22/2016

አደጋው እና አይቀሬው ለውጥ

ከርዋንዳ የምንማረው

የምእራባውያን ለአፍሪካ ያላቸው አመለካከት

በሜይ 1992 የሁቱ ውክልና ያለው አንባገነን መንግስት መሪ ባለፉት አመታት 1990-92 ይካሄዱ በነበር የህዝብ ሰላማዊ ጥያቄወች እና በአለማቀፍ የዴሞክራሲ፣ የሰበአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ግፊት ህገወጥ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶችን ህጋዊነት በመስጠት ብሎም የአደራ መንግስት እንዲመሰረት ምርጫም ስላልነበረው በሀሳብ ላይ በነበረበት ወቅት እናም አንዳንድ የፖለቲካ መሸሻሎች በነበረው ሁቱ አመራር ቢጀመሩም፤ ጅማሮው ከልብ እና የአገሪቱን እና የህዝቧን ደህንነት ተመርኩዞ ሳይሆን ግፊትን ለመቀነስ የተዘየደ ስለነበር የርዋንዳ ገዥው ክፍል መንታ ጎዳና እና መንታ ተግባራትን ማካሄድ ተየያዘው። ውጥረትን የመቀነስ ተግባርን ይፋዊ በሆነ መልክ እያካሄደ ውጥረቱን ወደከፍተኛ የማሸጋገር ስራ ደግሞ በውስጥ ህቡ በሆነ አካሄድ ይሰራ እንደነበር በግዜው የድህረ ምረቃ የምርምር ስራውን በሀይማኖት እና በጎሳ እርእስ ይሰራ የነበረው የአይን እማኝ ቲሞቲ ሎንግማን (Timothy Longman) (6 በሚያዚያ 2015) ባወጣው የዋሽንግተን ፖስት አርቲክሉ አስነብቧል።
ይህንኑ መጣጥፍ በመመርኮዝ እና በአገራችን ዛሬ በመካሄድ ላይ ያለው ሕዝባዊ ትግል በአንድ በኩል። የዘር ስርአትን ወደጥንታዊት እና ስልጡን ህዝብ ለግል አጀንዳ ማስፈጸሚያ ሲል በተግባር እያካሄደ ባለው መንግስት በሌላ በኩል፤ ይህን መንግስት በፋይናንስ፣ በፖለቲካ፣ በወታደራዊ ሀይል ማጠናከር የጡት ልጅ አድርገው የሚጠቀሙበት የአለም ልእለ ሀይል እና የምእራባውያኑ አቋም በሶስተኛ እረድፍ አስቀምጠን በጥሞና ለማየት እና አጀንዳውን ደግሞ በጥልቅ ተገንዝበን ትግሉን አቅጣጫ የማስያዝ፣ እና ሊደርስ የሚችለውን ከዚህ አሁን ከምናየው የከፋ ፍጅትን ለማምከን ከታሪክም አሁን ከምናየውም ተጨባጭ ተግባራት ተመርኩዘን መንቀሳቀስ እንዲኖርብን ለማስገንዘብ ነው።
ወደእርእሴ ስመለስ እርዋንዳ በክልንተን አድሚኒስትሬሽን እንደተነገረው ድንገት የተከሰተ ወይንም የክልንተን ካቢኔ ያላወቀው ወይንም ያልገመተው ሳይሆን፤ ለፍጅቱ ብዙም ያለመጨነቅ፤ በተለይም ለእነርሱ ጥቅምም ጉዳትም የለው ከሚል እሳቦት በመነጨ የታየ አስቀያሚ ሊከሰት የማይገባው ፍጅት ከናዚ ጀርመን የስድስት ሚሊዮኖች ፍጅት በኋላ ይህ የርዋንዳ ፍጅት ለምእራባውያኑ አሳፋሪም አስገማችም ተግባር ነበር።
ሎንግማን በ1992 ገብቶ ያየውን ሲተርክ በቀጣይ አስራሁለት ወራት አገሪቱ ወደከፋ የዘር ግጭት ስትሄድ መታዘቡን እና ከውጭ ምንም ሊደረግ አለማታሰቡን ያትታል። የልቅስ በስልጣን ላይ የነበረው የሀበርማና መንግስት የውጭ ውጥረት ለመቀነስ እና በህዝብ ትግል ተገዶ ወደመንግስት የጨመራቸውን ተቃዋሚወች ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሰላም መዛባትን በማሳበብ እነርሱን ተጠያቂ ማድረጉን እና የድብቅ ስራውን ቀጠለበት። በሌላ በኩል ጥሪውን ተቀብለው ስልጣን የተጋሩት የተቃዋሚ ፓርቲወች የፖሊስ፣ የጦርሰራዊት፣ እና የደህንነት መዋቅሩን ስለማይቆጣጠሩ እንዲሁ ሀይል አልባ መሆናቸውን ደጋግመው ማስተጋባት እና አደጋውን ማሳየት ጀምረው ነበር። ይህ ሲሆን የፕሮፖጋንዳ ስራውን የተቆጣጠሩት የሁቱ ባለስልጣናት በነዚሁ ተቃዋሚወች ላይ ዘመቻ ያደርጉ ጀመር። ሕዝቡ የድብቁ መንግስታዊ መጥፎ ስራን ማየት ባለመቻሉ ተቃዋሚወች የባሱ ጸረ ሰላም ናቸው የሚለውን ፕሮፖጋንዳ ማስተጋባቱን ተያያዘው። በአገሪቱ በተለይም በኪጋሊ የነበረው ውጥረት ከሮ እጅግ የሚያስፈራራ ሁኔታወች ይታዩ ጀመር። ይህ 1993 ሲሆን የክልንተን መንግስትም ሆነ አውሮፓውያኑ ሰፊ ግዜ እና እድሉም እያላቸው። በይበልጥም አደጋውን በግልጽ እያዩት የርዋንዳን ሕዝብ ለማህበራዊ ሳይንስ የቤተ ሙከራነት ተጠቀሙበት ሊያሰኝ በሚያስችል ግምት ጉዳያችን አይደለም ብለው አንድን የተባበሩት መንግስታት አባል ሀገር ሕዝብ ለእልቂቱ አዘጋጁት። Timoty Longman በአፕሪል 1993 የምርምር ተግባሬን ሳልጨርስ እጅግ ሁኔታው ስላሰጋኝ ኪጋሊን ለቅቄ ወጣሁ ይላል። እንደሱም አባባል የዩናይትድ ስቴትስ ተወካይ ጉዳዩን ለመንግስታቸው እንዳስታወቁም ገልጿል። ሆኖም ነገሩ ካለፈ በኋላ የተለያዩ የምእራብ መንግስታት የክልንተንን ጨምሮ እንደገለጹት አለማወቃቸውን ቢሆንም እውነታውን በተመለከተ እኔና Alison Des Forges አሁን በህይወት የሌለው ዲፕሎማት ደጋግመን አስገንዝበናል። እንዴውም የርዋንዳን ጀኖሳይድ በተመለከተ የቡሽ አስተዳደር ገና በ1992 መባቻ ላይ እንደደረሰው የሚያሳይ መልእክቶች ነበሩ። ሆኖም በግዜው መንግስት ዝውውሩ ወደክልንተን ሲመጣ የመጀመሪያ አጀንዳ ሆኖ ሊቀርብ የሚገባው ይህ ፍጅት ሳይሆን ቀርቶ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ በዘመናዊት አለም ፊት በቆንጨራ እና በተገኘው ሁሉ ስለት ታረደ።

ኢትዮጵያ ዛሬ

ሀያላኑ ከምንግዜውም በበለጠ ሁኔታውን ያውቃሉ። የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ የሚያሳየው በስልጣን ላይ ያሉት የሕወሐት መሪወች ፈጽሞ ከጥፋት የማይመለሱ መሆኑን እያሳዩን ነው። የእነርሱ እቅድ ወደፍጅት መውሰድ እንደሆነም በተለያዩ ሚዲያወች በሚያቀርቡት ለመረዳት ችለናል። በአጭር ባጭሩ ልዘርዝር።

• አባይ ጸሀየ በሰሞኑ ከስዩም መስፍን ጋር በፋና ብሮድካስቲንግ ባደረገው ውይይት እርዋንዳን የሚዘክር እና የሌለ ትግራውያን እየተፈናቀሉ መሆኑን አይን ባወጣ ውሸት ነገረን
• በባህርዳር የውጭ ዜጎችን የአበባ ማሳ አቃጥለው በሕዝብ ለማሳበብ እና ሕዝቡን ተጠያቂ የማድረግ ጸያፍ ስራ ሰሩ። ለእነሱ የሚጠቅመው ሕዝብን መግደል፣ እና በገፍ ወደማጎሪያ ካምፖች ማጋዙን በአለም ፊት ህጋዊ ለማድረግ የተዘየደ መላ መሆኑ ነው።
• በደብረታቦር ወህኒቤቱን በእሳት ማጋየት እና ዜጎች እንዲያልቁ የተሞከረው ወንጀል የዚሁ የፍጅት እቅድ አንድ ክፍል መሆኑ ነው።
• የቅሊንጦን ማጎሪያ ኮምፓውንድ ማቃጠላቸው። ይህ የማሰቃያ ካምፕ ጋዜጠኞች፣ የሰበአዊ መብት ተሟጋቾች፣ እና የታወቁ አክቲቪስቶች የታጎሩበት ሲሆን በእርግጥም ታርጌት ያደረጓቸውን የጎንደር ወልቃይት ወገኖችን በእሳት እንዲቃጠሉ በማድረግ ግባቸውን መተዋል
• በጎንደር አራዳ ቅዳሜ ገበያ ለህዝብ የሚያገለግሉ ሱቆችን ማቃጠል ሁለት ጥቅም የያዘ የሕወሐት አላማ መሆኑ። አንደኛው የትግራይ ሰወችም ንብረት ሲኖር እነዚህን ሰወች በአካባቢው ንብረታችሁ ወደመ በማለት አንድም የትግራይን ህዝብ የጸረ አማራ አላማን ማስጨበጥ፣ በሌላ መልኩ ይህ ህብረተሰብ ወያኔዋ ድርጅት ገና ስትነሳ በግንባር ቀደም ጠላቴ ነው ብላ የተደራጀችበት፣ የዘፈነች፣ የዘመረችበት እና የፎከረችበት ሲሆን ተቀጣጣይ ገበያወች መውደም ዞሮ ዞሮ የሚጎዳው ያንን ጠላት ህዝብ ስለሆነ
• በመተማ ነዋሪ የነበሩ ዜጎችን ንቅናቄ በእነርሱ ላይ ሳይሆን የመብት ጥያቄ ሆኖ እያለ ሕወሐትዋ ለይታ አንድ ዘርን ወደ ገላባት ማሻገር እና ቀሪውን ለመበቀል እንዲመች ማዘጋጀት።
• ስዩም መስፍን፣ በረከት ስምኦን፣ ማንትሴ እረዳ የሚሏቸው የሕወሐት ቱባ ባለስልጣናት በየተራ ያደረጉት የእንጨርሳችኋለን ፉከራ፣ ማስጠንቀቂያ እና ዘርን ከዘር የሚጋጭ ቅስቀሳ ሁሉ
አሁንም ተመሳሳይ እርዋንዳ በመደገም ላይ መሆኑ።

ትናንት ማክሰኞ ሴፕቶእምበር 20 ቀን የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ባደረጉት የ43 ደቂአቃ ንግግር ሙሉውን ማለት በሚያስደፍር የዘር ግጭት ማነሳሳት ወንጀልን፣ የህዝብን የምርጫ ሳጥን መገልበጥን ሁሉ ያስገነዘቡ ቢሆንም አደጋው በኢትዮጵያ ሕዝብ አፍጦ መጦ እና በቅርብ የስራ ዘመናቸውን ጨርሰው የተሰናበቱት አምባሳደር Patricia M. Haslach በአገሪቱ ያንዣበበውን ጥቁር ዳመና እና እየፈሰሰ ያለውን ደም በጎንዮሽ አነጋገር በመሰናበቻ ምሽታቸው መጠቃቀሳቸው ሌላው ጉዳይ ሲሆን። በዘር ላይ የተመረኮዘ ፍጅት እየተካሄደ መሆኑን ሃያላኑ እያወቁ አደጋውን ለመግታት ግን ምንም አይነት እርምጃ አልወሰዱም። የአውሮፓ ህብረት እሰይው የሚያሰኝ ጅማሮ ቢይዝም ይህን ሰፊ ዘር የማጥፋት ፍጅትን እውን በሆነ ተግባር የሚያስቆም እርምጃ አልወሰደም። ይባስ ብሎ በዩናይትድ እስቴትስ አንዳንድ የኮንግረስ ሰወች ብቅ ጥልቅ ከማለት ያለፈ« በምስራቅ አፍሪቃ ሁነኛ ወኪላቸው እና የሽብር ዘመቻው ሸሪክ የሆነው መንግስት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እና በተለይም በሁለቱ ዘሮች ያተኮረን ፍጅት እያወቁ ምንም አይነት ጣልቃ አለመግባታቸው የቡሽ እና የክልንተን መንግስታት በርዋንዳ ያሳዩትን የምን ግዴ ስራ መድገም መሆኑን ግዜው ካለፈ አቧራው ወደቦታው ከተመለሰ፣ የደም ጅረቱ በዝናብ ከታጠበ፣ በኋላ የዲፕሎማሲ ቋንቋ ይዘው መውጣታቸው አይቀርም። ታሪክ ዳግም ፍርዷን ልትሰጥ እየዘገበች ቢሆንም ሰወች አላፊ ናቸው እና ብሎም የደሀ ህዝብ ደም ጉዳያቸው አይሆንም።

የተቃዋሚ ሀይሎች

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ሀይሎች ከባድ የአደንዝዝ ድባብ ውስጥ መሆን ሌላው አሳሳቢ ተውኔት ነው። በባለ ብዙ ቢሊዮኖች እንቨስትመንት እና የአገሪቱን ካዝና በእጁ ያደረገ። የአየር እና የምድር ጦሩን የተቆጣጠረ። ደህንነቱን አጠናክሮ ሙሉ ለሙሉ በእጁ ያስገባ የአንድ ዘር መንግስት ነኝ ባይ የጦርነት ከበሮ እየመታ። ዜጎችን በዘር መድቦ በጠላትነት ነጥሎ እየገደለ ባለበት እና ይህች አገር ወዴት እያመራች መሆኑ ዳብዛው በጠፋበት በዚህ ክፉ ቀን በአንድ ቆመቅ ለአንድ አላማ ተሰልፈው ከእነርሱ በእጅጉ የገዘፈ እና የደለበ ጠላትን ለመግጠም አለመቻል ሌላው ችግር ነው። ግለሰቦች ዝናንም ሆነ ክብርን አገር ሲኖር፣ ሕዝብ ሰላም ሲሆን ማግኘት መቻላቸውን እረስተዋል ወይንም እንደተራው የቻሉትን ለመወርወር ብቻ ቆመዋል።
ሌላው አስፈሪ ተውኔት ከላይ የቲሞቲ ሎንግ ማንን አጭር ምሳሌ ለማመልከት እንደሞከርኩት ወያኔዋ የመጀመሪያው እቅድ እና ፍጅት አደጋ አለው ብላ ብታይ ወደሁለተኛው ልትሸጋገር ይጠበቃል። ፕላን A B C ሊኖሯት ይችላሉ። ለምሳሌ ልክ እንደርዋንዳ የገደለችውን ገድላ ወደየሽግግር መንግስ ጥሪም በሃያላኑ ግፊት ብትሄድ በትረ መንግስቷን በእጇ ስላደረገች ወታደራዊው ሀይል፣ ደህንነት፣ የአየር እና የምድር ጦር የአካባቢ ፖሊስና የፌደራል ሁሉም በእጇ ያለ በእርሷ እዝ የሚታዘዝ፤ ስለሆነ ሁለተኛውን እቅድ ብትይዝ ለዳግም የዘር ፍጅት እንዴውም የእርሷን ወንጀል የሚሸፍን፣ ጥሩም ምክንያት የሚሆንላት ታገኛለች ማለት ነው።
ዛሬ ህዝባችን ብቻውን እየታገለ እየሞተ መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው ስለሆነ ተቃዋሚ ሀይሎች ቢተባበሩ፣ በአንድ ቢቆሙ ከሀይል ማሰባሰብ በበለጠ ለህዝቡ የሚሰጠው የሞራል ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን ሊታወቅ ይገባል። የሽግግር የምንጥሴ የሚለው የነልደቱ ስራወች ከወዲሁ ቢታወቅ እና ወያኔን ለማስወገድ ታጥቆ መነሳቱ ልክ እንደህዝቡ ማለት ነው አማራጫችን አንድ ብቻ መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል። ምንም አይነት ሁኔታ ቢቀየር ወያኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ናት! ወያኔን ማመን ቀብሮ እንጅ በአንድ መክሮ ሊሆን ግን አይችልም።

ጸረ ሕዝቧ ወያኔ በህዝብ ትግል እናስወግድ !!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

References,

Newly released documents reveal the extent of warnings about the impending Rwandan genocide. The U.S. knew, but just didn’t care.
WASHINGTONPOST.COM

Leave a Reply